Dec 27, 2017

ፎረም 65፦ የ2017 ዳሰሳ - የአመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ማን?

ፎረም 65 ለዲያስፓራው ማህበረሰባችን መልካም አዲስ አመት እየተመኘን ፡ በ2017 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እነ ማን ነበሩ? የፎረም 65ትን የ2017 ዳሰሳ ውይይት  ያድምጡ! [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/4ZCdse ያድምጡ። (መጠን፦ 6.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]
Dec 26, 2017

Dec 13, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 2) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

እንግዳችን ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻል በፎረም 65 ይተነትናል። [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/RNt1Yx ያድምጡ። (መጠን፦ 5.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]
Dec 7, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 1) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ የኢትዮጵያን ፓለቲካ ወቅታዊ ሁኔታዎች አስመልክቶ በጻፋቸው ተከታታይ ጽሁፎቹ የህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ ወደ ዴሞክራሲያዊነት እንዴት መሻገርና መዳበር እንደሚችል ተንትኗል። እንዲሁም ሰሞኑን በጻፈው ጽሁፍ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻልም አመላክቷል።

"መዳበርና መሻሻል የሚመጣው አሮጌውን በመታገል ሳይሆን አዲሱን በመገንባት" መሆኑን በፎረም 65 እንገነዘባለን። ከዚህ አንጻር ከዶ/ር ጸጋየ አራርሳ ጋር አገራችን ያለችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ በሰፊው ዳስሰናል።

ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/XmF7c8 ያድምጡ። (መጠን፦ 6.92 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]


Dec 2, 2017

ፎረም 65 | ሙጠኖ:- #MeToo #እኔንምገጥሞኛል

በሕይወት ተሞክሮ ላይ በሚያተኩረው በሙጠኖ (Muxannoo ) ዝግጅታችን #MeToo ወይንም #እኔንምገጥሞኛል የተሰኘውን የሴቶች የማህብራዊ ሚዲያ ዘመቻ ላይ እናተኩራለን። የ#እኔንምገጥሞኛል ዘመቻንና እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሚገጥማቸውንና የሚያልፉበትን ጾታዊ ትንኮሳ ፡ ጥቃትና ወከባ ላይ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን ሶልያና ሽመልስ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ወ/ሮ አስቴር አስከዶም ከስዊድን እንግዶቻችን ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/bZEqo4 ያድምጡ። (መጠን፦ 7.44 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]


Nov 15, 2017

ፎረም 65፦ የኃይል እርምጃ መዘዝና መፍትሄ (ከቀይ ሽብር እስከ ኦሮሞ ተቃውሞ) #Forum65 #Ethiopia

ኃይል እርምጃዎች በሚፈጥሩት ግድያ ፡ መቁሰል ፡ መታሰር የተነሳ የአገራችን ፓለቲካዊ ቅራኔ ፡ ተቃውሞና አለመግብባት ሲባባስ እንጂ ሲለዝብ አይታይም።

የኃይል እርምጃዎችን መዘዝ በምን መልኩ ፍትሃዊ መፍትሄ ማበጀት ይቻላል? እንግዶቻችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ፡ የአለማአቀፍ ሰብዓሚ መብት የህግ ባለሙያ ዶ/ር አባድር ኢብራሂም ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/ih7WQX ያድምጡ። (መጠን፦ 7.01 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]

Nov 9, 2017

ፎረም 65፦ የህወሓት የበላይነት አለን?

በማህበራዊ ሚዲያ በተደጋጋሚ ከሚነሱት ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ የህወሓት የበላይነት የለም ወይም አለ የሚለው ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሁለት ሳምነታት በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳባቸውን የገለፁ ሁለት ወገኖች በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን ጋዜጠኛ አቶ አናንያ ሶሪ ከኔዘርላንድ እና የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት ተመራማሪ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዩናይትድ ስቴትስ ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/ek926v ያድምጡ። (መጠን፦ 8.37 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]


Oct 28, 2017

ፎረም 65፦ ወቅታዊ ጉዳዮች እንግዳ አቶ አሉላ ሰለሞን #Ethiopia #Forum65

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተከሰቱን አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የዲያስፓራ ሚዲያዎች የተቃዋሚውን ዕይታዎች ሲያስተናግዱ ቆይተዋል። በአገራዊ ሁኔታዎች የሕወሃት ደጋፊዎችን ሃሳብ ለማስተናገድ በፎረም 65 የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት ተመራማሪ የሆነው አቶ አሉላ ሰለሞን ጋር ቆይታ አድርገናል።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/X39JxM ያድምጡ። (መጠን፦ 4.57 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]


Oct 18, 2017

ፎረም 65፦ ፓለቲካዊ ጉዳዮች ከፕሮፌሰር በየነ ጋር

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ 1. የማንነት ፓለቲካ ተፅዕኖ 2. የአማራ ድርጅት በመድረክ 3. የህብረብሄራዊ ልጆች ማንነት 4. 'ያ ትውልድና' የዛሬ ሚናው 5. የአገራዊ መግባባት አስፈላጊነት ላይ ሃሳባቸውን አጋርተውናል። ፕሮፌሰር በየነ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፤   የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንደንት መድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ግንኙነት ሃላፊ ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/yFMQaY ያድምጡ። (መጠን፦ 5.13 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]


Oct 11, 2017

ፎረም 65፦ የአባዱላ ውሳኔ ፋይዳ (significance) #Ethiopia #Forum65

የአቶ አባዱላን ውሳኔ አንዳንዶች እንደፋይዳ ቢስ ሲያዩት ሌሎች እንደ ወሳኝ ፣ ታሪካዊ ፣ የሃይል ሚዛንና የፓለቲካ አሰላለፍ ሽግሽግ አመልካች ውሳኔ አድርገው ገልጸውታል። የአቶ አባዱላ ከአፈጉባኤነት የመልቀቅ ውሳኔ ፋይዳው ምንድን ነው? እንግዶቻችን አቶ ግርማ ጉተማ እና አቶ ኃይለኢየሱስ አዳሙ ናቸው። [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/xJGVd2 ያድምጡ። (መጠን፦ 5.79 MB)] [✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]
Oct 6, 2017

ፎረም 65፦ ኢሬቻና የፕሬዘደንት ለማ መገርሳ አመራር

የኦሮሚያን ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘደንት አቶ ለማ መገርሳን አመራርና እንዲሁም ስለኢሬቻ 2010 ዓ.ም. ሃሳቡን እንዲያጋራን ዶ/ር ብርሃነመስቀል በፎረም 65 እንግዳችን ነው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/rnMS2j ያድምጡ። (መጠን፦ 5.14 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]
Sep 30, 2017

ፎረም 65፦ መሪው ማን ነው? ኢሕአዴግ ወይስ ህወሓት? #Ethiopia #Forum65

የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በኢትዮጵያ ፓለቲካ፣ ኢኮኖሚ፣ ደህንነትና መከላከያ ላይ ያላቸው የተጽዕኖና የስልጣን መጠን ሚዛናዊ ነው ወይንስ አይደለም? የህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ክብሩ የማን ነው? በ2009 ዓ.ም. የእሬቻ በዓል ስለሞቱት ወገኖቻችን ተጠያቂው ማን ነው? እንግዶቻችን አቶ እስራኤል ገደቡ እና አቶ ግርማ ካሳ ናቸው።
[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/7EoBEA ያድምጡ። (መጠን፦ 5.81 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]

Sep 23, 2017

ፎረም 65፦ የህብረብሄራዊ ቤተሰብ ልጆች ማንነት #Ethiopia #Forum65

በአገራችን የብሔሮችን መብት ለማስከበር በሚያደርገው የፓለቲካ ሂደት ውስጥ ሰፊ ትኩረት ያላገኘው የህብረብሄራዊ ቤተሰቦች የማንነት ጥያቄ፣ ጥቅምና ስጋት ነው። በተለይም ወላጆቻቸው ከተለያየ ብሔር የሆኑ ኢትዮጵያውያን ማንነታቸው ችላ የተባለ፣ የታፈነና የተገፋ እንደሆነ ይገልፃሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ሃሳቡን እንዲያካፍለን ከህብረብሄራዊ ቤተሰብ የተወለደው ጋዜጠኛ አቶ አናንያ ሶሪ እንግዳችን ነው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/YgWUp7 ያድምጡ። (መጠን፦ 4.03 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።][ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/YgWUp7 ያድምጡ። (መጠን፦ 4.03 MB)]

[✆ ☎ ☏ አስተያየት አለዎት፦ ይደውሉልን +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]

Sep 19, 2017

ፎረም 65፦ የአቶ ልደቱ ፋይዳ

አቶ ልደቱ በኢትዮጵያ ፓለቲካ አነጋጋሪ እና ትኩረት ሳቢ ፓለቲከኛ ቢሆኑም የቅንጅት አለመግባባት በአቶ ልደቱ ላይ ያደረሰውና እስካሁንም የሚያደርሰው አሉታዊ ድባብ ቀጥሏል። ይህ ለምን ሆነ? የአቶ ልደቱ ፓለቲካዊ ፋይዳ ምንድን ነው? አቶ ልደቱ ወደ ቀድሞው ፓለቲካዊ ሞገስና ተሰሞነታቸው እንዴት መመለስ ይችላሉ?

በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን ለመግለፅ  አቶ ሽመለስ በዛብህ በስዊትዘርላድ ነዋሪና የአውሮፓ፡ የአፍሪካና የአውስትሬልያ የቅንጂት ድጋፍ ሰጪ የቀድሞ ቃልአቀባይ የነበሩና  እንዲሁም ዶ/ር ብርሃኑ ለንጅሶ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ በፎረም 65 እንግዶቻችን ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/GW9kEJ ያድምጡ። (መጠን፦ 4.56 MB) ]Sep 18, 2017

ፎረም 65፦ ግጭት በኦሮሚያና በሶማሊ #Ethiopia #Forum65

በኦሮሚያና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ ከተሞችና መንደሮች የተፈጠረ ግጭት የብዙ ሰዎችን ህይወትን አጥፍቷ፤ በርካቶችን አፈናቅሏል።፡ የግጭቶቹ መንስዔ ምንድን ነው? ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ እንግዶች ከሁለቱ ክልሎች ተወላጆች ጋብዘናል።

እንግዶቻችን የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዶ/ር ኡስማኤል ቋዴህ እና የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ አቶ ግርማ ጉተማ ሲሆኑ ፡ በኦጋዴን አካባቢ ለረዢም አመታት የቆየውን አለመረጋጋት አስመልክቶ የአለማቀፋዊ ሰብዓዊ መብት የህግ ባለሙያ የሆነውን ዶ/ር አባድር ኢብራሂም አካባቢውን አስመልክቶ ትንታኔ እንዲሰጠን አብሮን ይገኛል። 


[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/caUyZR ያድምጡ። (መጠን፦ 6.51 MB) ]Sep 13, 2017

ፎረም 65፦ 2009 የትውልዳዊ ሽግግር ዓመት

2009 ዓ.ም. የትውልዳዊ ሽግግር ዓመት ነበር። በ2009 ዓመት ፎረም አገራዊ ትኩረት የሳቡ አበይት ጉዳዮችን እናስታውሳለን። እንዲሁም ከዚህ አለም በሞት የተለዩንን ትኩረት ሳቢ ግለሰቦች እንዘክራለን።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/BJ52Sdያድምጡ። (መጠን፦ 4.09 MB) ]


Sep 8, 2017

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግና ቅቡልነት (legitimacy)

ለአገራዊ መግባባት መዳበር የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሚና ወሳኝና ሰፊ ነው። ሆኖም ኢሕአዴግ የቅቡልነት (የእውቅና እና የተቀባይነት/legitimacy) ሰፊ ተግዳሮት አለበት።

- ኢሕአዴግ ቅቡልነት ለምን ጎደለው?

- የቅቡልነት ጉድለት መዘዙ ምን ነው?

- የኢሕአዴግ ቅቡልነት እንዴት ይጨምር?

- በቅቡልነት የተቀናቃኝ ኋይሎች ሚና ነው?

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ እንግዳችን ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/1EvB6D ያድምጡ። (መጠን፦ 6.82 MB) ]Aug 26, 2017

ፎረም 65፦ ቄሮ እና አድማ

ከቤት ያለመውጣት፣ የግብይትና ገበያ አድማ ውጤትና እንዲሁም የሀረማያ ቄሮ ያስተላለፉትና በኋላ ያስተባበሉት መግለጫ ላይ የተደረገ የፎረም 65 ውይይት።
Aug 21, 2017

Aug 11, 2017

ፎረም 65፦ አርቲስቶች ላይ አድማ በዲያስፓራ

አርቲስቶች ላይ በዲያስፓራ አድማ ማስመታትን በመቃወም ከሚጽፉ ወገኖች አንዱ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቶ ቢላል መስፍን ነው። የአድማ ቅስቀሳዎችን በሚመለከት ሃሳቡን እንዲያካፍለን አቶ ቢላል በፎረም 65 እንግዳችን ነው።[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/8W78Md ያድምጡ። (መጠን፦ 2.14 MB) ]


Aug 7, 2017

ፎረም 65፦ የዶ/ር መረራ እስር ፎቶ ፡ የአስቸኳይ አዋጅ መነሳት

የዶ/ር መረራ ጉዲና እስር ፎቶ ፣ እንዲሁም የአስቸኳይ አዋጁ መነሳት ላይ አጭር ውይይት ያድምጡ። መግባባትን እናውርስ።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/b2hnrK ያድምጡ። (መጠን፦ 3.49 MB) ]


Jul 30, 2017

ፎረም 65፦ ወቅታዊ ጉዳዮች (አቶ አብርሃ ደስታ እና አቶ አሉላ ሰለሞን)

ፎረም 65 ስለ ትግራይ-አማራ ክልል ሽማግሌዎች ውይይት በመቀሌ ፤ የግብር ውዝግብ እና በሙስና ተጠርጥረው ስለታሰሩት 42 ሰዎች ከአቶ አብርህ ደስታ የአረና ትግራይ ሊቀመንበርና አቶ አሉላ ሰለሞን የፓለቲካ አክቲቪስትና የሚዲያና የሲቪክ ሶሳይቲ ተመራማሪ ጋር ውይይት አድርገናል። [ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/aenufb ያድምጡ። (መጠን፦ 3.97 MB) ]
Jul 26, 2017

ሙጠኖ:- የሲያትል 2017 ተሞክሮ (ESFNA 2017)

በሕይወት ተሞክሮ ላይ በሚያተኩረው በሙጠኖ (Muxannoo ) መሰናዷችን የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ 34ኛው ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት በሲያትል ዋሽንግተን ከጁላይ 2 እስከ ጁላይ 8 2017 እአአ ዝግጅት ላይ የተገኙ ሁለት እንግዶች ቆይታቸውን አጋርተውናል። እንግዶቻችን አቶ ተክለሚካኤል አበበ ከካናዳ እና አቶ ኦርቾ ኤራ ከዩናትድ ስቴት ናቸው።


Jul 22, 2017

ፎረም 65፦ የጥላቻ መንስዔ ፣ መዘዝና መፍትሄ

የጥላቻ መንስዔው ፣ መዘዙና መፍትሄው ምን ነው? በዚህ ላይ ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒየን ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/FyHV9v ያድምጡ። (መጠን፦ 6.40 MB) ]


Jul 18, 2017

ፎረም 65፦ የኢንቨስትመንት ውዝግብ በዲያስፓራ

በዲያስፓራ በሚኖሩ የኢሕአዴግ ደጋፊ ወገኖቻችን መካከል "ኩራት ለኢትዮጵያ" ከተሰኘው ኢንቨስትመት ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን አለመግባባት በሚመለከት በፎረም 65 አቶ ሽመልስ በዛብህንና አቶ እስራኤል ገበደቡ እንግዶቻችን ናቸው።

የውዝግቡን መንሴ ፣ ኢንቨስትመንቱ ዛሬ ያለበትን ጉዳይ ፣ እና ሰሞኑን ከአንዳንድ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች የተሰነዘረባቸውን ትችትና ጥቃትም በሚመለከት እንግዶቻችን ሃሳባቸውን ያጋሩናል።

DISCLAIMER:

በዚህ ፕሮግራም ወይም ድረገጽ ላይ ሚገለጹት እይታዎችና አመለካከቶች የተሳታፊው/ደራሲው ናቸው። እይታዎቹና አመለካከቶቹ የፎረም 65/65Percent.org አቋም አይደሉም።

The views and opinions expressed on Forum 65 are those of the persons appearing on the program and do not necessarily reflect the views and opinions of Forum 65.
Jul 15, 2017

ሙጠኖ:- እናቶችና የኦቲዝም ተሞክሮ

ፎረም 65 በሕይወት ተሞክሮ ላይ ያተኮረውን ሙጠኖ (Muxannoo ) የተሰኘውን አዲስ መሰናዶ ይዘንላችሁ ቀርበናል። በዚህ ዝግጅታችን "እናቶችና የኦቲዝም ተሞክሮ" በሚል ሁለት እናቶችን ጋብዘናል።

እንግዶቻችን ወ/ሮ ራሄል አባይነህ ከኢትዮጵያ እና  ከዩናትድ ስቴትስ ናቸው። እነዚህ ሁለት እናቶች ኦቲስቲክ የሆኑ ልጆቻቸውን በሚመልከት ተሞክሯቸውን ያጋሩናል።

ስለ ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ድረገጻቸውን ይጎብኙ፦ http://www.nehemiah-autism.org

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/yvH4Tt ያድምጡ። (መጠን፦ 4.90 MB) ]
Jul 3, 2017

ፎረም 65፦ ከዶ/ር ቴዎድሮስ ምን ይጠብቃሉ?

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው ዛሬ ቅዳሜ ጁላይ 1 2017 እ.አ.አ ስራ ጀምረዋል። ኢትዮጵያውያን ከዶ/ር ቴዎድሮስ ምን ይጠብቃሉ? በፎረም 65 ከአቶ አሉላ ሰለሞንና ከአቶ መስፈን ፈይሳ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/Wxctmr ያድምጡ። (መጠን፦ 4.04 MB) ]


Jun 30, 2017

ፎረም 65፦ የመግባባት ፓለቲካ (አቶ ኦባንግ ሜቶ)

የአገራችን ፓለቲካ በአለመግባባት የተወጠረ ነው። መግባባትን ለመፍጠር ምን ማድረግ ያስፈልጋል? በጉዳዩ ላይ በፎረም 65 ከአቶ ኦባንግ ጋር ውይይት አድርገናል። አቶ ኦባንግ የአኢጋን (SMNE) ዋና ዳይሬክተር ናቸው።  www.solidaritymovement.org


[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/MkzmC6 ያድምጡ። (መጠን፦ 6.2MB) ]
Apr 22, 2017

ፎረም 65፦ የቴዲ አፍሮ ሚና

ባለፈው ሳምንት ቴዲ አፍሮ የለቀቀው "ኢትዮጵያ" የተሰኘው ነጠላ ዜማ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ትኩረት ስቦ ሲያወያይና ሲያወዘግበን ቆይቷል።

በፍረም 65 የቴዲ አፍሮን ሚና በሚምለከት ከአቶ ግርማ ጉተማ እና ከአቶ ግርማ ካሳ ጋር አጭር ውይይት እናደርጋለን።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/hPQdTh ያድምጡ። (መጠን፦ 7MB) ]

Apr 19, 2017

ፎረም 65፦ ክፍል 2 - የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ተግዳሮቶች

ክፍል 2 ከ 3 የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ተግዳሮቶች
እንግዶቻችን፦
- ወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ምክትል ሊቀመንበር ፤
- ዶ/ር አባድር ኢብራሂም - የአለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት የህግ ባለሙያ ፤
- አቶ ነጋሲ በየነና የፓለቲካ አክቲቪስት የጋሻ ለኢትዮጵያ ተወካይ ፤
- አቶ ኦርቾ ኤራ የፓለቲካ አክቲቪስት ፤
- አቶ አሉላ ሰለሞን - የፓለቲካ አክቲቪስትና የሚዲያና የሲቪክ ሶሳይቲ ላይ ያተኮረ ተመራማሪ ናቸውApr 14, 2017

Apr 11, 2017

ፎረም 65፦ ክፍል 1 - የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነቶች

የብሔር ኋይሎችና የአንድነት ሃይሎችን በሚመልከት የሚከተለውን የውይይት ቅንብር ይዘንላችሁ ቀርበናል።

የውይይት ቅንብሩ 1ኛ ከወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ ና ከዶ/ር አባድር ኢብራሂም መካከል ያደረግነውንና ፣ 2ኛ ከአቶ ነጋሲ በየነና ከአቶ ኦርቾ ኤራ ጋር ያደረግነውን ያካተተ ሲሆን ፡ በጉዳዩ ላይ የኢሕአዴግ ደጋፊዎችን አመለካከት ለማሳተፍ ቅንብሩ ከአቶ አሉላ ሰለሞን ጋር ያደርገነውን ውይይትም የያዘ ነው።

ክፍል 1 ከ 3 የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነቶች
ክፍል 2 ከ 3 የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ተግዳሮቶች
ክፍል 3 ከ 3 የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ውጤታማነት

የቅንብሩን ክፍል 1 ከ 3 እነሆ።

እንግዶቻችን፦

- ወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ምክትል ሊቀመንበር ፤

- ዶ/ር አባድር ኢብራሂም - የአለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት የህግ ባለሙያ ፤

- አቶ ነጋሲ በየነና የፓለቲካ አክቲቪስት የጋሻ ለኢትዮጵያ ተወካይ ፤

- አቶ ኦርቾ ኤራ የፓለቲካ አክቲቪስት ፤

- አቶ አሉላ ሰለሞን - የፓለቲካ አክቲቪስትና የሚዲያና የሲቪክ ሶሳይቲ ላይ ያተኮረ ተመራማሪ ናቸው።Mar 31, 2017

ፎረም 65፦ ለድርድር አደራዳሪ ያስፈልገዋልን?

በገዢው ፓርቲ መሪነት የሚካሄደው የቅድመ ድርድር ውይይት ወቅት ኢሕአዴግ ድርድሩ ገለልተኛ ሶስተኛ አካል አደራዳሪዎች እንደማይኖሩትና ተደራዳሪዎች በፈረቃ እንዲመሩት ወስኗል። ፎረም 65 የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑትን ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱን በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡን ጋብዘናቸዋል።
Mar 29, 2017

ፎረም 65፦ የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች (ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ እና ዶ/ር ብርሃኑ ለንጂሶ)

የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነት ምንድን ነው? የብሔር ኃይሎች ውስጥ ያሉት ልዩነቶችስ ምንድን ናቸው? እንግዳቻችን ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ እና ዶ/ር ብርሃኑ ለንጂሶ ናቸው። (ለድምጽ ጥራት ጉድለት ይቅርታ እንጠይቃለን)[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/jJLGpY ያድምጡ። (መጠን፦ 4MB) ]


Mar 20, 2017

ፎረም 65፦ የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች (አቶ ጀዋር መሐመድ)

የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነት ምንድን ነው? የብሔር ኃይሎች ውስጥ ያሉት ልዩነቶችስ ምንድን ናቸው? እንግዳችን አቶ ጀዋር መሐመድ ነው።[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/dPSQxR ያድምጡ። (መጠን፦ 3MB) ]
Mar 9, 2017

ፎረም 65፦ በድርድሩ የዲያስፓራ ሚና ምን ይሁን?

ኢሕአዴግና ሀገር አቀፍ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ድርድር ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ ነው። ዲያስፓራው በድርድሩ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መሳተፍ ወይም ተጽዕኖ ማድረግ አለበት ወይስ የለበትም? እንግዶች፦ አቶ እስራኤል ገደቡና አቶ ግርማ ካሳ።[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/cvqemF ያድምጡ። (መጠን፦ 8MB) ]
Mar 5, 2017

ፎረም 65፦ ከቅራኔ ወደ መግባባት ("የት ነበርሽ?")

ቅራኔ ምንድን ነው? ቅራኔ ለምን ይፈጠራል? እንዴት ይገለፃል? ቅራኔን ለመፍታት መነጋገር ጥቅሙ ምንድን ነው? በሚሉና በሌሎች ከቅራኔ ጋር የተያያዙ ነጥቦች ላይ ለመወያየት እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ  (Conflict Resolution Expert) ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው።

ዶ/ር ብርሃኑ በኦልድ ደሚኒየን ዩኒቨርሲቲ የፐብሊክ አድሚንስትሬሽን ፕሮፌሰር ሲሆኑ ፡ የ"መንግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/63AWIL ያድምጡ። (መጠን፦ 6MB) ]Feb 27, 2017

ፎረም 65፦ የብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች

በብሔር ኃይሎችና የአንድነት ኃይሎች ልዩነት ምንድን ነው? የብሔር ኃይሎች ውስጥ ያሉት ልዩነቶችስ ምንድን ናቸው? የፎረም 65 አጭር ውይይት። ያድምጡጥ![ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/7Ojd1T ያድምጡ። (መጠን፦ 3MB) ]Feb 14, 2017

ፎረም 65፦ የግንቦት 7 ሚና

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን ያድምጡ። (መጠን፦ 6MB) ]

አርበኞች ግንቦት 7ትን ወክለው አቶ ነዓምን ዘለቀ በአትላንታ ከተማ "የኢትዮጵያ ሃገራዊ ንቅንቄ" ስብሰባ ላይ ያድደጉት ንግግር የአርበኞች ግንቦት 7ትን የትግል ስልትና በድርጅቱ ዙሪያ በአጠቃላይ ሰሞኑን አነጋጋሪ ሆኗል።

ግንቦት 7 ከተመሰረተ 8 ዐመታት ሆኖታል። በአርበኞች ግንቦት 7 የፓለቲካ ሚና ላይ ለመወያዬት በዲያስፓራ የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ተሳትፎ ከሚያደርጉት ከአቶ ተክለሚካኤል አበበ፣ አቶ ሽመልስ በዛብህ እና ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል ጋር በፎረም 65 ውይይት አድርገናል።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/S31VPI ያድምጡ። (መጠን፦ 6MB) ]


Feb 10, 2017

ፎረም 65፦ የአዲስ አበባ ማንነት፣ ጥቅምና ፓለቲካ (ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ) #Ethiopia #Forum65

አነጋጋሪና አወዛጋቢ ከሆኑት የአገራችን የማንነት ፓለቲካ ጉዳዮች አንዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎቿ ማንነት፣ ጥቅምና ፓለቲካ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በፎረም 65 እንግዳችን ነው።
ፎረም 65፦ የአዲስ አበባ ማንነት፣ ጥቅምና ፓለቲካ (ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ)

አነጋጋሪና አወዛጋቢ ከሆኑት የአገራችን የማንነት ፓለቲካ ጉዳዮች አንዱ የአዲስ አበባ ነዋሪዎቿ ማንነት፣ ጥቅምና ፓለቲካ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ በፎረም 65 እንግዳችን ነው።Feb 3, 2017

ፎረም 65፦ የኢሕአዴግ የድርድር ጥሪ

ኢሕአዴግ ያለ ቅድመ ሁኔታዎች ድርድር ጠርቷል። በዚህ ጉዳይ ላይ ፎረም 65 ሰፊ ውይይት አዘጋጅቷል። ያድምጡት! እንግዶቻችን፦
1. ወ/ሮ ጽጌረዳ ሙሉጌታ - የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ
ምክትል ሊቀመንበር - www.EthioShengo.org
2. ወ/ት ሶልያና ሽመልስ -
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጄክት ስራ አስኪያጅ
- www.EHRP.org
3. ዶ/ር ኡስማኤል ቋዴህ -
የኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ሸንጎ ሊቀመንበር
- www.EthioSomali.com
4. አቶ ነጋሲ በየነ - የጋሻ ለኢትዮጵያ ተወካይ -
EthiopianGasha.org
5. አቶ ገረሱ ቱፋ - የፓለቲካ አክቲቪስት
- facebook.com/geresu.tufa
6. ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል
- የፓለቲካ አክቲቪስት

Jan 24, 2017

Jan 18, 2017

ፎረም 65፦ ዕርቀ ሰላም በኢትዮጵያ

ዕርቅ ምንድን ነው? በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዕርቀ ሰላም ላይ የሚመክርና የመፍትሔ ሃሳብ የሚያመነጭ ውይይት አድርጓል። ፎረም 65 በጉባኤው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተወያይቷል። ያድምጡት!Jan 9, 2017

ፎረም 65፦ የሕወሃት ጥልቅ ተሃድሶ

ህወሓት ካደረገው ግምገማ የተነሳ በድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱ እየተዘገበ ነው። በሕወሃት ጥልቅ ተሃድሶ ላይ ለመወያየት ሁለት ትግራዋይ ጋብዘናል። እንግዶቻችን አቶ ነጋሲ በየነ እና አቶ አሉላ ሰለሞን ናቸው። ያድምጡት! #Ethiopia #Forum65
ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive