Oct 28, 2016

Oct 24, 2016

ፎረም 65፦ ኢትዮጵያዊነት

ባለፉት 25 ዓመታት ኢሕአዴግ በብሄር ማንነቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ችላ ብሏል የሚል ትችት በሰፊ ይሰማል። ፎረም 65 ኢትዮጵያዊነት ላይ ከሚያተኩሩ ስብስቦች ውስጥ ሁለት እንግዶች ጋብዘናል።



እንግዶቻችን ዶ/ር እርቁ ይመር "ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ" ሊቀመንበር ፤ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የ"አንድ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ" አስተባባሪ ናቸው።










Oct 15, 2016

ፎረም 65፦ ህወሓት፣ ትግራይና ዲያስፓራ

በዲያሥፓራ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን አስመልክቶ በተከታታይ ያወጧቸውን መግላጫዎችን በሚመለከት ከአቶ በየነ ገብራይ እና አቶ የማነ ምትኩ ጋር ቆይታ አድርገናል።



[ማስተካከያ፦ አቶ በየነ ገብራይ የኢሮብ ብሄር ናቸው። በቅጂው ላይ አቶ በየነን ትግራዋይ የሚለው ኢሮብ በሚለው ይስተካከል። ከይቅርታ ጋር!]












Oct 7, 2016

ፎረም 65፦ ሰላማዊ ትግል - ትርፍ ወይስ ኪሳራ?

የኢሬቻ በዓል ወቅት የብዙዎችን መሞትና መቁስል አስከትሎ የሰላማዊ ትግል አያዋጣንም የሚሉ እይታዎች እየተገለጹ ነው። "ሰላማዊ ትግል፦ ትርፍ ወይስ ኪሳራ?" በሚል ከአቶ አሰፋ ጫቦ፡ አቶ ፈቃደ ሸዋቀና እና አቶ ዳዊት ተሾመ ጋር ውይይት አድርገናል።








Oct 4, 2016

ፎረም 65፦ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት - አቶ ተክሌ ይሻው

በፎረም 65 ከአቶ ተክሌ ይሻው ጋር በዐማራ ሕዝብ ጥቅም፣ በዐማራ-ኦሮሞ አጋርነትና በዐማራነትና ኢትዮጵያዊነት ላይ አጭር ቆይታ አድርገናል። አቶ ተክሌ ይሻው የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሊቀመንበር ናቸው።



ስለድርጅቱ መረጃ ለማግኘት ድረገጹን ይጎብኙ፦ http://www.moreshwegenie.org/








ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive