Mar 31, 2018

ፎረም 65፦ ከጠ/ሚ አብይ ምን ይጠበቃል? (አቶ ልደቱ ፣ አቶ አምዶም ፣ አቶ ገረሱ)

"ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ምን ይጠበቃል?" በሚል ሀሳብ ዙሪያ የተደረገ ውይይት። እንግዶቻችን የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መስራችና የምክርቤት አባል አቶ ልደቱ አያሌው ፡ አቶ አምዶም ገብረስላሴ የአረና ትግራይ ፓርቲ የህዝብግንኙነት ኃላፊ እና አቶ ገረሱ ቱፋ የፓለቲካ አክቲቪስት ናቸው።


Mar 29, 2018

ፎረም 65፦ የጠ/ሚ አብይ ተግዳሮቶች (ከዶ/ር ጸጋየ አራርሳ)

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምን ይጠበቃል? አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ምን አይነት ተግዳሮቶች ይጠብቋቸዋል? ከዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ጋር በሚከተሉት ነጥቦች ጭምር ተወያይተናል። ያድምጡ።

1 - አብይና የኦሕዴድ ቅቡልነት 
2 - መለስ ፣ ኃይለማርያም ፣ አብይ 
3 - አብይና የህወሓት ስጋት 
4 - ጠ/ሚ አብይ ምንን ያስቀድሙ?



Mar 13, 2018

ፎረም 65፦ አስቸኳይ አዋጁና አደጋው

የሞያሌው ፍጅት አስቸኳይ አዋጁ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ሊያስከትል የሚችለው አመጽና ግጭት ከፍተኛ የሀገራዊ አደጋ ምንጭ ነው። ከሞያሌው ፍጂት አንጻር ያሉን አማራጮች ምንድን ናቸው? ውይይቱን ያድምጡ! ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/baSLQ6 ያድምጡ። (መጠን፦ 3.43 MB) Telegram: https://t.me/forum65


Mar 1, 2018

Ethiopia: ፎረም 65፦ ኢትዮጵያ ወዴት? እንዴት? (እንግዳ አቶ ግርማ ሰይፉ)



ሀገራችን ላለችበትን የፓለቲካ ቀውስ የመፍትሄ አቅጣጫ ሃሳብ ያዘለ ጽሁፍ ካቀረቡ ወገኖች አንዱ የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራርና የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው።

አቶ ግርማ ሰይፉ "አገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰላም እንድትሸጋገር ለማድረግ የቀረበ የመነሻ ሐሳብ" በሚል ጽሁፋቸው (ጽሁፉን ለማንበብ ☞https://goo.gl/67HKsH ) መሰረታዊ የሆኑ የመነሻ ሐሳብ ነጥቦችን አንስተዋል። ባቀረቡት የመነሻ ሐሳብ ላይ ለመነጋገር በፎረም 65 እንግዳቸውን ናቸው።

ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive