Jan 11, 2018

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግ ተለውጧልን? #Ethiopia #Forum65

ኢሕአዴግ ተለውጧልን? የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ መግለጫና የአባል ድርጅቶች መሪዎች ቃለምልልስ ኢሕአዴግ መለወጡን አመልካች ነውን? እንግዶቻችን አቶ ግርማ ካሳ ከዩናይትድ ስቴትስ ፡ አቶ እስራኤል ገደቡ ከኔዘርላንድ ፡ ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል ከኢንግላንድ እና አቶ ተስፋዬ ኡርጌ ከአውስትራሊያ ናቸው።



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/BTK4DM ያድምጡ። (መጠን፦ 8.79 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ መልዕክት ይላኩልን።]










Jan 9, 2018

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግ ፡ ዕርቅና ሀገራዊ መግባባት

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ "የተሻለ ሀገራዊ መግባባትን" ለመፍጠር የሚወሰዱ እርምጃዎች እንደሚኖሩ ገልጿል። የሥራ አስፈጻሚው የእርምጃ ውሳኔዎች ከዕርቅና ሀገራዊ መግባባት አንጻር ፋይዳቸው ምንድን ነው?



[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/AXVhNw ያድምጡ። (መጠን፦ 3.90 MB)]
[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]



Dec 27, 2017

ፎረም 65፦ የ2017 ዳሰሳ - የአመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ማን?

ፎረም 65 ለዲያስፓራው ማህበረሰባችን መልካም አዲስ አመት እየተመኘን ፡ በ2017 ተጽዕኖ ፈጣሪዎች እነ ማን ነበሩ? የፎረም 65ትን የ2017 ዳሰሳ ውይይት  ያድምጡ! [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/4ZCdse ያድምጡ። (መጠን፦ 6.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]




Dec 26, 2017

Dec 13, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 2) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

እንግዳችን ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻል በፎረም 65 ይተነትናል። [ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/RNt1Yx ያድምጡ። (መጠን፦ 5.70 MB)] [✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]




Dec 7, 2017

ፎረም 65፦ (ክፍል 1) የፌደራል ስርዓት ሙከራ ፥ ኦሕዴድ/ብአዴንና የለውጥ አጋጣሚ

ዶ/ር ጸጋየ አራርሳ የኢትዮጵያን ፓለቲካ ወቅታዊ ሁኔታዎች አስመልክቶ በጻፋቸው ተከታታይ ጽሁፎቹ የህብረብሄራዊ ፌደራል ስርዓቱ ወደ ዴሞክራሲያዊነት እንዴት መሻገርና መዳበር እንደሚችል ተንትኗል። እንዲሁም ሰሞኑን በጻፈው ጽሁፍ በኦሕዴድና ብአዴን የተንጸባረቀውን ገጽታዊ ለውጥ እንዴት ወደ ጥልቅ ለውጥ /transformation/ ማምራት እንደሚቻልም አመላክቷል።

"መዳበርና መሻሻል የሚመጣው አሮጌውን በመታገል ሳይሆን አዲሱን በመገንባት" መሆኑን በፎረም 65 እንገነዘባለን። ከዚህ አንጻር ከዶ/ር ጸጋየ አራርሳ ጋር አገራችን ያለችበትን ፓለቲካዊ ሁኔታ በሰፊው ዳስሰናል።

ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/XmF7c8 ያድምጡ። (መጠን፦ 6.92 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]






Dec 2, 2017

ፎረም 65 | ሙጠኖ:- #MeToo #እኔንምገጥሞኛል

በሕይወት ተሞክሮ ላይ በሚያተኩረው በሙጠኖ (Muxannoo ) ዝግጅታችን #MeToo ወይንም #እኔንምገጥሞኛል የተሰኘውን የሴቶች የማህብራዊ ሚዲያ ዘመቻ ላይ እናተኩራለን። የ#እኔንምገጥሞኛል ዘመቻንና እንዲሁም ኢትዮጵያውያን ሴቶች የሚገጥማቸውንና የሚያልፉበትን ጾታዊ ትንኮሳ ፡ ጥቃትና ወከባ ላይ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን ሶልያና ሽመልስ ከዩናይትድ ስቴትስ እና ወ/ሮ አስቴር አስከዶም ከስዊድን እንግዶቻችን ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/bZEqo4 ያድምጡ። (መጠን፦ 7.44 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]






Nov 15, 2017

ፎረም 65፦ የኃይል እርምጃ መዘዝና መፍትሄ (ከቀይ ሽብር እስከ ኦሮሞ ተቃውሞ) #Forum65 #Ethiopia

ኃይል እርምጃዎች በሚፈጥሩት ግድያ ፡ መቁሰል ፡ መታሰር የተነሳ የአገራችን ፓለቲካዊ ቅራኔ ፡ ተቃውሞና አለመግብባት ሲባባስ እንጂ ሲለዝብ አይታይም።

የኃይል እርምጃዎችን መዘዝ በምን መልኩ ፍትሃዊ መፍትሄ ማበጀት ይቻላል? እንግዶቻችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ፡ የአለማአቀፍ ሰብዓሚ መብት የህግ ባለሙያ ዶ/ር አባድር ኢብራሂም ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/ih7WQX ያድምጡ። (መጠን፦ 7.01 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]





Nov 9, 2017

ፎረም 65፦ የህወሓት የበላይነት አለን?

በማህበራዊ ሚዲያ በተደጋጋሚ ከሚነሱት ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ የህወሓት የበላይነት የለም ወይም አለ የሚለው ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ባለፉት ሁለት ሳምነታት በማህበራዊ ሚዲያ ሃሳባቸውን የገለፁ ሁለት ወገኖች በፎረም 65 ጋብዘናል። እንግዶቻችን ጋዜጠኛ አቶ አናንያ ሶሪ ከኔዘርላንድ እና የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት ተመራማሪ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዩናይትድ ስቴትስ ናቸው።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/ek926v ያድምጡ። (መጠን፦ 8.37 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ Viber, WhatsApp, Telegram ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]






Oct 28, 2017

ፎረም 65፦ ወቅታዊ ጉዳዮች እንግዳ አቶ አሉላ ሰለሞን #Ethiopia #Forum65

ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተከሰቱን አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የዲያስፓራ ሚዲያዎች የተቃዋሚውን ዕይታዎች ሲያስተናግዱ ቆይተዋል። በአገራዊ ሁኔታዎች የሕወሃት ደጋፊዎችን ሃሳብ ለማስተናገድ በፎረም 65 የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት ተመራማሪ የሆነው አቶ አሉላ ሰለሞን ጋር ቆይታ አድርገናል።

[ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/X39JxM ያድምጡ። (መጠን፦ 4.57 MB)]

[✆ አስተያየት አለዎት? ይደውሉልን፦ +001-929-367-8665 ☎ በቫይበር እና ዋትስ አፕ ላይ አለን። ☏ በቀጥታም በስልክ ያገኙናል።]






ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive