Sep 13, 2017

ፎረም 65፦ 2009 የትውልዳዊ ሽግግር ዓመት

2009 ዓ.ም. የትውልዳዊ ሽግግር ዓመት ነበር። በ2009 ዓመት ፎረም አገራዊ ትኩረት የሳቡ አበይት ጉዳዮችን እናስታውሳለን። እንዲሁም ከዚህ አለም በሞት የተለዩንን ትኩረት ሳቢ ግለሰቦች እንዘክራለን።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/BJ52Sdያድምጡ። (መጠን፦ 4.09 MB) ]






Sep 8, 2017

ፎረም 65፦ ኢሕአዴግና ቅቡልነት (legitimacy)

ለአገራዊ መግባባት መዳበር የገዢው ፓርቲ ኢሕአዴግ ሚና ወሳኝና ሰፊ ነው። ሆኖም ኢሕአዴግ የቅቡልነት (የእውቅና እና የተቀባይነት/legitimacy) ሰፊ ተግዳሮት አለበት።

- ኢሕአዴግ ቅቡልነት ለምን ጎደለው?

- የቅቡልነት ጉድለት መዘዙ ምን ነው?

- የኢሕአዴግ ቅቡልነት እንዴት ይጨምር?

- በቅቡልነት የተቀናቃኝ ኋይሎች ሚና ነው?

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ትንታኔ እንዲሰጡን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ እንግዳችን ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/1EvB6D ያድምጡ። (መጠን፦ 6.82 MB) ]







Aug 26, 2017

ፎረም 65፦ ቄሮ እና አድማ

ከቤት ያለመውጣት፣ የግብይትና ገበያ አድማ ውጤትና እንዲሁም የሀረማያ ቄሮ ያስተላለፉትና በኋላ ያስተባበሉት መግለጫ ላይ የተደረገ የፎረም 65 ውይይት።








Aug 21, 2017

Aug 11, 2017

ፎረም 65፦ አርቲስቶች ላይ አድማ በዲያስፓራ

አርቲስቶች ላይ በዲያስፓራ አድማ ማስመታትን በመቃወም ከሚጽፉ ወገኖች አንዱ የግጥምና ዜማ ደራሲ አቶ ቢላል መስፍን ነው። የአድማ ቅስቀሳዎችን በሚመለከት ሃሳቡን እንዲያካፍለን አቶ ቢላል በፎረም 65 እንግዳችን ነው።



[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/8W78Md ያድምጡ። (መጠን፦ 2.14 MB) ]










Aug 7, 2017

ፎረም 65፦ የዶ/ር መረራ እስር ፎቶ ፡ የአስቸኳይ አዋጅ መነሳት

የዶ/ር መረራ ጉዲና እስር ፎቶ ፣ እንዲሁም የአስቸኳይ አዋጁ መነሳት ላይ አጭር ውይይት ያድምጡ። መግባባትን እናውርስ።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/b2hnrK ያድምጡ። (መጠን፦ 3.49 MB) ]






Jul 30, 2017

ፎረም 65፦ ወቅታዊ ጉዳዮች (አቶ አብርሃ ደስታ እና አቶ አሉላ ሰለሞን)

ፎረም 65 ስለ ትግራይ-አማራ ክልል ሽማግሌዎች ውይይት በመቀሌ ፤ የግብር ውዝግብ እና በሙስና ተጠርጥረው ስለታሰሩት 42 ሰዎች ከአቶ አብርህ ደስታ የአረና ትግራይ ሊቀመንበርና አቶ አሉላ ሰለሞን የፓለቲካ አክቲቪስትና የሚዲያና የሲቪክ ሶሳይቲ ተመራማሪ ጋር ውይይት አድርገናል። [ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/aenufb ያድምጡ። (መጠን፦ 3.97 MB) ]




Jul 26, 2017

ሙጠኖ:- የሲያትል 2017 ተሞክሮ (ESFNA 2017)

በሕይወት ተሞክሮ ላይ በሚያተኩረው በሙጠኖ (Muxannoo ) መሰናዷችን የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ 34ኛው ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት በሲያትል ዋሽንግተን ከጁላይ 2 እስከ ጁላይ 8 2017 እአአ ዝግጅት ላይ የተገኙ ሁለት እንግዶች ቆይታቸውን አጋርተውናል። እንግዶቻችን አቶ ተክለሚካኤል አበበ ከካናዳ እና አቶ ኦርቾ ኤራ ከዩናትድ ስቴት ናቸው።






Jul 22, 2017

ፎረም 65፦ የጥላቻ መንስዔ ፣ መዘዝና መፍትሄ

የጥላቻ መንስዔው ፣ መዘዙና መፍትሄው ምን ነው? በዚህ ላይ ሙያዊ ሃሳባቸውን እንዲያጋሩን እንግዳችን የቅራኔ አፈታት ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ መንግስቱ ናቸው። ፕሮፌሰር ብርሃኑ በኦልድ ዶሚኒየን ዩኒቨርስቲ መምህር ናቸው።

[ ከኢትዮጵያ በአነስተኛ ሜጋባይት ውይይቱን እዚህ https://goo.gl/FyHV9v ያድምጡ። (መጠን፦ 6.40 MB) ]






Jul 18, 2017

ፎረም 65፦ የኢንቨስትመንት ውዝግብ በዲያስፓራ

በዲያስፓራ በሚኖሩ የኢሕአዴግ ደጋፊ ወገኖቻችን መካከል "ኩራት ለኢትዮጵያ" ከተሰኘው ኢንቨስትመት ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን አለመግባባት በሚመለከት በፎረም 65 አቶ ሽመልስ በዛብህንና አቶ እስራኤል ገበደቡ እንግዶቻችን ናቸው።

የውዝግቡን መንሴ ፣ ኢንቨስትመንቱ ዛሬ ያለበትን ጉዳይ ፣ እና ሰሞኑን ከአንዳንድ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች የተሰነዘረባቸውን ትችትና ጥቃትም በሚመለከት እንግዶቻችን ሃሳባቸውን ያጋሩናል።

DISCLAIMER:

በዚህ ፕሮግራም ወይም ድረገጽ ላይ ሚገለጹት እይታዎችና አመለካከቶች የተሳታፊው/ደራሲው ናቸው። እይታዎቹና አመለካከቶቹ የፎረም 65/65Percent.org አቋም አይደሉም።

The views and opinions expressed on Forum 65 are those of the persons appearing on the program and do not necessarily reflect the views and opinions of Forum 65.




ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive