Sep 30, 2017

ፎረም 65፦ መሪው ማን ነው? ኢሕአዴግ ወይስ ህወሓት? #Ethiopia #Forum65

የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በኢትዮጵያ ፓለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ደህንነትና መከላከያ ላይ ያላቸው የተጽዕኖና የስልጣን መጠን ሚዛናዊ ነው ወይንስ አይደለም? የህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ክብሩ የማን ነው? በ2009 ዓ.ም. የእሬቻ በዓል ስለሞቱት ወገኖቻችን ተጠያቂው ማን ነው? እንግዶቻችን አቶ እስራኤል ገደቡ እና አቶ ግርማ ካሳ ናቸው።
[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/7EoBEA ያድምጡ። (መጠን፦ 5.81 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]





Sep 23, 2017

ፎረም 65፦ የህብረብሄራዊ ቤተሰብ ልጆች ማንነት #Ethiopia #Forum65

በአገራችን የብሔሮችን መብት ለማስከበር በሚያደርገው የፓለቲካ ሂደት ውስጥ ሰፊ ትኩረት ያላገኘው የህብረብሄራዊ ቤተሰቦች የማንነት ጥያቄ፣ ጥቅምና ስጋት ነው። በተለይም ወላጆቻቸው ከተለያየ ብሔር የሆኑ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው ችላ የተባለ፣ የታፈነና የተገፋ እንደሆነ ይገልፃሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳቡን እንዲያካፍለን ከህብረብሄራዊ ቤተሰብ የተወለደው ጋዜጠኛ አቶ አናንያ ሶሪ እንግዳችን ነው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/YgWUp7 ያድምጡ። (መጠን፦ 4.03 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/YgWUp7 ያድምጡ። (መጠን፦ 4.03 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]





Sep 19, 2017

ፎረም 65፦ የአቶ ልደቱ ፋይዳ

አቶ ልደቱ በኢትዮጵያ ፓለቲካ አነጋጋሪ እና ትኩረት ሳቢ ፓለቲከኛ ቢሆኑም የቅንጅት አለመግባባት በአቶ ልደቱ ላይ ያደረሰውና እስካሁንም የሚያደርሰው አሉታዊ ድባብ ቀጥሏል። ይህ ለምን ሆነ? የአቶ ልደቱ ፓለቲካዊ ፋይዳ ምንድን ነው? አቶ ልደቱ ወደ ቀድሞው ፓለቲካዊ ሞገስና ተሰሞነታቸው እንዴት መመለስ ይችላሉ?

በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን ለመግለፅ  አቶ ሽመለስ በዛብህ በስዊትዘርላድ ነዋሪና የአውሮፓ፡ የአፍሪካና የአውስትሬልያ የቅንጂት ድጋፍ ሰጪ የቀድሞ ቃልአቀባይ የነበሩና  እንዲሁም ዶ/ር ብርሃኑ ለንጅሶ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ በፎረም 65 እንግዶቻችን ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/GW9kEJ ያድምጡ። (መጠን፦ 4.56 MB) ]



Sep 18, 2017

ፎረም 65፦ ግጭት በኦሮሚያና በሶማሊ #Ethiopia #Forum65

በኦሮሚያና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ ከተሞችና መንደሮች የተፈጠረ ግጭት የብዙ ሰዎችን ህይወትን አጥፍቷ፤ በርካቶችን አፈናቅሏል።፡ የግጭቶቹ መንስዔ ምንድን ነው? ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ እንግዶች ከሁለቱ ክልሎች ተወላጆች ጋብዘናል።

እንግዶቻችን የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዶ/ር ኡስማኤል ቋዴህ እና የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ አቶ ግርማ ጉተማ ሲሆኑ ፡ በኦጋዴን አካባቢ ለረዢም አመታት የቆየውን አለመረጋጋት አስመልክቶ የአለማቀፋዊ ሰብዓዊ መብት የህግ ባለሙያ የሆነውን ዶ/ር አባድር ኢብራሂም አካባቢውን አስመልክቶ ትንታኔ እንዲሰጠን አብሮን ይገኛል። 


[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/caUyZR ያድምጡ። (መጠን፦ 6.51 MB) ]







Sep 13, 2017

ፎረም 65፦ 2009 የትውልዳዊ ሽግግር ዓመት

2009 ዓ.ም. የትውልዳዊ ሽግግር ዓመት ነበር። በ2009 ዓመት ፎረም አገራዊ ትኩረት የሳቡ አበይት ጉዳዮችን እናስታውሳለን። እንዲሁም ከዚህ አለም በሞት የተለዩንን ትኩረት ሳቢ ግለሰቦች እንዘክራለን።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/BJ52Sdያድምጡ። (መጠን፦ 4.09 MB) ]






Sep 8, 2017

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግና ቅቡልነት (legitimacy)

ለአገራዊ መግባባት መዳበር የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሚና ወሳኝና ሰፊ ነው። ሆኖም ኢሕአዴግ የቅቡልነት (የእውቅና እና የተቀባይነት/legitimacy) ሰፊ ተግዳሮት አለበት።

- ኢሕአዴግ ቅቡልነት ለምን ጎደለው?

- የቅቡልነት ጉድለት መዘዙ ምን ነው?

- የኢሕአዴግ ቅቡልነት እንዴት ይጨምር?

- በቅቡልነት የተቀናቃኝ ኋይሎች ሚና ነው?

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ እንግዳችን ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/1EvB6D ያድምጡ። (መጠን፦ 6.82 MB) ]







ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive