Feb 9, 2018

ፎረም 65፦ የዐማራ-ኦሮሞ አጋርነት በነገዋ ኢትዮጵያ

በተቃዋሚው ጎራ የሚገኙ ዐማራና ኦሮሞ ሊሂቃን ከጊዜያዊና ስልታዊ አጋርነት ወደ ዘላቂና ስትራቴጂክ አጋርነት ለመሸጋግር የኦሮሞ ሊሂቃን ከዐማራ ሊሂቃን ምን ይጠብቃሉ? የአለመግባባት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?  ከትናንቷ ፡ ከዛሬዋና ከመጪዋ ኢትዮጵያ አንጻር የአለመግባባት መንስኤዎችን ለመዳሰስና የመፍትሄ ሃሳባቸውን እንዲጠቁሙ ሁለት ኦሮሞ ወገኖች በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን ዶ/ር በያን አሶባ ከዩናይትድ ስቴትስ እና አክቲቪስት አቶ ገረሱ ቱፋ ከኔዘርላንድ ናቸው። ውይይቱን ያድምጡ!
[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/CsqaZJ ያድምጡ። (መጠን፦ 10.2 MB)]
[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive