May 11, 2016

ፎረም 65፦ የአቶ በቀለ ገርባ ክስ (እንግዳ ተሳታፊ፦ አቶ እሸቱ ሆማ) ክፍል 1

መንግስት በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የመሰረታቸው ክሶችን ምንድን ናቸው? አቶ በቀለ ገርባ ከዚህ በፊት 4 ዓመታት ታስረው ነበር። ያሁኑን ክስ ልዩ ሚያደርገው ነገር አለ?

ክስ የተመሰረተባቸው አቶ በቀለ ገርባና አቶ ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳና ሌሎች ዜጎች ጉዳይ ባጠቃላይ ስለመንግስት ባህሪ ምን ያመለክታል? ተከሳሽሾች ከኦሮሞነታቸው የተነሳ ብቻ ነው የታሰሩት ሚለው ትችት መሰረት አለውን? በተለይ አቶ ዮናታንን ከኦነግ ጋር የሚያገናኝ ክስ ተመስርቷል። አቶ ዮናታን ግን የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነው። ይሄንን እንዴት ታዩታላችሁ?

የዛሬው የፎረም65 ውይይት እንግዳ ተሳታፊያችን አቶ እሸቱ ሆማ አገራዊ ጉዳዮች ላይ በፌስቡክ በሰፊው ከሚሳተፉ ወገኖች አንዱ ነው። አቶ እሸቱ የህግ ባለሙያ ነው።






ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive