Mar 31, 2017

ፎረም 65፦ ለድርድር አደራዳሪ ያስፈልገዋልን?

በገዢው ፓርቲ መሪነት የሚካሄደው የቅድመ ድርድር ውይይት ወቅት ኢሕአዴግ ድርድሩ ገለልተኛ ሶስተኛ አካል አደራዳሪዎች እንደማይኖሩትና ተደራዳሪዎች በፈረቃ እንዲመሩት ወስኗል። ፎረም 65 የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑትን ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱን በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡን ጋብዘናቸዋል።








Mar 29, 2017

ፎረም 65፦ የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች (ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ እና ዶ/ር ብርሃኑ ለንጂሶ)

የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነት ምንድን ነው? የብሔር ኃይሎች ውስጥ ያሉት ልዩነቶችስ ምንድን ናቸው? እንግዳቻችን ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ እና ዶ/ር ብርሃኑ ለንጂሶ ናቸው። (ለድምጽ ጥራት ጉድለት ይቅርታ እንጠይቃለን)



[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/jJLGpY ያድምጡ። (መጠን፦ 4MB) ]






Mar 20, 2017

ፎረም 65፦ የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች (አቶ ጀዋር መሐመድ)

የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነት ምንድን ነው? የብሔር ኃይሎች ውስጥ ያሉት ልዩነቶችስ ምንድን ናቸው? እንግዳችን አቶ ጀዋር መሐመድ ነው።



[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/dPSQxR ያድምጡ። (መጠን፦ 3MB) ]








Mar 9, 2017

ፎረም 65፦ በድርድሩ የዲያስፓራ ሚና ምን ይሁን?

ኢሕአዴግና ሀገር አቀፍ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ድርድር ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ዲያስፓራው በድርድሩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ ወይም ተጽዕኖ ማድረግ አለበት ወይስ የለበትም? እንግዶች፦ አቶ እስራኤል ገደቡና አቶ ግርማ ካሳ።



[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/cvqemF ያድምጡ። (መጠን፦ 8MB) ]








Mar 5, 2017

ፎረም 65፦ ከቅራኔ ወደ መግባባት ("የት ነበርሽ?")

ቅራኔ ምንድን ነው? ቅራኔ ለምን ይፈጠራል? እንዴት ይገለፃል? ቅራኔን ለመፍታት መነጋገር ጥቅሙ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎች ከቅራኔ ጋር የተያያዙ ነጥቦች ላይ ለመወያየት እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ  (Conflict Resolution Expert) ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው።

ዶ/ር ብርሃኑ በኦልድ ደሚኒየን ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚንስትሬሽን ፕሮፌሰር ሲሆኑ ፡ የ"መንግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/63AWIL ያድምጡ። (መጠን፦ 6MB) ]







ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive