Jul 22, 2026

ከምክክሩ በኋላስ? በያዬ አበበ

ሀገራዊ ምክክሮች የማይሳኩት ከምክክር በፊት ፣ በምክክር ወቅት እና ከምክክር በኋላ በሚከሰቱ እንቅፋቶች ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ቅድመ ዝግጅት ሂደት አንፃራዊ ቅቡልነት አትርፏል። የተጀመረው ምክክርም እንደዛው እንደሚሆን ይጠበቃል።

የምክክሩ ውጤት አፈፃፀም ግን ሌላ ጉዳይ ነው።

የሀገራዊ ምክክሩ ውጤት ብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተ ጀምሮ ላለፉት ስድስት አመታት ካጋጠሙት ተግዳሮቶች ውስጥ አንዱ ትልቁ ውስጣዊ ፈተናው ይሆናል።

በፓርቲው ውስጥ በሚገኙት በሕብረ-ብሔራዊ (multi nationalists) እና በንዑስ-ብሔርተኛ (ethno nationalists) መካከል ለሚቀጥሉት ወሳኝ አሥርት ዓመታት ስለኢትዮጵያ ባላቸው የማይታረቅ የርዕይ ልዩነት የተነሳ ገዢው ፓርቲ የመከፋፈል አዝማሚያው ከፍተኛ ነው።

​የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ሰሞኑን ‘የኦሮሚያ ክልል እንዳይኖር የሚፈልጉ አሉ’ ማለታቸው ሚጠቁመው የፓርቲው ልዩ ልዩ አንጃዎች ከሀገራዊ ምክክሩ የሚጠብቁት ውጤት እንዳለና ፡ በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ የምክክሩ ውጤት ሚፈጥረውን ውስጣዊ ክፍፍል ነው።


​የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ግጭቶች ባለፉት 8 ዓመታት መቋጫ አላገኙም። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ውክልና (mandate) ባልሰጣቸው የራሳቸው የትርፍ ጊዜ ፕሮጀክቶች (pet projects) ላይ ባተኮሩበት ወቅት ከድህነት ወለል በታች የሆኑ ዜጎች ቁጥር እጂግ ጨምሯል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣን የማያከብር—የግል ፕሮጀክቶቹን የገንዘብ ምንጭ ለመግለጽ ፈቃደኛ ያልሆነ—አቅም የሌለው እና ርዕዮተ-ዓለማዊ ብስለት የጎደለው ጠቅላይ ሚኒስትር ባለበት ሁኔታ፣ ለ8 ዓመታት የሰነበቱት የአገር ውስጥ አለመረጋጋቶች ላይ የተከፋፈለ ገዢ ፓርቲ ጋር ሲጨመርበት የሀገሪቱ ቀውስ ይበልጥ እየተባባሰ ይሄዳል።

​እንዲህ ዓይነቱ ሀገርዊ ቀውስ ባለሃብቶች ውስጥ ስጋትን ይጨምራል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ የኑሮ ውድነት መከራ ያባብሳል፣ ይህም ውሎ አድሮ ወደ ሁከትና ተቃውሞ ያመራል።

​ባለፉት 8 ዓመታት በአብዛኛው የከሸፈው፣ መርህ አልባ እና ርዕዮት የለሹ የአብይ አመራር ላይ አሁን ያለው ተለዋዋጭ የምስራቅ አፍሪካ፡ የመካከለኛው ምስራቅ እና የዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲላዊ አለመረጋጋት ሲጨመሩበት ለኢትዮጵያ ሕልውና ትልቅ ፈተና ሆኗል።

​እርግጥ ነው ለሀገራዊ መግባባት ስንሟገት ለቆየነው ወገኖች ምክክሩ መልካም ምዕራፍ ነው። ሀገራዊ ምክክሩ የኢፌዲሪ ሕገ-መንግሥት ያለበትን የቅቡልነት ማነስ ለመገንባት የሚያስችል አቅም ያለው ከመሆኑ ባሻገር ለአገሪቱ ሰፊ የወጣት ማኅበረሰብ የውይይት እና የመግባባት ባህልን ለማዳበር አዎንታዊ እርምጃ ነው።

​ነገር ግን የሀገራዊ ምክክሩ ውጤት በገዢው ፓርቲ ላይ ስለሚኖረው አንድምታ በጥንቃቄ አርቆ ሳያስቡ፣ እንዲሁም አቅም እና ርዕዮታዊ ብስለት የሌለውን የገዢውን ፓርቲ መሪ ሳይቀይሩ ኢትዮጵያ የሀገራዊ ምክክሩን ፍሬ አታጭድም፣ ይልቁንም ወደ ተባባሰ ሁከት ትገባለች።

የሌሎች ሀገራት የምክክር ተሞክሮ እንደሚያሳየው ቅድመ-ምክክር ዝግጅት እና የምክክር ክንዋኔዎች ብቻ ሳይሆኑ ድህረ ምክክር አፈፃፀምም ለምክክር ውጤታማነት ወሳኝ ነው። ዛሬ ባለው የአቢይ ደካማ አመራር በፈጠረው ሀገራዊ ቀውስ አውድ ውስጥ የምክክሩ ውጤትን ለመተግበር ማሰብ ከንቱ ድካም ነው።

Aug 28, 2025

Apr 30, 2019

65% እንቅስቃሴውን በስኬት አጠናቋል!

ክቡራትና ክቡራን፦ 65% ሲያራምድ የነበረው የዕርቅና ሀገራዊ መግባባት አጀንዳ በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት ስላገኜ እንቅስቃሴውን በስኬት አጠናቋል። እናመሰግናለን። ያዬ አበበ መስራች Due to the Ethiopian government embracing the national reconciliation and consensus agenda, 65% has successfully completed its operations as of April 2019. Thank you for your support! Yaye Abebe Founder

Apr 4, 2019

ፎረም 65፦ ፓለቲካና የኢትዮጵያ ፕሮቴስታንት #Ethiopia #Forum65

አቶ ዮናስ ጎርፌ የሙዚቃና የፊልም ባለሙያና የ"ቤት ያጣው ቤተኛ፦ ሙዚቃ ሙዚቀኛና ኢትዮጵያዊቷ ቤተክርስትያን" መጽሀፍ ደራሲ ጋር «ፓለቲካና ኢትዮጵያዊያን ፕሮቴስታንት» በሚል ቃለምልልስ አዘጋጅተናል።



Mar 28, 2019

ፎረም 65፦ የዐቢይ አንድ ዓመት ከየት ወዴት? #ኢትዮጵያ #Ethiopia #Forum65

የጠ/ሚ ዐቢይን 12 ወራት በጥቅሉ ለመዳሰስ ሁለት እንጎዶቻችን በፎረም 65 ጋብዘናል፡፡ እንግዶቻችን አቶ ሽመልስ በዛብህ ስዊትዝርላንድ እና አቶ ደረጄ ደምሴ ጂማ ከዩናይትድ ስቴትስስ ናቸው፡፡




Mar 21, 2019

Mar 15, 2019

ፎረም 65፦ ወደ ትግራይነቴ «ተገፍቻለሁ» (ወ/ሮ ሳባ ወልደገብርኤል) #Ethiopia #Forum65

የሀገራችን ፓለቲካ በብሄር ግንኙነት ላይ ያለውን ተፅዕኖና መፍትሄውን በሚመለከት በዩናይትድ ስቴትስ ኮሎራዶ ስቴት ነዋሪ የሆነቸው ወ/ሮ ሳባ ወልደገብርኤል ከራሷ ገጠመኝ አንጻር አካፍላናለች፡፡




Aug 10, 2018

ፎረም 65፦ ባለኮከብ ወይስ ልሙጥ? #Ethiopia #Forum65

የባንዲራ ፣ ወይም ሰንደቅ ኣላማ ጉዳይ ከሚያወዛግቡን አንዱ ነው። ይፋዊውን ባለኮከቡን ወይንስ ልሙጡን ባንዲራ ይደግፋሉ?

ሁለት እንግዶች ከአዲስ አበባ ጋብዘናል። እንግዶቻችን አቡበከር አለሙ (የቀድሞው የሙስሊሞች ጉዳይ መፅሄት መጣጥፍ አዘጋጅ) እና ይድነቃቸው ከበደ የፓለቲካ አክቪስት ናቸው።



Aug 6, 2018

ፎረም 65፦ የዐቢይ አሜሪካ ጉብኝት ግምገማ #Ethiopia #Forum65

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጉብኝት አጥጋቢ ነበርን? ምን አነሰ? ምንስ በዛ? ያስተላለፏቸው መልዕክቶች ይዘትና ትኩረትስ? ዲያስፓራው ከዐቢይ ምን ጨበጠ? እንግዶቻችን ወ/ት ሶሊያና ፣ አቶ ተክለሚካኤል እና ዶ/ር ብርሃነመስቀል ናቸው። ያድምጡት!


Aug 1, 2018

ተልዕኳችን | Our Mission

“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።

What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.

Post Archive