Sep 19, 2017

ፎረም 65፦ የአቶ ልደቱ ፋይዳ

አቶ ልደቱ በኢትዮጵያ ፓለቲካ አነጋጋሪ እና ትኩረት ሳቢ ፓለቲከኛ ቢሆኑም የቅንጅት አለመግባባት በአቶ ልደቱ ላይ ያደረሰውና እስካሁንም የሚያደርሰው አሉታዊ ድባብ ቀጥሏል። ይህ ለምን ሆነ? የአቶ ልደቱ ፓለቲካዊ ፋይዳ ምንድን ነው? አቶ ልደቱ ወደ ቀድሞው ፓለቲካዊ ሞገስና ተሰሞነታቸው እንዴት መመለስ ይችላሉ?

በጉዳዩ ላይ ሃሳባቸውን ለመግለፅ  አቶ ሽመለስ በዛብህ በስዊትዘርላድ ነዋሪና የአውሮፓ፡ የአፍሪካና የአውስትሬልያ የቅንጂት ድጋፍ ሰጪ የቀድሞ ቃልአቀባይ የነበሩና  እንዲሁም ዶ/ር ብርሃኑ ለንጅሶ የማህበራዊ ሳይንስ ተመራማሪ በፎረም 65 እንግዶቻችን ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/GW9kEJ ያድምጡ። (መጠን፦ 4.56 MB) ]



ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive