Jan 24, 2017

Jan 18, 2017

ፎረም 65፦ ዕርቀ ሰላም በኢትዮጵያ

ዕርቅ ምንድን ነው? በአዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዕርቀ ሰላም ላይ የሚመክርና የመፍትሔ ሃሳብ የሚያመነጭ ውይይት አድርጓል። ፎረም 65 በጉባኤው ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ተወያይቷል። ያድምጡት!







Jan 9, 2017

ፎረም 65፦ የሕወሃት ጥልቅ ተሃድሶ

ህወሓት ካደረገው ግምገማ የተነሳ በድርጅቱ አመራሮችና ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱ እየተዘገበ ነው። በሕወሃት ጥልቅ ተሃድሶ ላይ ለመወያየት ሁለት ትግራዋይ ጋብዘናል። እንግዶቻችን አቶ ነጋሲ በየነ እና አቶ አሉላ ሰለሞን ናቸው። ያድምጡት! #Ethiopia #Forum65








Dec 19, 2016

ፎረም 65፦ ዋለልኝና የድህረ አብዮቱ ትውልድ ሚና (ክፍል 2)

የድህረ አብዮቱ ትውልድ ከተማሪው ንቅናቄ አረጋውያን ትውልድ አንጻር ሚናው ምንድን ነው?

እንግዶቻችን፦ አቶ ተክለሚካኤል አበበ ከካናዳ ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ለንጅሶ ከዩናይትድ ስቴትስ ፣ አቶ አሉላ ሰለሞን ከዩናይትድ ስቴትስ ፣ ዶ/ር ኢዮብ ገብረመስቀል ከእንግሊዝ አገር ናቸው።





Dec 11, 2016

ፎረም 65፦ ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ ፡ የኢትዮጵያ ሶማሌ ዶሞክራሲያዊ ሸንጎ ሊቀመንበር ( www.ethiosomali.com )

ፎረም 65 ከኢትዮጵያ ሶማሌ ዶሞክራሲያዊ ሸንጎ ሊቀመንበር ዶ/ር ኡስማኤል ቋዳህ ጋር ስለ ሶማሊ ፓለቲካና አጠቃላይ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገናል። ( www.ethiosomali.com )



Nov 1, 2016

ፎረም 65፦ ሽምግልና፣ ዕርቅና መግባባት

ለኢትዮጵያ የፓለቲካ ቅራኔ መፍትሄው እርቅና መግባባት መሆኑን ከሚጠቁሙና ከዚያ አልፈው የሽምግልናና የማግባባት ስራ ከሚሰሩ ስብስቦች አንዱ "መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ነው። ዛሬ ከመድረኩ ሁለት አባላት በፎረም 65 ጋብዘናል።

እንግዶቻችን የ"መግባባትን ገንቢ የኢትዮጵያውያን መድረክ" ሰብሳቢ ዶ/ር ብርሃኑ መንግስቱ እና የመድረኩ አባል ዶ/ር ገበየሁ እጂጉ ናቸው።





Oct 28, 2016

Oct 24, 2016

ፎረም 65፦ ኢትዮጵያዊነት

ባለፉት 25 ዓመታት ኢሕአዴግ በብሄር ማንነቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ኢትዮጵያዊነትን ችላ ብሏል የሚል ትችት በሰፊ ይሰማል። ፎረም 65 ኢትዮጵያዊነት ላይ ከሚያተኩሩ ስብስቦች ውስጥ ሁለት እንግዶች ጋብዘናል።



እንግዶቻችን ዶ/ር እርቁ ይመር "ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ" ሊቀመንበር ፤ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ የ"አንድ ኢትዮጵያ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ" አስተባባሪ ናቸው።










Oct 15, 2016

ፎረም 65፦ ህወሓት፣ ትግራይና ዲያስፓራ

በዲያሥፓራ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሕዝባዊ ተቃውሞዎችን አስመልክቶ በተከታታይ ያወጧቸውን መግላጫዎችን በሚመለከት ከአቶ በየነ ገብራይ እና አቶ የማነ ምትኩ ጋር ቆይታ አድርገናል።



[ማስተካከያ፦ አቶ በየነ ገብራይ የኢሮብ ብሄር ናቸው። በቅጂው ላይ አቶ በየነን ትግራዋይ የሚለው ኢሮብ በሚለው ይስተካከል። ከይቅርታ ጋር!]












Oct 7, 2016

ፎረም 65፦ ሰላማዊ ትግል - ትርፍ ወይስ ኪሳራ?

የኢሬቻ በዓል ወቅት የብዙዎችን መሞትና መቁስል አስከትሎ የሰላማዊ ትግል አያዋጣንም የሚሉ እይታዎች እየተገለጹ ነው። "ሰላማዊ ትግል፦ ትርፍ ወይስ ኪሳራ?" በሚል ከአቶ አሰፋ ጫቦ፡ አቶ ፈቃደ ሸዋቀና እና አቶ ዳዊት ተሾመ ጋር ውይይት አድርገናል።








ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive