የዶሮ እርባታ አክሲዮን የፈጠረው ውዝግብ ለዱያስፓራ ፓለቲካዊ አለመግባባት ሌላ ማስረጃ ሆኖ ሰነባብቷል። አለመግባባት በዲያስፓራ አዲስ ክስተት አይደለም። ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ያጣነውን የሃሳብ መግለፅ ነፃነት በውጪ አገራት ስናገኝ ወደ መግባባት ሳይሆን ወደ አለመግባባት ፤ ወደ ትብብር ሳይሆን ወደ ክፍፍል ፤ ወደ ውጤታማነት ሳይሆን ወደ እንቅፋትነት የምናዘነብል ይመስላል ። ይህ ለምን ይሆናል?
በዛሬው የፎረም 65 ውይይት "አለመግባባት በዲያስፓራ" በሚል ርዕስ ውይይት እናደርጋለን። እንግዳ ተሳታፊያችን አቶ ግርማ ጉተማ ነው። አቶ ግርማ በፌስቡክና በት ዊተር በፓለቲካ ውይይቶች ላይ ሰፊ ተሳትፎ ከሚያደርጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው።
በዛሬው የፎረም 65 ውይይት "አለመግባባት በዲያስፓራ" በሚል ርዕስ ውይይት እናደርጋለን። እንግዳ ተሳታፊያችን አቶ ግርማ ጉተማ ነው። አቶ ግርማ በፌስቡክና በት ዊተር በፓለቲካ ውይይቶች ላይ ሰፊ ተሳትፎ ከሚያደርጉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አንዱ ነው።