Aug 10, 2018

ፎረም 65፦ ባለኮከብ ወይስ ልሙጥ? #Ethiopia #Forum65

የባንዲራ ፣ ወይም ሰንደቅ ኣላማ ጉዳይ ከሚያወዛግቡን አንዱ ነው። ይፋዊውን ባለኮከቡን ወይንስ ልሙጡን ባንዲራ ይደግፋሉ?

ሁለት እንግዶች ከአዲስ አበባ ጋብዘናል። እንግዶቻችን አቡበከር አለሙ (የቀድሞው የሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት መጣጥፍ አዘጋጅ) እና ይድነቃቸው ከበደ የፓለቲካ አክቪስት ናቸው።



Aug 6, 2018

ፎረም 65፦ የዐቢይ አሜሪካ ጉብኝት ግምገማ #Ethiopia #Forum65

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝት አጥጋቢ ነበርን? ምን አነሰ? ምንስ በዛ? ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ይዘትና ትኩረትስ? ዲያስፓራው ከዐቢይ ምን ጨበጠ? እንግዶቻችን ወ/ት ሶሊያና ፣ አቶ ተክለሚካኤል እና ዶ/ር ብርሃነመስቀል ናቸው። ያድምጡት!


Aug 1, 2018

Jul 20, 2018

ፎረም 65፦ መግባባት በኢትዮጵያ (ልዩ ዝግጅት)

መግባባት በኢትዮጵያ የአጋርነት ጉባዔ (ጁላይ 1፣ 2018 እአአ) መግለጫ ላይ የተድረገ ውይይት፡፡ ውይይቱ ስለ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነት ፣ የመብት ጥሰቶች አጣሪ ኮሚሽን እንዲቋቋም ፣ ወቅታዊ አደጋዎች ትኩረት እንዲያገኙ ፣ እንዲሁም «መደመርን» ስለማዳበርና የፓሊሲ ልማት ተቋም አስፈላጊነት ላይ ያተኩሯል፡፡


Jul 15, 2018

Jun 28, 2018

ፎረም 65፦ ሰብዓዊ መብቶች ለምን አልተከበሩም? #Ethiopia #Forum65

በህገ-መንግስት ውስጥ የተጎናጸፉ ሰብዓዊ መብቶችስ ለምን አልተከበሩም፣ እንዴትስ መከበር ይችላሉ? በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ሃሳቡን እንዲያጋራን እንግዳችን የሰብዓዊ መብት የህግ ባለሙያ ዶ/ር አባድር ኢብራሂም ነው። ዶ/ር አባድር የCenter for the Advancement of Human rights and Democracy in Ethiopia ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ የዕርቅና የርትዓዊ ፍትህ ምክርር ቤት አባል ነው።


Jun 27, 2018

ፎረም 65፦ የሰላምና ዕርቅ ጥሪ ከእምነት አባቶች #Ethiopia #Forum65

እንግዶቻችን ሼክ ካሊድ መሀመድ ኦመር የFirst Hijra Foundation ኢማም ፡ ከዋሽንግተን ዲሲ እና አባ ገብረኪዳን ከሚኒሶታ ደብረብርሃን ቅዱስ ኡራኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሴንት ፓል ሚኒሶታ ናቸው። 


Jun 26, 2018

Jun 25, 2018

ፎረም 65፦ የሰኔ 16 ድጋፍ ሰልፍና እንድምታው #Ethiopia #Forum65

ቅዳሜ ሰኔ 16 አዲስ አበባ ከተደርገው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ ሰፊ ተሳትፎ ከሚያደርጉት ከአቶ አሉላ ሰሎምን ከዩናይትድ ስቴትስ እና አቶ ዳንኤል ብርሃነ የ HornAffairs.com ዋና አዘጋጅ ከአዲስ አበባ በፎረም 65 ላይ ቀርበው ሰልፉን አስመልክቶ የተሰማቸውን ስሜትና እንዲሁም ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ እድል መስጠቱ ከሀገራዊ መግባባትና ወንድማማችነት አንጻር ጠቃሚ ሆኖ ስላገኘነው ጋብዘናቸዋል።


Jun 24, 2018

Jun 20, 2018

ፎረም 65፦ እስርና መዘዙ (ልዩ ዝግጅት)

መታሰር መዘዙ ምንድን ነው? ስነልቦናዊ ፣ አካላዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ቤተሰባዊና ማህበራዊ የኑሮ ላይ ምን አይነት መዘዝ ያስከትላል? የቀድሞ ታሳሪዎች ምን አይነት ፍትህ ይሻሉ? እንግዶቻችን ወ/ት ጫልቱ ታከለ ፣ አቶ ዮናታን ተስፋየና አቶ ነሲቡ ስብሃት ናቸው።



Jun 13, 2018

Jun 8, 2018

ፎረም 65፦ ዓብይ የዲያስፓራውን ፓለቲካ ያቃሉን? #Ethiopia #Forum65

አገር ውስጥ ያለውን የፓለቲካ ሂደትና የዲያስፓራውን ሚና በሚመለከት ከኢሕአዴግ ደጋፊዎች እንግዶቻችን ጋር ውይይት አዘጋጅተናል። እንግዶቻችን አቶ አሉላ ሰለሞንና አቶ እስራዔል ገደቡ ናቸው።


Jun 7, 2018

ፎረም 65፦ የዲያስፓራ ሚና በዘመነ ዓብይ #Ethiopia #Forum65

አገር ውስጥ ያለውን የፓለቲካ ሂደትና የዲያስፓራውን ሚና በሚመለከት ከተንፎካካሪው ጎራ እንግዶቻችን ጋር ውይይት አዘጋጅተናል። እንግዶቻችን አቶ ገረሱ ቱፋ ከኔዘርላንድ፣ ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል ከብሪታኒያ እና አቶ ግርማ ካሳ ከዩናይትድ ስቴትስ ናቸው።


Apr 15, 2018

ፎረም 65፦ ጠ/ሚ ዓብይና የኢትዮ-ሶማሊ ፓለቲካ #Ethiopia #Forum65 #PMAbiy



የጠቅላይ ሚኒስቴር ዓብይ አህመድ በኢትዮጵያ ሀገራዊ ፓለቲካና በሶማሊ ክልላዊ ፓለቲካ እንድምታ ምንድን ነው? ፎረም 65 ከኢትዮጵያ ሶማሌ ዶሞክራሲያዊ ሸንጎ አባል ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል። ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/R5zKUw ያድምጡ። (መጠን፦ 3.02 MB) Telegram: https://t.me/forum65

Apr 6, 2018

Apr 4, 2018

ቪኦኤ፦ ልጆቻቸው የተገደሉባቸው ወላጆች በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የይቅርታ መልዕክት ዙሪያ

VOA: አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በፓርላማ ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ሕወታቸው ለተቀጠፈ ሰዎች መፀፀታቸውን ገልፀው ይቅርታ ጠይቀዋል።

በቅርቡ ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው መካከልይቅርታ ብቻውን ለደማ ልብ መጠገኛ ሊሆን አይችልም ይቅርታው ተቀባይነት የሚኖረው ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው ብለዋል።

ቪኦኤ - ጽዮን ግርማ

[ ምንጭ፦ https://amharic.voanews.com/a/new-prime-minster-/4332592.html ]


Mar 31, 2018

ፎረም 65፦ ከጠ/ሚ አብይ ምን ይጠበቃል? (አቶ ልደቱ ፣ አቶ አምዶም ፣ አቶ ገረሱ)

"ከአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ምን ይጠበቃል?" በሚል ሀሳብ ዙሪያ የተደረገ ውይይት። እንግዶቻችን የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መስራችና የምክርቤት አባል አቶ ልደቱ አያሌው ፡ አቶ አምዶም ገብረስላሴ የአረና ትግራይ ፓርቲ የህዝብግንኙነት ኃላፊ እና አቶ ገረሱ ቱፋ የፓለቲካ አክቲቪስት ናቸው።


Mar 29, 2018

ፎረም 65፦ የጠ/ሚ አብይ ተግዳሮቶች (ከዶ/ር ጸጋየ አራርሳ)

ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ምን ይጠበቃል? አዲሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ምን አይነት ተግዳሮቶች ይጠብቋቸዋል? ከዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ ጋር በሚከተሉት ነጥቦች ጭምር ተወያይተናል። ያድምጡ።

1 - አብይና የኦሕዴድ ቅቡልነት 
2 - መለስ ፣ ኃይለማርያም ፣ አብይ 
3 - አብይና የህወሓት ስጋት 
4 - ጠ/ሚ አብይ ምንን ያስቀድሙ?



Mar 13, 2018

ፎረም 65፦ አስቸኳይ አዋጁና አደጋው

የሞያሌው ፍጅት አስቸኳይ አዋጁ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ ሊያስከትል የሚችለው አመጽና ግጭት ከፍተኛ የሀገራዊ አደጋ ምንጭ ነው። ከሞያሌው ፍጂት አንጻር ያሉን አማራጮች ምንድን ናቸው? ውይይቱን ያድምጡ! ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/baSLQ6 ያድምጡ። (መጠን፦ 3.43 MB) Telegram: https://t.me/forum65


Mar 1, 2018

Ethiopia: ፎረም 65፦ ኢትዮጵያ ወዴት? እንዴት? (እንግዳ አቶ ግርማ ሰይፉ)



ሀገራችን ላለችበትን የፓለቲካ ቀውስ የመፍትሄ አቅጣጫ ሃሳብ ያዘለ ጽሁፍ ካቀረቡ ወገኖች አንዱ የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አመራርና የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባል አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው።

አቶ ግርማ ሰይፉ "አገራችን ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሰላም እንድትሸጋገር ለማድረግ የቀረበ የመነሻ ሐሳብ" በሚል ጽሁፋቸው (ጽሁፉን ለማንበብ ☞https://goo.gl/67HKsH ) መሰረታዊ የሆኑ የመነሻ ሐሳብ ነጥቦችን አንስተዋል። ባቀረቡት የመነሻ ሐሳብ ላይ ለመነጋገር በፎረም 65 እንግዳቸውን ናቸው።

Feb 26, 2018

Ethiopia ፎረም 65፦ ከቀጣዩ ጠ/ሚ ምን ይጠበቃል? #Forum65 #Ethiopia

ሀገራዊ ፓለቲካዊ ቀውስ በኢትዮጵያ በተስፋፋበትና ዳግም አስቸኳይ አዋጅ በታወጀበት በአሁኑ ወቅት ፡ ከቀጣዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ምን ይጠበቃል? ውይይቱን ያድምጡ! ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/CNgBAq ያድምጡ። (መጠን፦ 3.62 MB) Telegram: https://t.me/forum65


Feb 19, 2018

ፎረም 65፦ ኢትዮጵያ ወዴት? እንዴት? (እንግዳ አቶ ልደቱ አያሌው)

ሀገራችን መሰረታዊ የለውጥ እድልና አጋጣሚ ወቅት ላይ ትገኛለች። የለውጥ አቅጣጫው ወዴት ነው? ወደ ለውጥ ግቡ እንዴት እንድረስ? ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር የሚከተሉትን ነጥቦች ዳስሰናል፦ 1. የአቶ ለማና ኦሕዴድ ፓለቲካ እንድምታው 2. የሀገራዊ መግባባት ኮሚሽን መመስረት አስፈላጊነት 3. በተቃዋሚው ውስጣዊ መግባባት እንዲፈጠር 4. የኢሕአዴግ መሪዎችና አባላት ዋስትና ጉዳይ።


[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/SjC1ws ያድምጡ። (መጠን፦ 7.99 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Feb 9, 2018

ፎረም 65፦ የዐማራ-ኦሮሞ አጋርነት በነገዋ ኢትዮጵያ

በተቃዋሚው ጎራ የሚገኙ ዐማራና ኦሮሞ ሊሂቃን ከጊዜያዊና ስልታዊ አጋርነት ወደ ዘላቂና ስትራቴጂክ አጋርነት ለመሸጋግር የኦሮሞ ሊሂቃን ከዐማራ ሊሂቃን ምን ይጠብቃሉ? የአለመግባባት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?  ከትናንቷ ፡ ከዛሬዋና ከመጪዋ ኢትዮጵያ አንጻር የአለመግባባት መንስኤዎችን ለመዳሰስና የመፍትሄ ሃሳባቸውን እንዲጠቁሙ ሁለት ኦሮሞ ወገኖች በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን ዶ/ር በያን አሶባ ከዩናይትድ ስቴትስ እና አክቲቪስት አቶ ገረሱ ቱፋ ከኔዘርላንድ ናቸው። ውይይቱን ያድምጡ!
[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/CsqaZJ ያድምጡ። (መጠን፦ 10.2 MB)]
[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Jan 26, 2018

ፎረም 65፦ ትውውቅ ከ"ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ" ጋር

ትውውቅ ከ"አንድ ሀገር! አንድ ሕዝብ! ኢትዮጵያችን ሕዝባዊ ንቅናቄ" ጋር። እንግዶች ሊቀመንበር አቶ ነሲቡ ስብሃት እና የንቅናቄው የፓለቲካና ፕሮፓጋንዳ ክፍል ሃላፊ አቶ ጸሃይ ደመቀ ናቸው። ለተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የንቅናቄውን ድረገጽ www.Ethiopiachen.org ይጎብኙ።



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/FfJ38b ያድምጡ። (መጠን፦ 6.77 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]


Jan 23, 2018

ፎረም 65፦ የመግባባት መኻል መንገድ

መንግስትም ተቃዋሚዎችም መኻል መንገድ ላይ መገናኘት እንዳለባቸው በቅርቡ የተፈቱት ዶ/ር መረራ ጉዲና አሳስበዋል። ተቃዋሚው የት ድረስ መሄድ አለበት? መንግስትስ?



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/xDA8gK ያድምጡ። (መጠን፦ 6.64 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]

Jan 11, 2018

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግ ተለውጧልን? #Ethiopia #Forum65

ኢሕአዴግ ተለውጧልን? የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ መግለጫና የአባል ድርጅቶች መሪዎች ቃለምልልስ ኢሕአዴግ መለወጡን አመልካች ነውን? እንግዶቻችን አቶ ግርማ ካሳ ከዩናይትድ ስቴትስ ፡ አቶ እስራኤል ገደቡ ከኔዘርላንድ ፡ ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል ከኢንግላንድ እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ከአውስትራሊያ ናቸው።



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/BTK4DM ያድምጡ። (መጠን፦ 8.79 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]










Jan 9, 2018

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግ ፡ ዕርቅና ሀገራዊ መግባባት

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ "የተሻለ ሀገራዊ መግባባትን" ለመፍጠር የሚወሰዱ እርምጃዎች እንደሚኖሩ ገልጿል። የሥራ አስፈጻሚው የእርምጃ ውሳኔዎች ከዕርቅና ሀገራዊ መግባባት አንጻር ፋይዳቸው ምንድን ነው?



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/AXVhNw ያድምጡ። (መጠን፦ 3.90 MB)]
[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]



ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive