Aug 24, 2013

“አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” - ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ

ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ
የኢህአዴግ ባለስልጣኖችና ደጋፊዎች ከየትኛውም ዜጋ በላይ ዋስትና እንደሚፈልጉ በመግለጽ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ። በአገራቸው ጉዳይ ላይ በተለይም በዕርቅ ዙሪያ በርካታ ጽሁፎችን ሲያቀርቡና ሲንቀሳቀሱ የቆዩት ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ በኃላፊነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከአገራቸው ውጪም በኬንያ፣ በሞዛምቢክ፣ በስዊትዘርላንድና በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች በከፍተና ኃላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

 በተለይም በዎርልድ ቪዥን፣ በተባበሩት መንግሥታ፣ በዓለምአቀፍ አብያተክርስቲያናት ካውንስል፣ … የሰጡት የዓመታት አገልግሎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በአገር ውስጥና በውጪ አገራት የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉት ዶ/ር ተጋ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የዕርቅ፣ የሰላምና የፍትሕ ሒደት ውስጥ የተጫወቱት መጠነኛ ሚና በአገራቸው ተግባራዊ ሆኖ ለማየት የሚመኙና ለዚያም የሚቻላቸውን ጥረት ሁሉ ሲያደርጉ መቆየታቸው እስካሁን የሠሩት ሥራ ምስክር ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ዶ/ር ተጋ ለንዳዶ የአገር ውስጥና የውጭ ስድስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው የሚናገሩ ናቸው፡፡ ተጨማሪ ያንብቡ


ምንጭ፦ http://www.goolgule.com/reconciliation-the-way-out/

ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive