Feb 19, 2018

ፎረም 65፦ ኢትዮጵያ ወዴት? እንዴት? (እንግዳ አቶ ልደቱ አያሌው)

ሀገራችን መሰረታዊ የለውጥ እድልና አጋጣሚ ወቅት ላይ ትገኛለች። የለውጥ አቅጣጫው ወዴት ነው? ወደ ለውጥ ግቡ እንዴት እንድረስ? ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር የሚከተሉትን ነጥቦች ዳስሰናል፦ 1. የአቶ ለማና ኦሕዴድ ፓለቲካ እንድምታው 2. የሀገራዊ መግባባት ኮሚሽን መመስረት አስፈላጊነት 3. በተቃዋሚው ውስጣዊ መግባባት እንዲፈጠር 4. የኢሕአዴግ መሪዎችና አባላት ዋስትና ጉዳይ።


[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/SjC1ws ያድምጡ። (መጠን፦ 7.99 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Feb 9, 2018

ፎረም 65፦ የዐማራ-ኦሮሞ አጋርነት በነገዋ ኢትዮጵያ

በተቃዋሚው ጎራ የሚገኙ ዐማራና ኦሮሞ ሊሂቃን ከጊዜያዊና ስልታዊ አጋርነት ወደ ዘላቂና ስትራቴጂክ አጋርነት ለመሸጋግር የኦሮሞ ሊሂቃን ከዐማራ ሊሂቃን ምን ይጠብቃሉ? የአለመግባባት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?  ከትናንቷ ፡ ከዛሬዋና ከመጪዋ ኢትዮጵያ አንጻር የአለመግባባት መንስኤዎችን ለመዳሰስና የመፍትሄ ሃሳባቸውን እንዲጠቁሙ ሁለት ኦሮሞ ወገኖች በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን ዶ/ር በያን አሶባ ከዩናይትድ ስቴትስ እና አክቲቪስት አቶ ገረሱ ቱፋ ከኔዘርላንድ ናቸው። ውይይቱን ያድምጡ!
[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/CsqaZJ ያድምጡ። (መጠን፦ 10.2 MB)]
[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Jan 26, 2018

ፎረም 65፦ ትውውቅ ከ"ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ" ጋር

ትውውቅ ከ"አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ" ጋር። እንግዶች ሊቀመንበር አቶ ነሲቡ ስብሃት እና የንቅናቄው የፓለቲካና ፕሮፓጋንዳ ክፍል ሃላፊ አቶ ጸሃይ ደመቀ ናቸው። ለተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የንቅናቄውን ድረገጽ www.Ethiopiachen.org ይጎብኙ።[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/FfJ38b ያድምጡ። (መጠን፦ 6.77 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Jan 23, 2018

ፎረም 65፦ የመግባባት መኻል መንገድ

መንግስትም ተቃዋሚዎችም መኻል መንገድ ላይ መገናኘት እንዳለባቸው በቅርቡ የተፈቱት ዶ/ር መረራ ጉዲና አሳስበዋል። ተቃዋሚው የት ድረስ መሄድ አለበት? መንግስትስ?[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/xDA8gK ያድምጡ። (መጠን፦ 6.64 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]

Jan 11, 2018

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግ ተለውጧልን? #Ethiopia #Forum65

ኢሕአዴግ ተለውጧልን? የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ መግለጫና የአባል ድርጅቶች መሪዎች ቃለምልልስ ኢሕአዴግ መለወጡን አመልካች ነውን? እንግዶቻችን አቶ ግርማ ካሳ ከዩናይትድ ስቴትስ ፡ አቶ እስራኤል ገደቡ ከኔዘርላንድ ፡ ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል ከኢንግላንድ እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ከአውስትራሊያ ናቸው።[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/BTK4DM ያድምጡ። (መጠን፦ 8.79 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Jan 9, 2018

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግ ፡ ዕርቅና ሀገራዊ መግባባት

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ "የተሻለ ሀገራዊ መግባባትን" ለመፍጠር የሚወሰዱ እርምጃዎች እንደሚኖሩ ገልጿል። የሥራ አስፈጻሚው የእርምጃ ውሳኔዎች ከዕርቅና ሀገራዊ መግባባት አንጻር ፋይዳቸው ምንድን ነው?[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/AXVhNw ያድምጡ። (መጠን፦ 3.90 MB)]
[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]Dec 27, 2017

ፎረም 65፦ የ2017 ዳሰሳ - የአመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ማን?

ፎረም 65 ለዲያስፓራው ማህበረሰባችን መልካም አዲስ አመት እየተመኘን ፡ በ2017 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እነ ማን ነበሩ? የፎረም 65ትን የ2017 ዳሰሳ ውይይት  ያድምጡ! [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/4ZCdse ያድምጡ። (መጠን፦ 6.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]
Dec 26, 2017

Dec 13, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 2) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

እንግዳችን ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻል በፎረም 65 ይተነትናል። [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/RNt1Yx ያድምጡ። (መጠን፦ 5.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]
Dec 7, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 1) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ የኢትዮጵያን ፓለቲካ ወቅታዊ ሁኔታዎች አስመልክቶ በጻፋቸው ተከታታይ ጽሁፎቹ የህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ ወደ ዴሞክራሲያዊነት እንዴት መሻገርና መዳበር እንደሚችል ተንትኗል። እንዲሁም ሰሞኑን በጻፈው ጽሁፍ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻልም አመላክቷል።

"መዳበርና መሻሻል የሚመጣው አሮጌውን በመታገል ሳይሆን አዲሱን በመገንባት" መሆኑን በፎረም 65 እንገነዘባለን። ከዚህ አንጻር ከዶ/ር ጸጋየ አራርሳ ጋር አገራችን ያለችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ በሰፊው ዳስሰናል።

ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/XmF7c8 ያድምጡ። (መጠን፦ 6.92 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]


ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive