Jul 30, 2017

ፎረም 65፦ ወቅታዊ ጉዳዮች (አቶ አብርሃ ደስታ እና አቶ አሉላ ሰለሞን)

ፎረም 65 ስለ ትግራይ-አማራ ክልል ሽማግሌዎች ውይይት በመቀሌ ፤ የግብር ውዝግብ እና በሙስና ተጠርጥረው ስለታሰሩት 42 ሰዎች ከአቶ አብርህ ደስታ የአረና ትግራይ ሊቀመንበርና አቶ አሉላ ሰለሞን የፓለቲካ አክቲቪስትና የሚዲያና የሲቪክ ሶሳይቲ ተመራማሪ ጋር ውይይት አድርገናል። [ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/aenufb ያድምጡ። (መጠን፦ 3.97 MB) ]
Jul 26, 2017

ሙጠኖ:- የሲያትል 2017 ተሞክሮ (ESFNA 2017)

በሕይወት ተሞክሮ ላይ በሚያተኩረው በሙጠኖ (Muxannoo ) መሰናዷችን የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ 34ኛው ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት በሲያትል ዋሽንግተን ከጁላይ 2 እስከ ጁላይ 8 2017 እአአ ዝግጅት ላይ የተገኙ ሁለት እንግዶች ቆይታቸውን አጋርተውናል። እንግዶቻችን አቶ ተክለሚካኤል አበበ ከካናዳ እና አቶ ኦርቾ ኤራ ከዩናትድ ስቴት ናቸው።


Jul 22, 2017

ፎረም 65፦ የጥላቻ መንስዔ ፣ መዘዝና መፍትሄ

የጥላቻ መንስዔው ፣ መዘዙና መፍትሄው ምን ነው? በዚህ ላይ ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒየን ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/FyHV9v ያድምጡ። (መጠን፦ 6.40 MB) ]


Jul 18, 2017

ፎረም 65፦ የኢንቨስትመንት ውዝግብ በዲያስፓራ

በዲያስፓራ በሚኖሩ የኢሕአዴግ ደጋፊ ወገኖቻችን መካከል "ኩራት ለኢትዮጵያ" ከተሰኘው ኢንቨስትመት ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን አለመግባባት በሚመለከት በፎረም 65 አቶ ሽመልስ በዛብህንና አቶ እስራኤል ገበደቡ እንግዶቻችን ናቸው።

የውዝግቡን መንሴ ፣ ኢንቨስትመንቱ ዛሬ ያለበትን ጉዳይ ፣ እና ሰሞኑን ከአንዳንድ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች የተሰነዘረባቸውን ትችትና ጥቃትም በሚመለከት እንግዶቻችን ሃሳባቸውን ያጋሩናል።

DISCLAIMER:

በዚህ ፕሮግራም ወይም ድረገጽ ላይ ሚገለጹት እይታዎችና አመለካከቶች የተሳታፊው/ደራሲው ናቸው። እይታዎቹና አመለካከቶቹ የፎረም 65/65Percent.org አቋም አይደሉም።

The views and opinions expressed on Forum 65 are those of the persons appearing on the program and do not necessarily reflect the views and opinions of Forum 65.
Jul 15, 2017

ሙጠኖ:- እናቶችና የኦቲዝም ተሞክሮ

ፎረም 65 በሕይወት ተሞክሮ ላይ ያተኮረውን ሙጠኖ (Muxannoo ) የተሰኘውን አዲስ መሰናዶ ይዘንላችሁ ቀርበናል። በዚህ ዝግጅታችን "እናቶችና የኦቲዝም ተሞክሮ" በሚል ሁለት እናቶችን ጋብዘናል።

እንግዶቻችን ወ/ሮ ራሄል አባይነህ ከኢትዮጵያ እና  ከዩናትድ ስቴትስ ናቸው። እነዚህ ሁለት እናቶች ኦቲስቲክ የሆኑ ልጆቻቸውን በሚመልከት ተሞክሯቸውን ያጋሩናል።

ስለ ነህሚያ የኦቲዝም ማዕከል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ድረገጻቸውን ይጎብኙ፦ http://www.nehemiah-autism.org

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/yvH4Tt ያድምጡ። (መጠን፦ 4.90 MB) ]
Jul 3, 2017

ፎረም 65፦ ከዶ/ር ቴዎድሮስ ምን ይጠብቃሉ?

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ሆነው ዛሬ ቅዳሜ ጁላይ 1 2017 እ.አ.አ ስራ ጀምረዋል። ኢትዮጵያውያን ከዶ/ር ቴዎድሮስ ምን ይጠብቃሉ? በፎረም 65 ከአቶ አሉላ ሰለሞንና ከአቶ መስፈን ፈይሳ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/Wxctmr ያድምጡ። (መጠን፦ 4.04 MB) ]


ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive