በፎረም65 ሁለት ሳምንታት በፊት ሜይ 3፣ 2016 እ.አ.አ "በዲያስፓራ የትግራይ ጥላቻ አለን?" በሚል ርዕስ ተወያይተን ነበር። ውይይቱ በድረገፃችን www.65Percent.org ላይ ይገኛል። የውይይቱ ጉዳይ ላይ የትግራዋይ እይታም መደመጥ አለበት ብለን ስለምናምን ዛሬ ሁለት ትግራዋይ ወገኖቻችንን በፎረም65 ለውይይት ጋብዘናል። እንግዶቻችን አቶ ግደይ ዘራፅዮን ከኖርዌይ እና አቶ አብርሃም አሰፋ ከኢትዮጵያ ናቸው።

