Apr 30, 2019

65% እንቅስቃሴውን በስኬት አጠናቋል!

ክቡራትና ክቡራን፦ 65% ሲያራምድ የነበረው የዕርቅና ሀገራዊ መግባባት አጀንዳ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት ስላገኜ እንቅስቃሴውን በስኬት አጠናቋል። እናመሰግናለን። ያዬ አበበ መስራች Due to the Ethiopian government embracing the national reconciliation and consensus agenda, 65% has successfully completed its operations as of April 2019. Thank you for your support! Yaye Abebe Founder

Apr 4, 2019

ፎረም 65፦ ፓለቲካና የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት #Ethiopia #Forum65

አቶ ዮናስ ጎርፌ የሙዚቃና የፊልም ባለሙያና የ"ቤት ያጣው ቤተኛ፦ ሙዚቃ ሙዚቀኛና ኢትዮጵያዊቷ ቤተክርስትያን" መጽሀፍ ደራሲ ጋር «ፓለቲካና ኢትዮጵያዊያን ፕሮቴስታንት» በሚል ቃለምልልስ አዘጋጅተናል።



Mar 28, 2019

ፎረም 65፦ የዐቢይ አንድ ዓመት ከየት ወዴት? #ኢትዮጵያ #Ethiopia #Forum65

የጠ/ሚ ዐቢይን 12 ወራት በጥቅሉ ለመዳሰስ ሁለት እንጎዶቻችን በፎረም 65 ጋብዘናል፡፡ እንግዶቻችን አቶ ሽመልስ በዛብህ ስዊትዝርላንድ እና አቶ ደረጄ ደምሴ ጂማ ከዩናይትድ ስቴትስስ ናቸው፡፡




Mar 21, 2019

Mar 15, 2019

ፎረም 65፦ ወደ ትግራይነቴ «ተገፍቻለሁ» (ወ/ሮ ሳባ ወልደገብርኤል) #Ethiopia #Forum65

የሀገራችን ፓለቲካ በብሄር ግንኙነት ላይ ያለውን ተፅዕኖና መፍትሄውን በሚመለከት በዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ስቴት ነዋሪ የሆነቸው ወ/ሮ ሳባ ወልደገብርኤል ከራሷ ገጠመኝ አንጻር አካፍላናለች፡፡




Aug 10, 2018

ፎረም 65፦ ባለኮከብ ወይስ ልሙጥ? #Ethiopia #Forum65

የባንዲራ ፣ ወይም ሰንደቅ ኣላማ ጉዳይ ከሚያወዛግቡን አንዱ ነው። ይፋዊውን ባለኮከቡን ወይንስ ልሙጡን ባንዲራ ይደግፋሉ?

ሁለት እንግዶች ከአዲስ አበባ ጋብዘናል። እንግዶቻችን አቡበከር አለሙ (የቀድሞው የሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት መጣጥፍ አዘጋጅ) እና ይድነቃቸው ከበደ የፓለቲካ አክቪስት ናቸው።



Aug 6, 2018

ፎረም 65፦ የዐቢይ አሜሪካ ጉብኝት ግምገማ #Ethiopia #Forum65

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝት አጥጋቢ ነበርን? ምን አነሰ? ምንስ በዛ? ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ይዘትና ትኩረትስ? ዲያስፓራው ከዐቢይ ምን ጨበጠ? እንግዶቻችን ወ/ት ሶሊያና ፣ አቶ ተክለሚካኤል እና ዶ/ር ብርሃነመስቀል ናቸው። ያድምጡት!


Aug 1, 2018

Jul 20, 2018

ፎረም 65፦ መግባባት በኢትዮጵያ (ልዩ ዝግጅት)

መግባባት በኢትዮጵያ የአጋርነት ጉባዔ (ጁላይ 1፣ 2018 እአአ) መግለጫ ላይ የተድረገ ውይይት፡፡ ውይይቱ ስለ ሀገራዊ ምክክር አስፈላጊነት ፣ የመብት ጥሰቶች አጣሪ ኮሚሽን እንዲቋቋም ፣ ወቅታዊ አደጋዎች ትኩረት እንዲያገኙ ፣ እንዲሁም «መደመርን» ስለማዳበርና የፓሊሲ ልማት ተቋም አስፈላጊነት ላይ ያተኩሯል፡፡


Jul 15, 2018

ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive