Jun 29, 2016

ፎረም 65፦ እርቅ፡ ይቅርታና ምህረት (ዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ)

የኢትዮጵያ የፓለቲካ ቅራኔ መፍትሄው ህዝባዊ አመፅም ሆነ ትጥቅ ትግል አይደለም የምንል ወገኖች የአገራዊ እርቅና መግባባትን መንገድ እንደ አበይት መፍትሄ እየጠቆምን ነው።

"ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ" እንደሚባለው ማለት ነው።

በዚህ ውይይት amnesty እና pardon በእርቅ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ቦታ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ከዶ/ር ጸጋዬ ረጋሳ አራርሳ ጋር እንዳሣለን።

[ማሳሰቢያ፦ ይህ ውይይት ምንኛውንም በመንግስት ሃላፊነት ላይ የነበረም ሆነ ያለን ሰው ወንጀለኛ ነው/ናት ብሎ አይፈርጅም፥ አልፈረጀምም። ውይይቱ ፅንሰ ሃሳባዊ ዳሰሳ ብቻ ነው። ወንጀለኛነት ሚወሰነው በፍርድ ቤት ነው።]






Jun 27, 2016

ፎረም 65፦ አቶ ነጌሳ ኦዶ (ኦፌኮ)

የፎረም 65 ዝግጅት እንግዳችን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አለማቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ሊቀመንበር አቶ ነጌሳ ኦዶ ነው። አቶ ነጌሳ ጋር ስለ ኦፌኮ እና ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገናል።








Jun 23, 2016

ፎረም 65፦ ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ (እንግዳ፦ ዶ/ር አባድር ኢብራሂም)

የኢትዮጵያ የፓለቲካ ቅራኔ መፍትሄው ህዝባዊ አመፅም ሆነ ትጥቅ ትግል አይደለም የምንል ወገኖች የአገራዊ እርቅና መግባባትን መንገድ እንደ አበይት መፍትሄ እየጠቆምን ነው።



"ለምጣዱ ሲባል አይጧ ትለፍ" እንደሚባለው ማለት ነው።



በዚህ ውይይት amnesty እና pardon በእርቅ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ቦታ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ከዶ/ር አብድር ጋር እንዳሣለን።



[ማሳሰቢያ፦ ይህ ውይይት ምንኛውንም በመንግስት ሃላፊነት ላይ የነበረም ሆነ ያለን ሰው ወንጀለኛ ነው/ናት ብሎ አይፈርጅም፥ አልፈረጀምም። ውይይቱ ፅንሰ ሃሳባዊ ዳሰሳ ብቻ ነው። ወንጀለኛነት ሚወሰነው በፍርድ ቤት ነው።]








Jun 16, 2016

ፎረም 65፦ ፓለቲካችን ከዚህ ወዴት?

ከኢሕአዴግ በስልጣን 25 አመታት መቆየትና የተቃዋሚዎች የ25 ዓመታት ውጤት አልባነት ስሜት ጋር ተደምሮ መሰረታዊ ጥያቅዎች እየተነሱ ነው። ጥያቄዎቹ ተቃዋሚው ራሱን ይፈትሽ፥ ቅደም ተከተሉን ይመርምር፥ ጉልበቱና ትኩረቱን በጥንቃቄ ይጠቀም የሚሉ ናቸው።



እነዚህን ጥያቄዎች ያነሱ ሁለት የፌስቡክ ተሳታፊዎችን ጋብዘናል። እንግዶቻችን ዶ/ር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ዶ/ር ደረጀ ገረፋ ቱሉ ከኢትዮጵያ ናቸው።








Jun 14, 2016

ፎረም 65፦ ሃርቤ እና ኮሮጆ

በፍረም 65 እንግዶቻችን በፓልቶክ ከተቃዋሚ ክፍሎች አንዱና ተዋደጃ የሆነው የ"ቃሌ ኢትዮጵያውያን መወያያ መድረክ" (Qale Ethiopian Discussion Forum 1) መደበኛ አወያይ ከሆኑት ከኮሮጆ ኢትዮጵያ እና ከሃርቤ ጋር ነው።



ውይይታችን በአጠቃላይ የፓለቶክን ሚና፡ የቃሌን የውይይት ትኩረቶች፡ እንዲሁም በአገራዊ መግባባት ላይ ፓልቶክ ሊያደርግ የሚችለውን ድርሻ ከእንግዶቻችንን ጋር እንወያያለን።








Jun 9, 2016

ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive