Dec 27, 2017

ፎረም 65፦ የ2017 ዳሰሳ - የአመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ማን?

ፎረም 65 ለዲያስፓራው ማህበረሰባችን መልካም አዲስ አመት እየተመኘን ፡ በ2017 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እነ ማን ነበሩ? የፎረም 65ትን የ2017 ዳሰሳ ውይይት  ያድምጡ! [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/4ZCdse ያድምጡ። (መጠን፦ 6.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]




Dec 26, 2017

Dec 13, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 2) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

እንግዳችን ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻል በፎረም 65 ይተነትናል። [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/RNt1Yx ያድምጡ። (መጠን፦ 5.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]




Dec 7, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 1) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ የኢትዮጵያን ፓለቲካ ወቅታዊ ሁኔታዎች አስመልክቶ በጻፋቸው ተከታታይ ጽሁፎቹ የህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ ወደ ዴሞክራሲያዊነት እንዴት መሻገርና መዳበር እንደሚችል ተንትኗል። እንዲሁም ሰሞኑን በጻፈው ጽሁፍ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻልም አመላክቷል።

"መዳበርና መሻሻል የሚመጣው አሮጌውን በመታገል ሳይሆን አዲሱን በመገንባት" መሆኑን በፎረም 65 እንገነዘባለን። ከዚህ አንጻር ከዶ/ር ጸጋየ አራርሳ ጋር አገራችን ያለችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ በሰፊው ዳስሰናል።

ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/XmF7c8 ያድምጡ። (መጠን፦ 6.92 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]






Dec 2, 2017

ፎረም 65 | ሙጠኖ:- #MeToo #እኔንምገጥሞኛል

በሕይወት ተሞክሮ ላይ በሚያተኩረው በሙጠኖ (Muxannoo ) ዝግጅታችን #MeToo ወይንም #እኔንምገጥሞኛል የተሰኘውን የሴቶች የማህብራዊ ሚዲያ ዘመቻ ላይ እናተኩራለን። የ#እኔንምገጥሞኛል ዘመቻንና እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሚገጥማቸውንና የሚያልፉበትን ጾታዊ ትንኮሳ ፡ ጥቃትና ወከባ ላይ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን ሶልያና ሽመልስ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ወ/ሮ አስቴር አስከዶም ከስዊድን እንግዶቻችን ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/bZEqo4 ያድምጡ። (መጠን፦ 7.44 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]






ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive