Sep 18, 2017

ፎረም 65፦ ግጭት በኦሮሚያና በሶማሊ #Ethiopia #Forum65

በኦሮሚያና ሶማሊ ክልሎች አዋሳኝ ከተሞችና መንደሮች የተፈጠረ ግጭት የብዙ ሰዎችን ህይወትን አጥፍቷ፤ በርካቶችን አፈናቅሏል።፡ የግጭቶቹ መንስዔ ምንድን ነው? ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ እንግዶች ከሁለቱ ክልሎች ተወላጆች ጋብዘናል።

እንግዶቻችን የሶማሌ ክልል ተወላጅ ዶ/ር ኡስማኤል ቋዴህ እና የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ አቶ ግርማ ጉተማ ሲሆኑ ፡ በኦጋዴን አካባቢ ለረዢም አመታት የቆየውን አለመረጋጋት አስመልክቶ የአለማቀፋዊ ሰብዓዊ መብት የህግ ባለሙያ የሆነውን ዶ/ር አባድር ኢብራሂም አካባቢውን አስመልክቶ ትንታኔ እንዲሰጠን አብሮን ይገኛል። 


[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/caUyZR ያድምጡ። (መጠን፦ 6.51 MB) ]







ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive