የሚከተለው ውጤት ድህረ ገፆች ላይ ከወጡት ፅሁፎቼ ሊንክ በማድረግ በ www.myEthiopia.com ድህረ ገፅ ላይ
የተሰበሰበ የዳሰሳ ጥናት ነው። ጥናቱ ሳይንሳዊ ያልሆነ ቢሆንም ለመንደርደሪያ ጥናትና አሳብ ሊረዳ ይችል ይሆናል
ብዬ አስባለው። ይህ ማለት ስለ እርቅና መግባባት ውስብስብ ጥያቄ እልባት ለማግኘት አይደለም። ያ በእኔ አይሞከርም
ከአቅሜ በላይ ነውና። ዓላማዬ ስለ እርቅ ቅድመ ሁኔታዎች መንደርደሪያ አሳብ ለመሰብሰብ በማሰብ ነው። እነሆ ድምፅ
የሰጡትን ሰዎች አሳቦች አጠርና ጠቅለል አድርጌ ከዚህ በታች በጥሬው አቅርቤያለው። የራሴን ትንታኔ ትቸዋለሁ። ያንን
ለአንባቢው እተዋለሁ። በዚህ ዳሰሳ ጥናት ላይ የተሳተፉትን ከልብ አመሰግናለው። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ።
ፍቅርም ይስጠን። –—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]——
Oct 11, 2014
Aug 6, 2014
ብሔራዊ መግባባት ወይስ አገራዊ ውድመት? በያዕቆብ ኃይለማርያም ዶ/ር
Posted on August 06, 2014
![]() |
| ያዕቆብ ኃይለማርያም ዶ/ር |
ጥላቻና ገደብ የለሽ
የአገር ሀብት ዝርፊያ በተለይም የዘር ጥላቻና ዘረኝነት በሩዋንዳ ያስከተለውን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ዘግናኝ
እልቂትና ጭካኔን ያየና፤ የእነዚያ አክራሪ የሁቱ ጐሣ አባላትና መሪዎቻቸውን ሰይጣናዊ ድርጊቶች በፍርድ ቤት ከስሶ
ሁኔታውን በዝርዝርና በጥልቀት የተረዳ ኢትዮጵያዊ፤ የዘርና የጐሣ ጥላቻ ያስከተለውን እልቂትና የአገር ውድመት
በአገሩ ላይ እንዳይከሰት፣ ምንም ቢያስከፍልም ሆነ ምናልባትም የቁራ ጩኸት ቢሆን እንኳን ‹‹ውርድ ከራሴ›› በማለት
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው በሚችልበት ቋንቋ በግልጽ የማስረዳት ኃላፊነት አለበት፡፡ በሩዋንዳ ከሰላሳ ዓመታት
በላይ ሲያመረቅዝ የቀዬው የዘር ጥላቻ ወደ እልቂት ሊያመራ እንደሚችል ገና ከጠዋቱ ያስጠነቀቁ ምሁራን ከፋፋይ ሽብር
ነዢዎች ተብለው እንደተፈረጁ ሁሉ፤ አሁንም ይህ ማስጠንቀቂያ ተመሳሳይ ዘለፋ ያስከትል ይሆናል፡፡ ዋናው ነገር ግን
በአገራችን ላይ እያንዣበበ ያለውን አደጋ ሕዝብና መንግሥት ይረዱት እንጂ፣ ሌላው ሁሉ ገብስ ነው፡፡
የዘር ጥላቻንና የጐሣ ግጭቶችን በጠቅላላው ጐሰኛነትንና ጐጠኛነትን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ድሮ ልናልፋቸው በተገባ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እኮ፣ ከብዙ አገራት ቀድማ አገራዊ አንድነትና ሉዐላዊነት የተጐናጸፈች፣ ጥልቅ ታሪክና የራስዋ ፊደልና የዳበረ ባህል ያላት አገር ነች፡፡ ሕዝቡም ለብዙ ምዕተ ዓመታት ክፉውንና ደጉን እየተጋራ በነፃነት የኖረ ሲሆን፤ ትናንት የተፈጠሩ አገራት ዘረኝነትንና ጐጠኝነትን አልፈው ሄደው አገራዊ አንድነት ሲፈጥሩ፣ እኛ በብሔረሰቦች መብት ስም እንዴት በዘረኝነት ውስጥ እንደነጋገራለን? ኢሕአዴግ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በመታወቂያ ካርድ እየለየ በጐሣ ወይንም በብሔር ከረጢት ውስጥ እንዲገባ ከመደንገጉ በፊት፣ ይህንን ዛሬ የተንሰራፋውን ጐሰኝነት ልናልፈው ተቃርበን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በሩዋንዳ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ቀላል ካደረጉት ነገሮች አንዱ፣ ሕዝቡ በነቂስ ዘሩን ወይንም ብሔሩን የሚያመላክት መታወቂያ አውጥቶ እንዲይዝ መደረጉ ነበር፡፡
በኢትዮጵያም ይህ አላስፈላጊ የሆነ ዝርዝር ሁኔታ፣ ማለትም ብሔረሰብ በመታወቂያ ካርድ ላይ እንዲጠቀስ የመደረጉ ጥቅም ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ጐሰኝነትንና ጐጠኝነትን ልናልፋቸው ተቃርበን እንደነበረ ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሰላሳ ዓመታት በፊት ዩኒቨርስቲ አካባቢ፣ አንድ ሰው ከኢትዮጵያዊነቱ ውጭ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤ ጉራጌ ይሁን ከምባታ አይታወቅም ነበር፡፡ ቢታወቅም በጓደኛ አመራረጥ ላይ የብሔር ማንነት ምንም ተጽእኖ እንዳልነበረው በዩኒቨርስቲው ያለፉ ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ በጊዜው የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኢዲዩ፣ ኢሠፓ፣ ወዘተ ሕብረ ብሔራዊ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ ከሕወሓትና ከኦነግ ውጭ ጐሰኝነትን መሰረት ያደረገ ፓርቲ አልነበረም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊቀበሉት የሚገባ አንድ ሐቅ ግን አለ፡፡
የዘር ጥላቻ የሰውን ሕሊና ከሚሰውሩ፣ የሰው ልጅ የመጨረሻ አውሬነት አፍጥጦ እንዲወጣ ከሚያደርጉ ክፉ ድርጊቶች አንዱ ነው፡፡ የዘር ጥላቻ ተደጋግሞ እንደታየው በዘር ማጥፋት ይደመደማል፡፡ ቦስኒያ ውስጥ ሰርብ ያልሆኑት ዜጐችን መጨፍጨፍ፣ ኦቶማኖች በአርመኖች ላይ ያደርሱት እልቂት፣ የጀርመን ናዚዎች በይሁዲዎች ላይ የፈጸሙት ግድያና ስቃይ፣ ሳዳም ሁሴን በኩርዶች ላይ ያካሄደው የዘር ምንጠራ፣ ፖል ፖት ያካሄደው ገደብ የለሽ ጭፍጭፋ፣ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ የፈፀሙት እልቂት፤ በዘር ጥላቻ ላይ ተመስርተው ከተፈፀሙ ግድያዎችና ሰቆቃዎች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ አሳዛኙ ነገር ዘረኛነት ከመሰረተው ስርዓት ተጠቃሚ ያልሆኑ የዚያ ዘር አባላትንም ለብቀላውና ለጥቃቱ ሰለባ ማድረጉ ነው፡፡
የዘር ጥላቻ ከወለዳቸው ዕልቂቶች መሀከል፣ እንስሳት እንኳን ሊፈጽሙት ከማይችሉት የጭካኔ ተግባራት የሚቆጠረው የሩዋንዳው የቱትሲዎች እልቂት ቀዳሚነቱን ሳይዝ አይቀርም፡፡ ሩዋንዳ የቤልጅየም ቅኝ ግዛት በነበረችበት ጊዜ፤ ቅኝ ገዢዎቹ አፍንጫ ሰልካካና ቁመተ ረጃጅምና ከኢትዮጵያ ፈልሰው እንደሄዱ የሚነገርላቸውን ከሕዝቡ 15% የሚሆኑትን ቱትሲዎች ወኪል በማድረግ፣ 85% በሆኑት መደበኛ አፍሪካዊ መልክ ባላቸው ሁቱዎች ላይ አነገሷቸው፡፡ የቱትሲዎችና የኢትዮጵያ ግንኙነት ከተነሳ፤ ከሃያ ሺህ በላይ ቱትሲዎች እግርና እጃቸውን ታስረው ወደአገራችሁ ኢትዮጵያ ግቡ ተብለው ወደሰሜን ከሚፈስ ቪክቶሪያ ኃይቅ ጋር ከሚቀላቀል ወንዝ ውስጥ መጨመራቸው ይታወቃል፡፡ ሥልጣን በመጠቀም የመንግሥቱን ቢሮክራሲ፣ ንግዱን፣ ትምህርቱን፣ የከብት እርባታውን በመጠቅለል ሁቱዎችን መብት አልባ ዜጐች አደረጓቸው፡፡
ቂም ቋጥረው የኖሩት ሁቱዎች፣ እ.ኤ.አ. በ1962 ዓ.ም. ሩዋንዳ ነፃ ስትወጣ የመንግሥቱን ሥልጣንና መዋቅራት፣ ቢሮክራሲውን፣ የትምህርቱና የንግድ ዘርፎችን በሙሉ ከመጠቅለል አልፈው፤ በቱትሲዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ቤት ንብረታቸውን ንግዳቸውን የተዘረፉት፣ ከቢሮክራሲው የተባረሩት ቱትሲዎች ደግሞ ወደኡጋንዳ ተሰደዱ፡፡ ወደኡጋንዳ የተሰደዱት ቱትሲዎች ተደራጅተው ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ በጦር ኃይል አማካኝነት ወደ አገራቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ሲጀምሩ፤ ለዘመናት እያመረቀዘ የመጣው የዘር ጥላቻ፣ አገሪቷ ነፃ ከወጣች ከ32 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም. ፈንድቶ፣ መቶ በማይሞሉ ቀናት ውስጥ በሩዋንዳዎች ስሌት አንድ ሚልዮን ሶስት መቶ ሺህ ቱትሲዎችና ጥቂት ለዘብተኛ ሁቱዎች፤ ህፃን፣ አሮጊትም ሆነ ሽማግሌ ሳይባል በቆንጨራ ራሳቸውን ለሁለት በመበርቀስ ተጨፈጨፉ፡፡
ፈረንጆች፣ አንድ ክፉ ነገር አሸንፎ የሚወጣው በጥቂት ሰዎች ዝምታ ምክንያት ነው የሚል አባባል አላቸው፡፡ በዚህ ድሀ ሕዝብ ጫንቃ ተምረው፣ ኑሮአቸውን ካደላደሉ በኋላ አገር አማን ነው ብለው ዝምታን መርጠው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ ቢያንስ የሕሊና ወቀሳ እንደሚነዘንዛቸው ሊክዱ አይችሉም፡፡ በዚህ አደገኛ ጊዜ ዝምታ ወርቅ ሳይሆን ክህደት ነው፡፡ በሥልጣን ላይ የተቀመጡ ሰዎች ስልጣንና ቁሳዊ ጥቅሞች አይናቸውን ጋርዶት፣ ልሳናቸውን ዘግቶት እንደሆነ አይናቸውን መግለጥ ብቻ ሳይሆን ቢበለጥጡት ይበጃቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህች አገር በዘር ጥላቻና በሙስና ምክንያት ብትፈርስና የጅምላ እልቂት ቢከሰት፤ በመጀመርያ የገመዱ ሸምቀቆ የሚገባው በእነርሱ አንገት መሆኑን መዘንጋት የለባቸውምና፡፡ በአገራችን የዘር ጥላቻ በየእለቱ የምናየው ነገር መሆኑ፤ በዚህ ጥላቻ ምክንያትም አገራችን ወደገደል እያመራች መሆኑን አሌ የሚሉ መሪዎችም ሆኑ ምሁራን፤ አውሎ ነፋስ እየመጣ መሆኑንና ሊያደባያት እንደሚችል እያወቀች ራሷን አሸዋ ውስጥ በቀበረች ሰጐን ይመሰላሉ፡፡ ስለዚህ ዘረኝነት የሚያስከትለው አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት የጅምላ እልቂት እርቆ ሳይሄድ፣ መዋጋት ዛሬ እንጂ ለነገ የሚተው አይደለም፡፡ የዚህ ጸሐፊ አስተያየትና ግንዛቤ ስህተት ቢሆን ምንኛ በተደሰተ! ስህተት ባይሆንስ? አንዴ ካንሸራተተ መመለስ እንደማይችል ወይንም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ለመሆኑ፤ በመፍረስ ላይ ያሉት እነሶርያ፣ የመሃከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክና ደቡብ ሱዳን (ግብጽ እንኳን ሳትቀር) ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡
የችግራችን መፍትሔ ሁሉም ሊገባው በሚችልበት፣ በሁለት ቃላት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ይህን ያህል የዘር ጥላቻ ተካርሮ ወደ ግጭት ባላመራባት ኢትዮጵያ ቀርቶ፤ በዚያ በጥቂት ቀናት ውስጥ በዓለም ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እልቂት በተፈጸመባት ሩዋንዳ እንኳን፤ ዛሬ በሕዝቡ መሀከል እርቅ ወርዶ፣ ሩዋንዳ በአፍሪቃ የሰላምና የእኩልነት ተምሳሌት ለመሆን ችላለች፡፡ ዛሬ ሩዋንዳዊ እንጂ እገሌ ሁቱ ነው፣ እገሌ ቱትሲ ነው ማለት አጸያፊ ሆኗል፡፡ ስለዚህ፣ ምንም እንኳን መጪዎቹ ጊዜያት አስፈሪ ቢሆኑም ቅሉ፤ ብሔራዊ ዕርቅ በሚሉ ሁለት ቃላት፣ መፍትሔውን ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
በአገራችን የኢሕአዴግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች ፈቃደኝነት እስካለ ድረስ፣ በቀላሉ እርቅ ወርዶ፣ ለዘር ጥላቻ መንስኤ የሆኑ ነገሮች ታርመው፤ አገራችን ሰላም፣ ፍቅርና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ከመሆን ምንም የሚያግዳት ነገር አይኖርም፡፡ ብሔራዊ ዕርቅ ይውረድ ሲባል፣ “ማን ከማን ጋር ተጣልቷል?” ብሎ መቀለድ፤ በኋላ መሪር ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ ብሔራዊ መግባባት እንዴት ይመጣል የሚለው፣ በአገሪቱ እኩልነት፣ ዴሞክራሲና ፍትሕ ያለመ በአገር ደረጃ የሚወሰን ሲሆን፤ ለመነሻነት ያህል ቀጥሎ በተዘረዘሩት መጀመር ይችላል፡፡
ሀ) ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲና የሃይማኖት መሪዎችና አባላት፤ በጠቅላላው ከፖለቲካና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎችን በሙሉ መፍታት፤
ለ) የጸረ-ሽብርተኛ አዋጅ መሰረዝ፤ እና
ሐ) በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች አባላትና መሪዎችን በሽብርተኛነት የተፈረጁትንም አጠቃሎ የያዘ አንድ ጉባዔ በአዲስ አበባ ማካሄድ፤ የሚሉት መነሻ ሊሆኑን ይችላሉ ብዬ አምናለሁ፡፡
ይህ በሀገራችን ያለው ሁኔታም፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው የሚገባ በመሆኑ፣ ጽሑፉን ያነበበ ለሌላ ቢያስተላልፈው ግንዛቤ ለማስጨበት የሚረዳ ይመስለኛል፡፡
የዘር ጥላቻንና የጐሣ ግጭቶችን በጠቅላላው ጐሰኛነትንና ጐጠኛነትን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ድሮ ልናልፋቸው በተገባ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እኮ፣ ከብዙ አገራት ቀድማ አገራዊ አንድነትና ሉዐላዊነት የተጐናጸፈች፣ ጥልቅ ታሪክና የራስዋ ፊደልና የዳበረ ባህል ያላት አገር ነች፡፡ ሕዝቡም ለብዙ ምዕተ ዓመታት ክፉውንና ደጉን እየተጋራ በነፃነት የኖረ ሲሆን፤ ትናንት የተፈጠሩ አገራት ዘረኝነትንና ጐጠኝነትን አልፈው ሄደው አገራዊ አንድነት ሲፈጥሩ፣ እኛ በብሔረሰቦች መብት ስም እንዴት በዘረኝነት ውስጥ እንደነጋገራለን? ኢሕአዴግ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በመታወቂያ ካርድ እየለየ በጐሣ ወይንም በብሔር ከረጢት ውስጥ እንዲገባ ከመደንገጉ በፊት፣ ይህንን ዛሬ የተንሰራፋውን ጐሰኝነት ልናልፈው ተቃርበን ነበር፡፡ በነገራችን ላይ በሩዋንዳ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ቀላል ካደረጉት ነገሮች አንዱ፣ ሕዝቡ በነቂስ ዘሩን ወይንም ብሔሩን የሚያመላክት መታወቂያ አውጥቶ እንዲይዝ መደረጉ ነበር፡፡
በኢትዮጵያም ይህ አላስፈላጊ የሆነ ዝርዝር ሁኔታ፣ ማለትም ብሔረሰብ በመታወቂያ ካርድ ላይ እንዲጠቀስ የመደረጉ ጥቅም ምን እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ጐሰኝነትንና ጐጠኝነትን ልናልፋቸው ተቃርበን እንደነበረ ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል ከሰላሳ ዓመታት በፊት ዩኒቨርስቲ አካባቢ፣ አንድ ሰው ከኢትዮጵያዊነቱ ውጭ አማራ ይሁን ኦሮሞ፤ ጉራጌ ይሁን ከምባታ አይታወቅም ነበር፡፡ ቢታወቅም በጓደኛ አመራረጥ ላይ የብሔር ማንነት ምንም ተጽእኖ እንዳልነበረው በዩኒቨርስቲው ያለፉ ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡ በጊዜው የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ኢሕአፓ፣ መኢሶን፣ ኢዲዩ፣ ኢሠፓ፣ ወዘተ ሕብረ ብሔራዊ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ ከሕወሓትና ከኦነግ ውጭ ጐሰኝነትን መሰረት ያደረገ ፓርቲ አልነበረም፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሊቀበሉት የሚገባ አንድ ሐቅ ግን አለ፡፡
ይኸውም ዛሬ የአንድ ጐሳ ወይንም ብሔር
አባል ቋንቋውን የመናገርና የማበልጸግ፣ በባህሉ መኩራትና መተግበር፣ የውስጥ አስተዳደሩን ራሱ የመምራት መብት
እንዳለው አጠያያቂ ያለመሆኑ በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት እውቅና ያገኘ ጉዳይ ነው፡፡ ሆኖም እንዲህ
ዓይነት ያልተገደበ መብት መገንጠልን እንደማይጨምር አንዳንድ ኢትዮጵያውያን የተረዱት አይመስልም፡፡ የመገንጠል መብት
መቼና በምን ሁኔታ ይፈቀዳል የሚለው ጥያቄ ሰፊ ርዕስ በመሆኑ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን፡፡ የእነዚህ የብሔረሰብ
መብቶች መከበር፣ ዘረኝነትን አጥፍተው ብሔራዊ አንድነትን ያዳብራሉ እንጂ አያዳክሙም፡፡
ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ፡፡ በስውር ቋንቋ ሳንሸፋፍነው፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳናሽሞነሙነው ከተነጋገርን፤ በአገራችን የዘር ጥላቻ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየተንሰራፋና እየተስፋፋ መሄዱ፣ ሰው ሁሉ ያወቀው ጸሐይ የሞቀው እውነታ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ በእነዚህ 23 ዓመታት ውስጥ የዘረኝነት ክስተቶች የተገለጡባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች በጣም ብዙ ስለሆኑ፣ ለናሙና ያህል ጥቂቶችን ብቻ እንጥቀስ፡፡
ወደ ዋናው ጉዳያችን እንግባ፡፡ በስውር ቋንቋ ሳንሸፋፍነው፣ በዲፕሎማሲያዊ ቋንቋ ሳናሽሞነሙነው ከተነጋገርን፤ በአገራችን የዘር ጥላቻ አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየተንሰራፋና እየተስፋፋ መሄዱ፣ ሰው ሁሉ ያወቀው ጸሐይ የሞቀው እውነታ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ በእነዚህ 23 ዓመታት ውስጥ የዘረኝነት ክስተቶች የተገለጡባቸው ቦታዎችና ሁኔታዎች በጣም ብዙ ስለሆኑ፣ ለናሙና ያህል ጥቂቶችን ብቻ እንጥቀስ፡፡
በብሔር ወይንም በዘር ልዩነት ምክንያት ከሕይወት መጥፋት ጀምሮ ያሉ ግጭቶች ያልተከሰቱባቸው የአገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች
ጥቂቶች ናቸው፡፡ አንድ ጐሳ ወይንም ብሔር ከሌላ ጐሳ ጋር ተጋጭቶ፤ ይህን ያህል ሰው ሞተ፣ ይህን ያህል ንብረት
ወደመ የሚል ዜና ሰርክ እየሰማን ነው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት አንዳንድ ሃፍረተ ቢስ ኃላፊነት የጐደላቸው
ኢትዮጵያውያን፣ በፌስ ቡክ አማካይነት የሩዋንዳ እልቂት በኢትዮጵያ መደገም አለበት የሚል አስደንጋጭ መልእክቶች
እንደሚያስተላልፉ ሳንረዳ አንቀርም፡፡ ጨቅላ ሕፃን ይዛ የእለት ጉርስዋን የምትለምነው የእኔ ቢጤ እንኳን፣ ብሔሯን
ከምትለምነው ሰው መደበቅ አለባት፡፡ አለበለዚያ ተለማኙ ሰውዬ የማይወደው ብሔር አባል መሆኗን ካወቀ፣ የዳቦ ሳንቲም
መንፈግ ብቻም ሳይሆን ብሔሯን እየጠቀሰ ሊቀልድባት ይችላል፡፡
መንግሥት አለ ወይ እስኪባል ድረስ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን፣ የክልሉ ብሔር አባላት
አይደላችሁምና ከክልሉ ወይንም ከወረዳው በዚህ ቀናት ውጡ እየተባለ፤ የአካባቢው ሕዝብ ማፈናቀሉን ቢቃወምም
እንኳን፣ ባለስልጣናቱ እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ሜዳ እንዲወድቁ አድርገዋቸዋል፡፡ በጊዜው
በኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቁጣ በታጀበ ንግግራቸው፣ በቤኒሻንጉል አማርኛና
ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከኖሩበት ክልል ማፈናቀል ሕገ-ወጥ መሆኑን እና ጥብቅ እርምጃም በአስቸኳይ
እንደሚወሰድ ገልጸው ነበር፡፡
አስገራሚው ነገር ደግሞ ተፈናቃዮቹ ወደ ቤት ንብረታቸው ካለመመለሳቸውና መንግስት
ነገሩን ናቅ አድርጐ ከመተው ባሻገር፣ እንዲያውም ተጨማሪ ዜጐች እንዲፈናቀሉ ተደርጓል፡፡ ‹‹አለማወቅ ደጉ›› ሆነና
ነው እንጂ፤ በዓለም አቀፍ ወንጀለኝነት የሚታወቀው የዘር ማጥፋት ወንጀል የሚፈጽሙና የፈጸሙ ባለስልጣናት ምን
እንደሚጠብቃቸው ቢያውቁ እንቅልፍ በዓይናቸው ባልዞረ ነበር፡፡ ከሰባ አመታት በፊት ለፈጸሟቸው ዓለም አቀፍ ወንጀሎች
የቀድሞ ናዚ ጀርመናውያን፤ ስፔን ውስጥ ተይዘው፣ በዚሁ በያዝነው ዓመት ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ የቀድሞው
ዩጐዝላቪያ መሪ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ፊት የቆመው፣ ግድያ ቢኖርም ግን በዋናነት ሰርቦች ሙስሊሞችን
ከቤት ንብረታቸው አፈናቅለው ካምፕ ውስጥ አጉረው በማሰቃየታቸው ነው፡፡
የዘር ጥላቻ የሰውን ሕሊና ከሚሰውሩ፣ የሰው ልጅ የመጨረሻ አውሬነት አፍጥጦ እንዲወጣ ከሚያደርጉ ክፉ ድርጊቶች አንዱ ነው፡፡ የዘር ጥላቻ ተደጋግሞ እንደታየው በዘር ማጥፋት ይደመደማል፡፡ ቦስኒያ ውስጥ ሰርብ ያልሆኑት ዜጐችን መጨፍጨፍ፣ ኦቶማኖች በአርመኖች ላይ ያደርሱት እልቂት፣ የጀርመን ናዚዎች በይሁዲዎች ላይ የፈጸሙት ግድያና ስቃይ፣ ሳዳም ሁሴን በኩርዶች ላይ ያካሄደው የዘር ምንጠራ፣ ፖል ፖት ያካሄደው ገደብ የለሽ ጭፍጭፋ፣ ሁቱዎች በቱትሲዎች ላይ የፈፀሙት እልቂት፤ በዘር ጥላቻ ላይ ተመስርተው ከተፈፀሙ ግድያዎችና ሰቆቃዎች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ አሳዛኙ ነገር ዘረኛነት ከመሰረተው ስርዓት ተጠቃሚ ያልሆኑ የዚያ ዘር አባላትንም ለብቀላውና ለጥቃቱ ሰለባ ማድረጉ ነው፡፡
የዘር ጥላቻ ከወለዳቸው ዕልቂቶች መሀከል፣ እንስሳት እንኳን ሊፈጽሙት ከማይችሉት የጭካኔ ተግባራት የሚቆጠረው የሩዋንዳው የቱትሲዎች እልቂት ቀዳሚነቱን ሳይዝ አይቀርም፡፡ ሩዋንዳ የቤልጅየም ቅኝ ግዛት በነበረችበት ጊዜ፤ ቅኝ ገዢዎቹ አፍንጫ ሰልካካና ቁመተ ረጃጅምና ከኢትዮጵያ ፈልሰው እንደሄዱ የሚነገርላቸውን ከሕዝቡ 15% የሚሆኑትን ቱትሲዎች ወኪል በማድረግ፣ 85% በሆኑት መደበኛ አፍሪካዊ መልክ ባላቸው ሁቱዎች ላይ አነገሷቸው፡፡ የቱትሲዎችና የኢትዮጵያ ግንኙነት ከተነሳ፤ ከሃያ ሺህ በላይ ቱትሲዎች እግርና እጃቸውን ታስረው ወደአገራችሁ ኢትዮጵያ ግቡ ተብለው ወደሰሜን ከሚፈስ ቪክቶሪያ ኃይቅ ጋር ከሚቀላቀል ወንዝ ውስጥ መጨመራቸው ይታወቃል፡፡ ሥልጣን በመጠቀም የመንግሥቱን ቢሮክራሲ፣ ንግዱን፣ ትምህርቱን፣ የከብት እርባታውን በመጠቅለል ሁቱዎችን መብት አልባ ዜጐች አደረጓቸው፡፡
ቂም ቋጥረው የኖሩት ሁቱዎች፣ እ.ኤ.አ. በ1962 ዓ.ም. ሩዋንዳ ነፃ ስትወጣ የመንግሥቱን ሥልጣንና መዋቅራት፣ ቢሮክራሲውን፣ የትምህርቱና የንግድ ዘርፎችን በሙሉ ከመጠቅለል አልፈው፤ በቱትሲዎች ላይ የበቀል እርምጃ መውሰድ ጀመሩ፡፡ ቤት ንብረታቸውን ንግዳቸውን የተዘረፉት፣ ከቢሮክራሲው የተባረሩት ቱትሲዎች ደግሞ ወደኡጋንዳ ተሰደዱ፡፡ ወደኡጋንዳ የተሰደዱት ቱትሲዎች ተደራጅተው ወታደራዊ ስልጠና በመውሰድ በጦር ኃይል አማካኝነት ወደ አገራቸው ለመመለስ እንቅስቃሴ ሲጀምሩ፤ ለዘመናት እያመረቀዘ የመጣው የዘር ጥላቻ፣ አገሪቷ ነፃ ከወጣች ከ32 ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ. በ1994 ዓ.ም. ፈንድቶ፣ መቶ በማይሞሉ ቀናት ውስጥ በሩዋንዳዎች ስሌት አንድ ሚልዮን ሶስት መቶ ሺህ ቱትሲዎችና ጥቂት ለዘብተኛ ሁቱዎች፤ ህፃን፣ አሮጊትም ሆነ ሽማግሌ ሳይባል በቆንጨራ ራሳቸውን ለሁለት በመበርቀስ ተጨፈጨፉ፡፡
በኢትዮጵያ ፋሽስቱ ደርግ እንዳደረገውም፣ አንዳንዶቹ የሚገደሉበትን ጥይት መግዛት መቻላቸውን እንደ
አንድ ልዩና ጥሩ ዕድል ቆጥረውታል፡፡ የሩዋንዳ ሁቱ ጨፍጫፊዎች ተራ የመንደር ወይንም የገዢው ፓርቲ ዱርዬዎች
(ኢንተራሃሞዌ) ብቻ ሳይሆኑ፤ የዘር ጥላቻ ምሁር ወይንም መሃይም ስለማይል የታወቁ ምሁራን እና ቄሶች ሳይቀሩ
ተሳትፈዋል፡፡ በመሃል ኪጋሊ አንድ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ሁቱ ቄሶች ቱትሲ ቄሶችና ምዕመናንን የጨፈጨፉት የሬሳ
ክምር፣ ዛሬም በቤተ-ክርስቲያኑ ውስጥ ይታያል፡፡ ቱትሲዎች ወደኡጋንዳ ሲሰደዱ የ6 ዓመት ሕፃን በነበረው በዛሬው
ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ መሪነት፣ በጦርነቱ አሸንፈው አገሪቱን ሲቆጣጠሩ፤ ቁጥራቸው የበዛ ሁቱዎች በተራቸው
ተገድለዋል፡፡ የእነዚህ የሁለቱ ጐሳዎች መጨፋጨፍ የአገር ጥፋትንና የጅምላ እልቂትን ከመውለዱ ውጪ፤ በዘር ጥላቻ
አሸናፊና ተሸናፊ እንደሌለ አመላካች ነው፡፡
ፈረንጆች፣ አንድ ክፉ ነገር አሸንፎ የሚወጣው በጥቂት ሰዎች ዝምታ ምክንያት ነው የሚል አባባል አላቸው፡፡ በዚህ ድሀ ሕዝብ ጫንቃ ተምረው፣ ኑሮአቸውን ካደላደሉ በኋላ አገር አማን ነው ብለው ዝምታን መርጠው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ ቢያንስ የሕሊና ወቀሳ እንደሚነዘንዛቸው ሊክዱ አይችሉም፡፡ በዚህ አደገኛ ጊዜ ዝምታ ወርቅ ሳይሆን ክህደት ነው፡፡ በሥልጣን ላይ የተቀመጡ ሰዎች ስልጣንና ቁሳዊ ጥቅሞች አይናቸውን ጋርዶት፣ ልሳናቸውን ዘግቶት እንደሆነ አይናቸውን መግለጥ ብቻ ሳይሆን ቢበለጥጡት ይበጃቸዋል፡፡ ምክንያቱም ይህች አገር በዘር ጥላቻና በሙስና ምክንያት ብትፈርስና የጅምላ እልቂት ቢከሰት፤ በመጀመርያ የገመዱ ሸምቀቆ የሚገባው በእነርሱ አንገት መሆኑን መዘንጋት የለባቸውምና፡፡ በአገራችን የዘር ጥላቻ በየእለቱ የምናየው ነገር መሆኑ፤ በዚህ ጥላቻ ምክንያትም አገራችን ወደገደል እያመራች መሆኑን አሌ የሚሉ መሪዎችም ሆኑ ምሁራን፤ አውሎ ነፋስ እየመጣ መሆኑንና ሊያደባያት እንደሚችል እያወቀች ራሷን አሸዋ ውስጥ በቀበረች ሰጐን ይመሰላሉ፡፡ ስለዚህ ዘረኝነት የሚያስከትለው አሸናፊና ተሸናፊ የሌለበት የጅምላ እልቂት እርቆ ሳይሄድ፣ መዋጋት ዛሬ እንጂ ለነገ የሚተው አይደለም፡፡ የዚህ ጸሐፊ አስተያየትና ግንዛቤ ስህተት ቢሆን ምንኛ በተደሰተ! ስህተት ባይሆንስ? አንዴ ካንሸራተተ መመለስ እንደማይችል ወይንም እጅግ በጣም አስቸጋሪ ለመሆኑ፤ በመፍረስ ላይ ያሉት እነሶርያ፣ የመሃከለኛው አፍሪቃ ሪፐብሊክና ደቡብ ሱዳን (ግብጽ እንኳን ሳትቀር) ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡
የችግራችን መፍትሔ ሁሉም ሊገባው በሚችልበት፣ በሁለት ቃላት ማስቀመጥ ይቻላል፡፡ ይህን ያህል የዘር ጥላቻ ተካርሮ ወደ ግጭት ባላመራባት ኢትዮጵያ ቀርቶ፤ በዚያ በጥቂት ቀናት ውስጥ በዓለም ተወዳዳሪ ያልተገኘለት እልቂት በተፈጸመባት ሩዋንዳ እንኳን፤ ዛሬ በሕዝቡ መሀከል እርቅ ወርዶ፣ ሩዋንዳ በአፍሪቃ የሰላምና የእኩልነት ተምሳሌት ለመሆን ችላለች፡፡ ዛሬ ሩዋንዳዊ እንጂ እገሌ ሁቱ ነው፣ እገሌ ቱትሲ ነው ማለት አጸያፊ ሆኗል፡፡ ስለዚህ፣ ምንም እንኳን መጪዎቹ ጊዜያት አስፈሪ ቢሆኑም ቅሉ፤ ብሔራዊ ዕርቅ በሚሉ ሁለት ቃላት፣ መፍትሔውን ማስቀመጥ ይቻላል፡፡
በአገራችን የኢሕአዴግ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች ፈቃደኝነት እስካለ ድረስ፣ በቀላሉ እርቅ ወርዶ፣ ለዘር ጥላቻ መንስኤ የሆኑ ነገሮች ታርመው፤ አገራችን ሰላም፣ ፍቅርና ዴሞክራሲ የሰፈነባት ከመሆን ምንም የሚያግዳት ነገር አይኖርም፡፡ ብሔራዊ ዕርቅ ይውረድ ሲባል፣ “ማን ከማን ጋር ተጣልቷል?” ብሎ መቀለድ፤ በኋላ መሪር ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል፡፡ ብሔራዊ መግባባት እንዴት ይመጣል የሚለው፣ በአገሪቱ እኩልነት፣ ዴሞክራሲና ፍትሕ ያለመ በአገር ደረጃ የሚወሰን ሲሆን፤ ለመነሻነት ያህል ቀጥሎ በተዘረዘሩት መጀመር ይችላል፡፡
ሀ) ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲና የሃይማኖት መሪዎችና አባላት፤ በጠቅላላው ከፖለቲካና ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎችን በሙሉ መፍታት፤
ለ) የጸረ-ሽብርተኛ አዋጅ መሰረዝ፤ እና
ሐ) በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች አባላትና መሪዎችን በሽብርተኛነት የተፈረጁትንም አጠቃሎ የያዘ አንድ ጉባዔ በአዲስ አበባ ማካሄድ፤ የሚሉት መነሻ ሊሆኑን ይችላሉ ብዬ አምናለሁ፡፡
ይህ በሀገራችን ያለው ሁኔታም፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው የሚገባ በመሆኑ፣ ጽሑፉን ያነበበ ለሌላ ቢያስተላልፈው ግንዛቤ ለማስጨበት የሚረዳ ይመስለኛል፡፡
May 17, 2014
እውነታ + እውቅና + ፍትህ = እርቅ (ያዬ አበበ)
Posted on May 17, 2014
የኢትዮጵያ
ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ለዚህ ተተኪ ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርዓያነት
ማውረስ አስፈላጊነት ስላመንኩበት ስለ እርቅና መግባባት ለመሟገትና ፋና ወጊ ሚና ለመጫወት የዜግነት ሃላፊነቴን
ጀምሬያለሁ።
ሰዎች እርቅን የተለያዬ ትርጉም እንደሚሰጡት የ65Percent.org ድረ-ገጽን ከጀመርኩበት ከዚህ አመት አጥቢያ አንስቶ እየተረዳሁ ነው። ድረ-ገጼን ከመጀመሬ በፊት ከ16 ኢትዮጵያውያን ጋር በፓልቶክ የፖለቲካ መወያያ ክፍሎች የሃሳብ አሰሳ አድርጌያለሁ። ከአሰሳው እንደተረዳሁት ስለእርቅ እና ፖለቲካዊ መግባባት በቂ የሚዲያ ሽፋንም ሆነ ውይይት አልተደረገም።
ለአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ከትጥቅ ትግልና ከአመጽ የላቀ አማራጭ
አለን፦ የእርቅና መግባባት አማራጭ። በዚህ አጭር ጽሁፍ ሰለፖለቲካዊ እርቅና መግባባት በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ጥቂት
አጠቃላይ ነጥቦችን እዳስሳለሁ።
ሁለት ጭብጦች፦ ውጥረትና አለመግባባት
አንደኛ፦ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ስርአትና ሂደት በውጥረት ውስጥ ይገኛል። ሁለተኛ፦ የአገራችን ፖለቲካ በእጅጉ ባለመግባባት የተጠመደ
ነው። እነዚህ ሁለት ጭብጦች የአደባባይ ሚስጥር ቢሆኑም መፍትሄ ለመቅረጽ በነዚህ ነጥቦች ላይ መስማማቱ እንደ
ቅደመ ሁኔታ እመለከተዋለሁ። ውጥረትና አለመግባባት የሰፈነበትን ፖለቲካችንን ማርገብና ማግባባት መሰረታዊ የእርቅ
ግብ ነው።
መደበኛ ፓለቲካዊ ሂደት
የፓለቲካችንን ውጥረት ማርገብ ለፓለቲካዊ መግባባት ሁኔታዎችን
ያመቻቻል። የአገራችን ፖለቲካ ላለፉት 40 አመታት ከነውጥ ወደ ቀውስ ፤ ከአመጽ ወደ እልቂት ፤ ከቁስል ወደ
ቂምና ጥላቻ ሲገለባበጥ የቆየ ነው። ፖለቲካችን መደበኛ ሆኖ አያቅም። መደበኛ ፓለቲካዊ ሂደት ማለት ከቀውስ ፥ ከደም መፋሰስ ፥ ከአላስፈላጊ ውጥረትና ከጥላቻ ውጥቶ ፥ ወደ ሚዛናዊ የሃሳብ ፉክክርና ፍትሃዊ ሂደት ውስጥ የገባ ማለት ነው።
ፓለቲካዊ ቅራኔ
የፓለቲካዊ ውጥረታችን መንስኤው ፓለቲካዊ ቅራኔ ነው።
የአገራችን ፓለቲካዊ ውጥረት የብዙ ዘመናት ፡ የልዩ-ልዩ ድርብርብ ቁስሎች ፡ ቁርሾዎች ፡ ያልተቋጩ ታሪካዊ
ክስተቶች ፡ ርዮተአለሞች ፡ ማንነቶች ፡ ስሜቶች … ወዘተ ውጤት ነው። እነዚህ ድርብርብና ዘርፈ-ብዙ የቅራኔ
መንስኤዎች አልፎ አልፎ ምልክታዊ ትኩረት አግኝተዋል። እንደ ዋቢ ከሚጠቀሱት አንዱ የቀይ ሽብር መታሰቢያ ሙዚየም
ሲሆን ፡ ሌላው የወታደራዊው መንግስት ባለስልጣናት ከእስር መለቀቅ ነው።
ሆኖም ግን የፖለቲካ ቅራኔያችን ሲባባስ ፥ የፖለቲካ ምህዳር
ሲጠብ ፥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመድብለ ፓርቲ ስርአት ወደ አሃዳዊ ፓርቲ ቁጥጥር ሲያዘነብል እንጂ ፡ ወደ መደበኛ
ፖለቲካዊ ሂደት ሲገባ አይታይም።
ዘርፈ-ብዙ መፍትሄ
በቅራኔ እየከረረ ያለው ፓለቲካዊ ውጥረታችንን ማርገብ የምንችለው
የቅራኔው መንስኤዎች ላይ በማተኮር ፥ ተግባራዊና አስታራቂ መፍትሄ በመወጠን ነው። ይሄንን ለማድረግ የሌሎች
አገሮችን ተሞከሮ በአርአያነት በመጠቀም የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ቅራኔ ምንጮች ማድርቅ እንችላለን።
ይሄን ለማድረግ የኔልሰን ማንዴላ መንግስት የወሰደውን
ቀመር/ፎርሙላ መጠቀሙ አማራጭ የሌለው ሆኖ አግኘቼዋለሁ። ማንዴላ የደቡብ አፍሪካ ነጮች መንግስት በጥቁሮችና በሌሎች
ዘሮች ላይ ያደረገውን ግፍና እልቂት በጥበብና አርቆ አስተዋይነት አርግቦታል።
ምንም እንኳን ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ በእጅጉ የተለያዬ ፓለቲካዊ ሁኔታዎች ላይ ያሉ ቢሆንም፥ የማንዴላ ቀመር የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ውጥረት ለማርገብ ፍቱን መድሃኒት መሆኑን አምንበታለሁ። ላብራራ።
የማንዴላ ቀመር/ፎርሙላ፦ እውነታ + እውቅና + ፍትህ = እርቅ
የማንዴላ መንግስት የውጥረት ማርገብ ስራውን የጀመረው እውነታን በማፈላለግ ስራ ነው። ቀጥሎም በተሰበሰበው መረጃ ላይ እውቅና የመስጠት ስራ ተካሄደ። የእውቅና ሂደቱን በቴሌቪዥን የተከታተላችሁ እንደምታስታውሱት በጣም ልብ ይሚነካ ሂደት ነበር። በመጨረሻም እውነታ ማፈላለጉና እውቅና የመስጠቱ ስራ ወደ ፍትህ አመራ።
የፍትህ ሂደቱ አንዳንድ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ መንግስት
ተሳታፊዎችን ከክስ ነጻ ማድረጉ ይታወሳል። ይህ የሆነው በእውነታና በእውቅና ሂደት ውስጥ ስለተሳተፉና ለፈጸሙት
በደል ይቅርታ ሰለጠየቁ ፡ እንዲሁም ያንን በማድረጋቸው የማንዴላ መንግስት ለተሳታፊዎቹ ከሰጣቸው ዋስትና የተነሳ
ነበር። ለተበዳዮችና ቤተሰቦቻቸውም የደቡብ አፍሪካ መንግስት የገንዘብ ካሳ ከፍሏል። ውጥረትን ማርገብ ማለት ይህ ነው።
የእርቅ ሂደት ውጥረትን ያረግባል ፡ ለመግባባት ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል።
እውነታ + እውቅና + ፍትህ = እርቅ!
*********
ያዬ አበበ የ65Percent.org መስራች ነው። የ65ፐርሰንት ድረ-ገጽ ግብ ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት የመሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።
Feb 13, 2014
Democracy and its Trade-off: Ethiopia’s Path to National Reconciliation – Messay Kebede, PhD
Posted on February 13, 2014
![]() |
| Messay Kebede, PhD |
Before I go further, there is one basic hurdle that needs to be removed. Every time I propose a government of national reconciliation, I face two different objections. Some pity my naivety and demolish my proposal with a heavy blow of realism by asking, why would the ruling elite invite the opposition parties when it feels strong in the face of a weak and divided opposition? Others tell me that my position does no more than side with the ruling party by throwing cold water on the struggle to remove the EPRDF which, they say, is beyond redemption.
Parties and groups advocating and actually carrying out armed struggle to dislodge the ruling party are entitled to ridicule my proposal. Their rejection is in perfect accord with their view of the TPLF as a party fundamentally hostile to Ethiopia’s interests. However, those parties and groups that champion non-violent form of struggle should refrain from adopting the same stand. Most of them work with the belief that democratic elections are the only means to bring about real change in Ethiopia. As a result, they expect the EPRDF to hand over power in the case they win the majority of parliamentary seats.
This expectation is, for me, the apex of political gullibility: there is nothing more unlikely than a party as sectarian, suspicious, and panicky as the TPLF surrendering power peacefully. The best that elections can achieve, in the remote case that they are relative democratic, is the possibility for the opposition to participate in political life as a minority party. If election cannot achieve the removal of the ruling party, then my proposal looks rational and realistic for the reason that it is a win-win alternative that ruling elite and opposition parties can bring to life with a little dose of realism and good faith.
Consider for one moment the political situation in today’s Ethiopia. It is ruled by an incompetent, mediocre, self-serving, and divided group. For a short time, I speculated together with other observers that Haile Mariam Dessalegn may try to implement a less repressive policy providing the opposition with some space for political expression. In effect, we saw some signs of reduced repression, for example the lifting of the ban on political demonstrations. We expected the next logical step, which should have been the freeing of unjustly jailed political prisoners. This next step did not come about; instead, the new prime minister saw his power curtailed by the unconstitutional addition of two deputy prime ministers whose obvious assignment is to make sure that decisions never divert from the wishes of the hegemonic party, namely, the TPLF. Though divided around different personalities, the TPLF still shows a remarkable determination to retain its hegemonic position at all costs. Consequently, even the baby steps toward relaxing repression are now reversed under various lame excuses. The outcome is a government without vision whose main purpose is to maintain the status quo through a weakened prime minister. I see no other reason for the violation of the constitution by the addition of deputy prime ministers than the fact that the new prime minister is not Tigrean.
The situation can only be described as a deadlock; it is moving neither forward nor backward. The only thing that can happen in a stalemate is a steady deterioration of the situation, with more and more Ethiopians becoming alienated and angry. Despite its illusion, this mediocre government, whose only expertise is corruption and repression, cannot stop this deterioration by itself. Deepening crises and finally popular uprisings are inevitable. And yet, though I energetically oppose the present government, I do not wish for the explosion of a generalized uprising. Not only I fear chaos, but also I am not convinced that the overthrow of this government will bring about democracy.
What I see, on the contrary, is either an uncontrollable irruption of violent social unrests exasperated by the government’s bloody repression or another form of dictatorship and revengeful policy against members of the ruling elites, their protégés, and those people perceived as ethnic foes, in the case where the present government collapses. I just don’t picture how democracy can come into being and grow on a soil poisoned by so much hostility, mutual suspicion, and exasperated ethnic divisions––some exhibiting secessionist tendencies––not to mention the abyssal divide between the haves and the have-nots. To direct this perilous situation toward a democratic process, Ethiopia needs a leader of the stature of Mandela, a condition that cannot be fulfilled any time soon.
The coming elections, some might say, could be a way out. Such is actually the expectations of all those opposing parties that have accepted the constitution and a non-violent approach. Unfortunately, even if the opposition does well in elections, the outcome will be a repeat of the 2005 election. I cannot picture the ruling party conceding even a modest place for the opposition in a political atmosphere where any gain of the opposition, however small, is perceived as having ominous consequences for the ruling elites. Let us not forget that what unites members of the ruling party is not shared appreciation, but survival, which is their only goal. So long as the ruling party is terrified by the prospect of losing power because it believes that the loss would certainly translate into a campaign of revenge and repression, this party cannot be expected to play fair in elections.
If popular uprisings or violent overthrow of the government are undesirable and elections are ineffective and if, on the other hand, there is a stalemate, what is then the way out? We must take here the bull by the horns and find a solution with a win-win outcome. I believe the formation of a government of national reconciliation to be such solution. It means a political arrangement in which the ruling party and the opposition parties participate, it is true unequally, in the same government. Obviously, the solution is not an ideal one, but it has the advantage of being affordable and, more importantly, of warding off dreadful consequences for everybody.
To the question of why it is the affordable solution, my answer has various facets. The one facet is that my proposal is logical or rational in that it is the only path that guarantees a win-win outcome for everybody. The process initiates a situation where the ruling elite is protected from all revengeful policy because it retains an appreciable power and the opposition can pressure for a change of policy that eases the glaring mistakes of the regime. In particular, the opposition gains the opportunity to freely organize without fear of repression. Because power is shared, it cannot be used to eliminate opponents. I add that there is no other way for the components of the EPRDF to lift the burden of the TPLF hegemony than to call for a government of reconciliation. The presence of opposition parties will force the TPLF to be more attentive to their viewpoints in order to prevail: their support becomes crucial and hence negotiable.
Doubtless, attempts to create governments in which ruling and opposition parties work together have failed in many countries. The reason seems obvious to me: many of these attempts were either imposed by patron countries or the existing government was in a weak position and needed to buy time to regain strength. The recent remarkable achievement of Tunisia confirms that a genuine willingness to include the opposition is the only way of moving toward a democratic path. After a bumpy road marred by assassination of opposition leaders followed by massive protests, the Tunisian prime minister announced the formation of a new government of technocrats. The decision was a clear concession to the secular and leftist oppositions whose main demand was the change of the pro-Islamist dominated government. This momentous concession led to the signing of a new constitution committed to a secular state and guaranteeing basic freedom and gender equality. “The constitution,” the assembly speaker said, “without being perfect, is one of consensus.” Contrast this outcome with that of Egypt: the refusal of the Morsi government to include the opposition in the political process despite large and violent protests demanding unity government only led to the ousting of the Islamist government by the military, which is but a serious setback in the democratization process.
Two major lessons can be drawn from the Tunisian experience. 1) There is no democracy without compromise with the opposition. The Leninist version still practiced by many African countries, including Ethiopia, and according to which democracy is the violent silencing of the “enemies of the people,” is diametrically opposed to the simple fact that democracy means the acceptance of participation in the political system of all those who have different programs from the ruling party. This same requirement applies to the opposition as well: opposing the government cannot mean the political exclusion of the ruling party by means of election or armed struggle under pain of adopting the Leninist version of democracy. 2) In the case of Ethiopia, which is entangled in the far more serious ethnic embroglios, the feasible solution is a government of national reconciliation, which government only works under the condition that all those concerned and especially the TPLF make the necessary concessions by themselves, that is, without external intervention. If it is imposed or accepted reluctantly, it will undoubtedly fail. As attested by the Tunisian case, the willingness to make it work must be equally present in all the parties. By will I understand a strong commitment emanating from well-thought out interests by all concerned, especially long–term interests. Simply put, it is a choice between dictatorial power––the severe downsides of which are blockage of development in all aspects of life and uncertainty with the constant danger of popular rebellion––and democracy with the promises of stability and the unleashing of the creative forces of the country. That is why I say it is a rational position.
I add that, on top of securing protection against revengeful policy, the TPLF can find another opportunity, no more to rule Ethiopia exclusively, but to become the patron of its democratization, a role that can be construed as a corrected continuation of the sacrifices paid to defeat the Derg. The perception by the people of the TPLF as a patron and protector of democracy is not only how it dissolves the popular resentment accumulated during two decades of repressive policy, but also how it acquires authority, as distinct from brute force, which authority can easily be used to build popular support within and outside Tigray.
A government of national reconciliation is by definition transitional; its main task is to create mutual confidence, realize some common goals achieved through consensus, define clearly the duties and rights of all participants, and ensure their protection by established institutions. Moreover, each time the government stumbles against a contentious issue that seems irreconcilable, it refrains from making any final decision. Instead, it agrees to put the matter to a popular vote as soon as conditions for fair debates and voting permit. How long this government of national reconciliation will last should also be a matter of agreement.
It follows that the immediate task of the government is not to organize elections; rather, it is to prepare the conditions of fair elections. To rush to elections without establishing the appropriate condition, especially the creation of an atmosphere of mutual confidence, is to invite the fear of “winner-take-all.” Elections must be organized only when all involved feel confident enough to no longer fear repression and revenge and when the country shows some sign of real development, not only for the few, but also for the many so that people see what is at stake when they cast their vote. The purpose of reconciliation is to create the hope for a better future for all involved and to get out of the present system in which the gains of some are built on the mistreatment of others.
Source: http://www.abugidainfo.com/index.php/22266/
Feb 7, 2014
ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ለኢትዮጵያ ጥናታዊ ጽሁፍ - ተክሉ አባተ
Posted on February 07, 2014
ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ለኢትዮጵያ: ጥናታዊ ጽሁፍ
![]() |
| ተክሉ አባተ |
በአገራችን ኢትዮጵያ ያለውን ብሄር ገነን ሥርዓት በእውነተኛ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ለመተካት ኢትዮጵያውያን
(የሌላ አገር ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንንም ማለቴ ነው) የተለያዩ መንገዶችንና ዘዴዎችን በመጠቀም
እየታገሉ ይገኛሉ:: በአገር ቤት ያሉ ወደ 100 የሚጠጉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በይፋ ሰላማዊ የትግል ስልት ይከተላሉ
ቀላል የማይባል ህዝብም በሰላማዊ መንገድ መታገል እንደሚበጅ ያምናል:: በጣት የሚቆጠሩ ድርጅቶች ደግሞ
እሾህን በእሾህ እንዲሉ መሳርያ አንስተው ወደበረሃ ገብተዋል:: እንደ ግንቦት 7 ያሉት ደግሞ ሁሉንም አይነት የትግል ስልት መጠቀም አዋጭ እንደሆነ ያምናሉ::
በአንድም በሌላም መንገድ ስለነዚህ የትግል ስልቶች አንጻራዊ አዋጭነትና አስፈላጊነት ውይይቶች ሲደረጉ
ነበር:: ነገር ግን የትኛው የትግል ስልት ትክክለኛ ለውጥ ለማምጣት አስተማማኝ እንደሆነ መደምደም የሚቻል
አይመስልም:: ለዚህም ይመስላል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማኅበራዊ ሚዲያዎችና በድረ ገጾች የሚደረጉ ውይይቶችና የሚለቀቁ
መጣጥፎች ይህን ጉዳይ በቀጥታ የማያነሱት::
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በርከት ያሉ ውይይቶችና መጣጥፎች እያተኮሩበት የመጣው ጉዳይ ትንሽ የተለዬ
ይመስላል:: ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማድረግ ለአገራችን ሰላማዊና ዘለቄታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚችል እየተነገረ ነው:: ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማድረግ ከባህላችን ጋር አብሮ ከመሄዱም በላይ እጅግ አስፈላጊና ወቅታዊም
እንደሆነ የሚሞግቱ አሉ:: በአንጻሩ ደግሞ ብሄራዊ እርቅ ፈጽሞ የማይሰራ ከመሆኑም በላይ የህግንና ፍትህን መርሆች የሚቃወም
እንደሆነ የሚያስጠነቅቁም አሉ:: አንዳንዶች ደግሞ ስለብሄራዊ መግባባትና እርቅ ማውራትና መወያየት የዋህነት አላዋቂነት ሃይማኖታዊነት
እንደሆነ በድፍረት ይናገራሉ:: ሌሎች ደግሞ ሃሳቡ መንግስትና ባለሥልጣናቱን ለመታደግ የታሰበ የቆረጣ ስልት እንደሆ ይጠቁማሉ::
ዳሩ ግን ብሄራዊ ኢትዮጵያዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ ጠቅለል ያለ የዳሰሳ ጥናት እስካሁን አልቀረበም:: ጉዳዩን በተመለከተ የሚደረጉት የተናጥል ውይይቶችና የተጻፉት መጣጥፎች የተሟላ ሃሳብ ለማግኘት አያስችሉም:: እንዲያውም በጉዳዩ ላይ ምን ያህል እንደተጻፈና ምን ምን ዝርዝር ሃሳቦች እንደተነሱ አይታወቅም:: ይህም ብሄራዊ መግባባትና እርቅ በይፋ እንደ አንድ የትግል ስልት እንዳይቆጠርና በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ
ዳብሮ ሥራ ላይ እንዳይውል ተጽእኖ አሳድሯል:: ይህን ችግር ለመቅረፍ የዳሰሳ ጥናት አስፈላጊ ሆኗል:: የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ዓላማ
ጉዳዩን በተመለከተ የተጻፉትን መሠረት በማድረግ አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖርና በርዕሱ ላይ ውይይት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማነሳሳት ነው::
የጥናቱ ዓላማ
የዚህ ጥናት ዋና ዋና ዓላማዎች ቀጥለው የተዘረዘሩት ናቸው::
1.
እስካሁን
ድረስ ስለብሄራዊ (ኢትዮጵያዊ) መግባባትና እርቅ በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ
ምን እንደተጻፈ መመርመር
2.
ብሄራዊ
መግባባትና እርቅን በተመለከተ በሚገባ ያልተብራሩ ሃሳቦችን ለይቶ ማውጣት
3.
ብሄራዊ
መግባባትና እርቅን በተመለከተ ወደፊት በጽንሰ ሃሳብና በተግባር ደረጃ ምን መደረግ እንዳለበት መጠቆም
የጥናቱ ዘዴና የመረጃ ምንጮች
በእርግጥ በድረ
ገጾች በፌስቡክ በፓልቶክ
ክፍሎች እንዲሁም በቴሌቪዥንና
በሬዲዮ ፕሮግራሞች ጉዳዩን
(ብሄራዊ መግባባትና እርቅን) የተመለከቱ
ውይይቶች ተካሂደው ይሆናል::
ለዚህ ጥናት እነዚህን
ሁሉ የመረጃ ምንጮች
ማካተቱ ጊዜ ወሳጅ
መሆኑ ታምኖበታል::
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን
የጥናቱን ዓላማዎች ለማሳካት
በዋና ዋና ድረ
ገጾች የታተሙ መጣጥፎችን
መመልከት ጠቃሚና ጊዜ
ቆጣቢ ሆኖ ተገኝቷል::
አንድም የተቀናጀ ጽሁፍ
በድረ ገጾች ማውጣት
የተለመደ ነውና:: በመሆኑም ይህ
ጥናት አራት ዋና
ዋና ድረ ገጾችን
በመረጃ ምንጭነት ተጠቅሟል::
እነሱም ECADF
Ethiomedia Ethiopian Review እና
Zehabesha ናቸው::
እነዚህ ድረ ገጾች
በኢትዮጵያዊያን
ዘንድ በደንብ የሚታወቁና
ፖለቲካዊ ማኅበራው ባህላዊ
ሃይማኖታዊ ምጣኔ ሃብታዊና
ሌሎችንም ጉዳዮች ያካተቱ
በርካታና ጠቃሚ ጽሁፎች
የሚታተሙባቸው
ናቸው:: በአጠቃላይ ሲታይ
እነዚህ ድረ ገጾች
ስለብሄራዊ መግባባትና እርቅ በቂ መጣጥፎችን እንደሚያትሙ ይገመታል::
በተመረጡት አራት ድረ ገጾችም የተጻፈውን ሁሉ አንድ በአንድ
መፈተሽ አሰልቺና ጊዜ ወሳጅ ከመሆኑም በላይ አላስፈላጊም ነው:: በመሆኑም የእያንዳንዱን ድረ ገጽ የመፈለጊያ ሳጥን Search
box በመጠቀም በጉዳዩ ላይ የተጻፉትን መጣጥፎች በቀላሉ ማግኘት ይቻላል:: ቀጥለው የተዘረዘሩትን የአማርኛና የእንግሊዝኛ
የመፈለጊያ ቃላት ወይም ቁልፎች keywords በመጠቀም አራቱም ድረ ገጾች ተፈትሸዋል::
·
National
dialogue
·
National consensus
·
National reconciliation
·
ብሄራዊ ውይይት
·
ብሄራዊ መግባባት
·
ብሄራዊ
እርቅ
በሌሎች ድረ ገጾች ጉዳዩን በተመለተ መጣጥፎች ታትመው ስለሚሆን Googleን በመጠቀም ተጨማሪ ፍለጋ ተካሂዷል:: ይህንም ለማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን የአማርኛና የእንግሊዝኛ የመፈለጊያ ቃላትን ተጠቅሜአለሁ:: በአጠቃላይ ሲታይ አራቱ ድረ ገጾች በርካታ በብሄራዊ መግባባትና እርቅ ላይ የተጻፉትን ይዘው ተገኝተዋል:: ዳሩ ግን በፍለጋው ያልተገኙ ጥቂት መጣጥፎች ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል:: የጥናቱ ዋና ዓላማ ስንት እንደታተመ መቁጠር ሳይሆን ምን እንደተባለ መመርመር ስለሆነ ይህ ብዙም አያሳስብም:: ለአንባቢ ግልጽ መሆን ያለበት ሌላ ጉዳይ ቢኖር ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ የሚያተኩረው የድኅረ 97 ምርጫ ጊዜን ነው:: ይህ ጥናት ምርጫውን ተከትሎ የነበሩትን የእርቅ ሙከራዎች አያጠቃልልም:: ምንም እንኳን ከዚህ ውጭ የጊዜ ገደብ ባይደረግም በርዕሱ ላይ የተጻፉት ጽሁፎች ለንባብ የበቁት ከ2010 ጀምሮ
መሆኑን ግንዛቤ ወስጃለሁ:: የጥናቱ ዋና ዋና ግኝቶች ቀጥለው ቀርበዋል::
የጥናቱ ግኝቶች
በአጠቃላይ ሲታይ ብሄራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ 18 ጽሁፎች ከ2010 እስከ 2014 ታትመዋል:: ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉ በ2014 ብቻ የታተሙ ናቸው:: አብዛኞቹ (14ቱ) በ2013 እና በ2014 የተጻፉ ናቸው:: ሰባቱ በአማርኛ ሲጻፉ ቀሪዎቹ 11ዱ ደግሞ በእንግሊዝኛ ተጽፈዋል:: የ16ቱ መጣጥፎች አርእስትና ሙሉ ይዘታቸው ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ሲሆን ቀሪዎቹ ሁለቱ የተጻፉት ግን በሌላ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው:: ቢሆንም ግን ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ከተነሱት አበይት ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳል:: አብዛኞቹ መጣጥፎችን ያቀረቡት ብዙውን
ጊዜ በተለያዪ ሚዲያዎች የሚታወቁ ኢትዮጵያውያን ፕሮፈሰሮች ወይም ዶክተሮች ናቸው:: ሁሉም ጽሁፎች ከዚህ ጽሁፍ መጨረሻ ላይ በጸሃፍት ስም በታተሙበት ዓመት በርዕሳቸውና ጽሁፎች በታተሙባቸው ድረ ገጾች ተዘርዝረው ይገኛሉ አንባቢያን
ጸሃፍትን በቀላሉ ይለዩአቸው ወይም ያውቋቸው ዘንድ ሙሉ ስማቸውን በቅንፍ ውስጥ ጠቅሻለሁ:: አንድ ጽሁፍ በተለያዩ ድረ ገጾች ታትሞ ቢገኝም ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ ግን መጀመሪያ የተገኘበትን ድረ ገጽ ብቻ ይጠቅሳል::
ምንም
እንኳን ሁሉም ጽሁፎች
ብሄራዊ ውይይት መግባባትና እርቅ ዋና ጉዳያቸው ቢሆንም በዝርዝር ያተኮሩባቸው ጉዳዮች እንዲሁም የሰጧቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ግን የተለያዩ ናቸው:: በአጠቃላይ ሲታይ ግን የሚከተሉት ጉዳዮች በተለያዩ ጽሁፎች ተዳሰዋል::
·
የብሄራዊ
እርቅ ጥቅምና አስፈላጊነት
·
እርቅ
የሚያስፈልጋቸው
አካላት
·
እርቁን
ማን ማስተባበር ወይም መጀመር እንዳለበት
·
እርቁ
እንዴት ሊካሄድ እንደሚችል
·
ብሄራዊ
እርቅና ፍትህ እንዴት ሊታዩ እንደሚገባ
እነዚህን ጉዳዮች
በተመለከተ የተገኙት 18ቱ መጣጥፎች
ምን እንዳስቀመጡ ቀጥሎ በአጭሩ
ቀርቧል:: በቅንፍ የተመለከቱት የጸሃፍት ስምና መጣጥፎች የታተሙበት ዓመታት ናቸው:: ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው በዋናና ጠቅላላ ሃሳቦች ዙሪያ ስለሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመረዳት በአባሪ መልክ የተያያዙትን
18ቱን ጽሁፎች ማንበብ ይጠቅማል:: እንደገና የማሳስበው ጉዳይ ቢኖር 18ቱም ጽሁፎች ሁሉንም ከላይ የተዘረዘሩትን ንዑስ ጉዳዮች እንዳላተቱ ነው::
ምንም እንኳን ሁሉም ጽሁፎች ብሄራዊ ውይይት መግባባትና እርቅ ዋና ጉዳያቸው ቢሆንም በዝርዝር ያተኮሩባቸው ጉዳዮች እንዲሁም የሰጧቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ግን የተለያዩ ናቸው:: በአጠቃላይ ሲታይ ግን የሚከተሉት ጉዳዮች በተለያዩ ጽሁፎች ተዳሰዋል::
እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የተገኙት 18ቱ መጣጥፎች ምን እንዳስቀመጡ ቀጥሎ በአጭሩ ቀርቧል:: በቅንፍ የተመለከቱት የጸሃፍት ስምና መጣጥፎች የታተሙበት ዓመታት ናቸው:: ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው በዋናና ጠቅላላ ሃሳቦች ዙሪያ ስለሆነ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመረዳት በአባሪ መልክ የተያያዙትን 18ቱን ጽሁፎች ማንበብ ይጠቅማል:: እንደገና የማሳስበው ጉዳይ ቢኖር 18ቱም ጽሁፎች ሁሉንም ከላይ የተዘረዘሩትን ንዑስ ጉዳዮች እንዳላተቱ ነው::
የብሄራዊ እርቅ አስፈላጊነትና ጥቅም
ሁሉም ጽሁፎች ብሄራዊ መግባባትና
እርቅ እጅግ ተፈላጊ የሆኑ ማኅበራዊ እሴቶችን ለመመስረትና ለማጽናት ወሳኝ እንደሆነ ያስገነዝባሉ:: እንዲሁም ከሌሎች የትግል ስልቶች አግባብነትና አተገባበር ጋር
ብሄራዊ እርቅን ያወዳድራሉ ያነጻጽራሉ:: አብዛኞቹ ጽሁፎች ብሄራዊ እርቅ
የሚያስፈልገው ኢትዮጵያ ያለችበት ዘርፈ ብዙ ችግር ተባብሶ ወደ ከባድ ቀውስ እንዳትገባ ስለሚያደርግ እንደሆነ ያትታሉ:: ያሉትን ችግሮች በህዝባዊ አመጽም
ሆነ በጦርነት ለመፍታት አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ተያይዞ ሊመጣ የሚችለው ቀውስ በቶሎ ማቆሚያ ሊኖረው እንደማይችል የብዙ
አገሮችን ተሞክሮ በማንሳት ብዙዎች ያስጠነቅቃሉ:: ለምሳሌ ያህል ጥቂት ስለብሄራዊ
እርቅ ጥቅም ወይም አስፈላጊነት የተሰጡት ማሳመኛዎች ቀጥለው ቀርበዋል::
- ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በምርጫ ካልሆነ በጦርነትም
ካልተቻለ ህዝባዊ አመጽም አደጋ ካለው ብሄራዊ የእርቅ
መንግስት ከመመስረት ውጭ ሌላ ምን አማራጭ የለም (መሳይ ከበደ
2013/2014)
- የመንግስት ባለሥልጣናት
ሳይቀሩ ስለሚፈልጉ ብሄራዊ እርቅን ለመተግበር የማይቻል አይደለም
(ተጋ 2013)
- በቋንቋ በዘር
በሃይማኖት በፖለቲካ ምክንያት ጥላቻ ያደረባቸውን አካላት ለማገናኘት ይረዳል (ዳዊት ተሾመ 2013)
- ብሄራዊ እርቅ በሚገባ ከተያዘና ከተጠናቀቀ አምባገነኖችን ሳይቀር ነጻ የሚያወጣ ነው ሁሉም ተሳታፊ ስለሚሆን ጦርና የጦር ወሬዎች ታሪክ እየሆኑ ይሄዳሉ ይህ መንገድ የሰው ህይወትም ሆነ ንብረትና ሃብት አያጠፋም በመሆኑም ይህ የፖለቲካ መስመር ጭስ አልባ ሊባል ይችላል ስለሆነም በሚያስፈራ ዝምታ ውስጥ ያለውን የሰፊውን የኢትዮጵያን ህዝብ ቀልብ ሊስብ ይችላል ለመግባባትና ለእርቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ በዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ ተቀባይነት ስላለው አስፈላጊውን ድጋፍና ማበረታቻ ማግኘት አይከብድም
በመጨረሻም ይህ የትግል ስልት ቀጣይነት ያለው ሰላምና እድገት እንዲመጣ ፈር ይቀዳል (ተክሉ አባተ 2013/2014)
- ቀጣይነት ላለው
ሰላምና ጤናማ ማኅበረሰብ ለመፍጠር መግባባትና እርቅ ማድረግ ወሳኝ ነው (ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቂ አኢጋን 2014
የሚታረቀው ማን ነው?
ይህን
ጉዳይ በተመለከተ በቂ ትንተና አልተሰጠበትም:: ጠቅለል ያሉና ግልጽነት የጎደላቸው ሃሳቦች ግን ተቀምጠዋል:: ከአብዛኞቹ ጽሁፎች ጀርባ
ተቀምጠው የሚገኙት ነጥቦች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እርቅ የሚደረገው ወይም መደረግ ያለበት በመንግስትና በህዝቡ መካከል ነው::
መንግስት በዳይና ህዝብ ተበዳይ ስለሆኑ የሁለቱ መወያየት መግባባትና መታረቅ ወሳኝ እንደሆነ ያብራራሉ:: እንዲሁም አንዱ ህዝብ
ወይም ብሄር ከሌላው ጋር በጥርጣሬና በመፈራራት ስለሚኖር መታረቅ እንዳለበትም የሚጠቁሙ አሉ:: በተጨማሪም መግባባትና
እርቅ በግለሰቦች መካከል ያለውን ያልጠራ ስሜትም ለማከም ማገልገል እንዳለበት የጠቆሙ አሉ (አኢጋን
2014):: ከዚህ ባለፈ ግን ጉዳዩን
ብትንትን አድርጎ ያስቀመጠ ጽሁፍ የለም::
አንዳንዶች (ለምሳሌ ያዕቆብ ኃይለማርያም 2014) ማን ከማን ተጣላና
ነው እርቅ የሚያስፈልገው ብሎ መቀለድ ዋጋ እንደሚያስከፍል ሲያስጠነቅቁ ሌሎች (ለምሳሌ
ቴዎድሮስ ኪሮስ 2014; ተክሉ አባተ 2014 )ደግሞ በደፈናው በእርቁ መሳተፍ ያለባቸው ተቃዋሚ ኃይሎችና ድምጹን ያጠፋው አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንዲሁም የፖለቲካ እስረኞች መሆን እንዳለባቸው ይጠቁማሉ:: አኢጋን ደግሞ የመጀመሪያ ደረጃ
እርቅ የሚያስፈልገው በዘር በቋንቋ በሃይማኖትና በፖለቲካ በሚለያዩ ቡድኖች መካከል ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ ብሄራዊ እርቅ መደረግ
እንዳለበት ይጠቁማል:: በአጠቃላይ ሲታይ እርቅ
የሚያስፈልገው በህዝብና በመንግስት መካከል ብቻ ሳይሆን ወረድ ብሎም በየደረጃው መከናወን እንዳለበት ጽሁፎች ጠቁመዋል:: ይሁን እንጅ መንግስትና ህዝብ ዋናዎቹ እርቅ የሚያስፈልጋቸው
አካላት እንደሆኑ ሁሉም ጽሁፎች ያመላክታሉ::
እርቁን ማን ያስተባብረው?
ብሄራዊ እርቁን ማን ማስተባበር
እንደሚገባው ግልጽ የሆኑ ሦስት ዋና ዋና አማራጮች ተቀምጠዋል:: አንድ እርቁን መጀመርና ማስተባበር ያለበት መንግስት እንደሆነ ያተቱ አሉ (ለምሳሌ ዘላለም
እሸቴ 2014; መሳይ ከበደ 2013/2014 እና ገላውዲዎስ አርአያ 2010):: ፍላጎትና ዝግጁነት ካለው መንግስት ካለበት ብሄራዊ ኃላፊነትና ካለው አቅም አኳያ
ይህን የማስተባበር ሥራ ቢወስድ እንደማይከብደው ይገመታል:: ሁለት እርቁን መምራት ያለባቸው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው የሚሉም አሉ (ለምሳሌ ዋለልኝ
መኮንን 2012 እና ቴዎድሮስ ኪሮስ 2014):: ይህ አማራጭ ከፖለቲካው ሜዳ
በመንግስት እየተገፉ ያሉት ኃይሎች ሂደቱን እንዲመሩት ያመቻቻል:: ሦስት መንግስትና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዋና የእርቁ አካል ስለሆኑና
በዳይና ተበዳይም ስለሆኑ ነጻና ገለልተኛ ኢትዮጵያውያንን ያቀፈ አስታራቂ ግብረ ኃይል የእርቁን ሂደት
መምራት አለበት የሚሉም አሉ (ለምሳሌ ተክሉ
አባተ 2013 2014)::
ከነዚህ አማራጮች ለየት ያሉም አሉ:: ሁሉን አቀፍ የምክክር ጉባዔ እንዲጠራ ያሳሰቡም አሉ (ሰሎሞን ታረከኝ 2011):: መገናኛ
ብዙኅን አስተዋጽዖ ማድረግ እንደሚችሉ ቢጠቀስም ሂደቱን ማን እንደሚመራውና እንደሚጀምረው ግን ግልጽ አይደለም:: እንዲሁም ወጣቱ ትውልድ ወደብሄራዊ እርቅ የሚያደርሰውን ውይይትና ምክክር በበላይነትና በባለቤትነት መምራት እንዳለበት
ያሳሰቡ አሉ (አለማዬሁ
ገብረ ማርያም 2012):: የተማረው ወጣቱ ትውልድ የትናንቱ ትውልድ ከሚዳክርበት የግራና የቀኝ
የፖለቲካ አመለካከት ነጻ ሆኖ የእርቁን ሂደት ቢመራው እጅግ እንደሚሻል ተጠቁሟል:: ይህ እንዴት መካሄድ እንዳለበትም የመነሻ ሃሳቦች ተሰጥተዋል::
እርቅ እንዴት ይካሄድ?
ብሄራዊ መግባብትና እርቅ እንዴት መካሄድ እንዳለበት በርከት ያሉ ትንተናዎች ተሰጥተዋል:: ብዙዎች (ለምሳሌ ተክሉ አባተ
2014; ዘላለም እሸቴ 2014; ሰሎሞን ታረከኝ 2011; አለማዬሁ ገብረ ማርያም 2012; ገላውዲዎስ አርአያ 2010)
ከእርቅ በፊት ቀጣይነት ያላቸውና
ሁሉን አቀፍ ክርክሮችና ውይይቶች መካሄድ እንዳለባቸው ጠቁመዋል:: ብሄራዊ ክርክሮችና ውይይቶች መንግስትና
ተቃዎሚ ድርጅቶችን በእኩልነት
የሚያስተናግዱ: የእያንዳንዳቸውን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየት የሚያስችሉ: እንዲሁም በእውነት ላይ የተመረኮዙ
መሆን እንዳለባቸው ተጠቁሟል:: ሌሎች ስለእርቅ ሂደት የተዘረዘሩ
ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው::
- በውይይቶች ጊዜ እውነታን መለየትና እውቅና መስጠት (ያዬ አበበ 2014)
- ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ መለየት: ከዚያም የስምምነት ሰነድ መፈራረም (ገለታው ዘለቀ 2014)
- ችግሮችን መመርመር: ተጎጅዎችን መለየት (ዳዊት ተሾመ 2013)
- የተሰሩ ወንጀሎችን
መለየት: መከላከያና ደህንነት ተቋማትን ገለልተኛ
ማድረግ: በነጻ
የመናገር መብት ማስከበር (ዋለልኝ መኮንን 2012)
- መጀመሪያ ወጣቶች ኢ-መደበኛ ውይይቶችን በአካባቢያቸው መጀመር: ንቃተ ኅሊናን የሚያዳብሩ መርሃ ግብሮችን ማዘጋጀ: ውይይቶች ግልጽነትን ዲሞክራሲያዊ አሠራርን የተከተሉ: ሰብአዊ መብቶችንና ነጻነትን ማዕከል ያደረጉ ይሁኑ:: የራስን ችሎታና አቅም መመዘን: ያሉትን ተቋማት ለዚሁ ዓላማ መጠቀም: ከትናንቱ ትውልድ የአዙሪት ፖለቲካ መጠንቀቅና ከስህተቱ መማር (አለማዬሁ ገብረ ማርያም 2013)
- መንግስት ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለአገር እድገት አስተዋጽዖ
እንደሚያደርጉ ይመን:: እነሱንም ከማሳደድና ከመፍራት
ይልቅ ያቅርባቸው:: በዘር ላይ የተመሰረተውን
የፌደራል አወቃቀር እንደገና ያጢነው (ገላውዲወስ አርአያ 2010)
- የታሰሩትን ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲና የሃይማኖት መሪዎችና አባላትን በሙሉ መፍታት፤ የጸረ-ሽብርተኛ አዋጅ መሰረዝ፤ እና የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሕዝባዊ ድርጅቶች አባላትና መሪዎችን በሽብርተኛነት የተፈረጁትንም አጠቃሎ የያዘ አንድ ጉባዔ በአዲስ አበባ ማካሄድ (ያዕቆብ ኃይለ ማርያም 2014)
- የብሄራዊ እርቅ መድረኮች ይዘጋጁ (ቴዎድሮስ ኪሮስ 2014)
- ከልብ የሆነ ይቅርታ መጠየቅና ማድረግ (አኢጋን 2014)
እርቅና ፍትህ
ብሄራዊ መግባባትና እርቅ በሚጀመርበት ጊዜ የፍትህ አገሯ ወዴት ይሆናል? ይህ ጥያቄ ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ አኳያ በቂ መልስ ያገኘ
አይመስልም:: ከ18ቱ መጣጥፎች ውስጥ ሦስት
የሚሆኑት ብቻ ይህን ጉዳይ በግልጽ አንስተዋል:: በጣም ለተበደሉ ወገኖች ፍትህ (ለምሳሌ ካሳ) መደረግ እንዳለበት ጠቆም ያደረጉ አሉ (ያዬህ አበበ 2014; አኢጋን 2014):: በጣም የተበደሉት ወገኖች እነማን
እንደሆኑና ምን አይነት ካሳ በማን መሰጠት እንዳለበት ግን የተብራራ ነገር የለም:: ከሁሉም ጽሁፎች ገለታው ዘለቀ (2014 ገጽ 4)የጻፉት የእርቅና የፍትህ ግንኙነት
እጅግ በተሻለ መልኩ እንደሚከተለው ያብራራል:: ዋናው መልእክት እርቅ በሚደረግበት ጊዜ እንደአስፈላጊነቱ ፍትህም ሥራ ላይ ሊውልበት የሚችል
እድል እንዳለ ያመላክታል:: የእርቅና የፍትህ ውሳኔዎች
በአንድ ላይ ተጣጥመው መሄድ እንደሚችሉ ባህላችንን በምሳሌነት እያነሳ ይተነትናል::
በስምምነት ላይ የተመሰረተ ባህላዊ ውህደት ብሄራዊ እርቅን በኢትዮጵያ የሚያየው እንደዚህ ነው። በዚህ ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ብሄራዊ እርቁ ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስን መሰረት ያደረገና በሚያድግ ዴሞክራሲ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ስምምነት ማለት ነው። ይህ ማለት ግን ሪትሪቢዩቲቭ ጀስቲስ ቦታ የለውም ማለት ኣይደለም። በኣሁኑ ሰዓት በከፍተኛ ሙስናና ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸሙ ያሉ ሰዎች ይህንን ኣሳባችንን እያዩ እንደ ጅልነት ኣይተው ከስልጣን እስኪወርዱ በግፋቸው እንዲቀጥሉ በር ኣይከፍትም። የብሄራዊ እርቅ ሰነዱ እንደነዚህ ኣይነት ሰዎችን በቡድን እያየ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ወደ ፍርድ ሊያመጣቸው መቻሉ ኣያጠያይቅም። እንደ ቡድን እንደ ሃገር ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻችንን ዝግ እያለ ሊሰራጭ በሚችል የሪዲስትሪቢዩሽን ዘዴ ተመጣጣኝ እድገት ለማምጣት መስማማት፣ ፖለቲካዊ ተሳትፎን ከባህላዊ ውህደት ስምምነት ኣንጻር ኣይቶ ከብሄር ፖለቲካ ኣውጥቶ በኣንድ ብሄራዊ ማንነት ስር ለመገንባት መስማማት፣ ዋና የሃገሪቱን ቋንቋዎችን ቁጥር መጨመር ኣጠቃላይ ፈውስን ለማምጣት ይጠቅማል። ኢትዮጵያ ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ላይ እንድታተኩር የሚያደርጋት ለዘላቂ ሰላምና ልማት ኣንድነት የሚረዳት ሲሆን ይህ የፍትህ ኣሰጣጥ ዘዴ በኢትዮጵያ ቡድኖች ዘንድ የተባረከና የሚበረታታ ነው። የኦሮሞ ስርዓትን ብናይ ለሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ ትልቅ ቦታ ኣለው። ይቅር ማለትን፣ በዳዩን ከመቅጣት ይልቅ ተበዳዩን መካስን ያበረታታል። ኣማራው ኣካባቢ ያለውን የሽምግልና ስርዓት ስናይ በኣብዛኛው ሪስቶሬቲቭ ጀስቲስ የሚበረታታበት
ሁኔታ ኣለ። በደቡብ፣ በምስራቅ በተለይም በሶማሌ ክልል ይህ የፍትህ ስርዓት ከፍተኛ ተጽእኖ ኣለው ገለታው
የማጠቃለያ ሃሳቦች
ይህ ጥናት
ብሄራዊ መግባባትና እርቅን በተመለከተ በርካታ ጠቅለል ያሉ ጉዳዮችን ዳሷል:: ዝርዝር ትንተናዎችን ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት መጣጥፎች ማግኘት
ይቻላል:: ለማጠቃለል ያህል ግን ጥቂት ነጥቦችን ማንሳት ያስፈልጋል::
አንደኛ ምንም እንኳን የተዳሰሱት 18ቱ መጣጥፎች የብሄራዊ መግባባትና እርቅን ጠቀሜታና አስፈላጊነት ከሌሎች የትግል ስልቶች ጋር በማነጻጸርና በማወዳደር ለማቅረብ መሞከራቸው
ክፉ ባይሆንም ጉዳዩን በሌላ መነጽር መመልከቱ ይበልጥ ጠቃሚ ነው:: ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ተጀምሮ የተወሰነ አጓጊ ደረጃ እስኪደርስ
ድረስ ሌሎችን ትግሎች ማቆም ላያስፈልግ ይችላል:: ሌሎች ትግሎች (ለምሳሌ የተቀናጀና ደረጃ በደረጃ የሚመራ ህዝባዊ እምቢተኝነት
http://tekluabate.blogspot.no/2014/08/blog-post_6.html#more) ምናልባትም መንግስት የእርቁን ጉዳይ በሚገባ እንዲያጤነው ሊያስገድዱት ይችላሉ:: በመሆኑም የእርቅን ጠቀሜታ ለማውሳት
ሌሎች ትግሎችን ማኮሰስ የግድ አይጠበቅም::
ሁለተኛ የተወሰኑ ጽሁፎች ህዝብ ለህዝብ መታረቅ እንዳለበት አሳስበዋል:: ምንም እንኳን ሃሳቡ በራሱ ክፉ ባይሆንም ለበርካታ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ የሆነውን አካል ማለትም መንግስትን ላላ አርገን
እንድንይዝ የሚጋብዝ :: በመጀመሪያ ደረጃ ህዝብ ለህዝብ
ሊጣላ አይችልም:: ከበስተጀርባ ያሉ ተንኳሽ የመንግስት ፖሊሲዎችና ፕሮፓጋንዳዎች የህዝብን ልብ ይከፍላሉ:: መንግስት ከትንኮሳው ሁሉ ታቅቦ ህዝቦች በሰላምና በአንድነት እንዲኖሩ ቢሰራ በአጭር ጊዜ ውስጥ የነበረን መከባበርና
መተሳሰብ ይመለሳል:: ስለዚህ መታረቅ ያለበት መንግስ
ከህዝብ ጋር ነው ብዬ አምናለሁ::
ሦስተኛ መንግስትም ሆነ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች እውነተኛ እርቅን ጀምረው ማስተባበር ይችላሉ ማለት ዘበት ነው:: መንግስት እንደግለሰብ ቂመኛ
በቀለኛና ትምክህተኛም ነው:: ለተቃዋሚዎች ያለው ንቀትና
ጥርጣሬ መጠን የለውም:: እርቅን እሱ ቢጀምር የመሸነፍና
የመዋረድ ያህል ይመለከተዋል:: ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ከመንግስት
ጋር ያላቸው ቅራኔ እርቅ ለመጠየቅ የሚያበቃ አይመስልም:: ሰጥቶ የመቀበልና የማሳመን ችሎታና ፍላጎት እስካሁን አላየንም:: በመሆኑም ሌላ ገለልተኛና አንጻራዊ በሆነ መልኩ ንጹህ ኢትዮጵያውያን የተሰባሰቡበት አካል ያስፈልጋል:: ይህን አካል የሚያቋቁመው አካል: የሚቋቋምበት መስፈርት: የሚኖረው ዝርዝር የሥራ ድርሻ: የሚጠቀማቸው ዘዴዎች: ወዘተ ግን ጥርት ብለው ለውይይት ቢቀርቡ የተመረጠ ነው
እላለሁ:: እንዲሁም ፍትህና እርቅ ምን
ያህል የሚዛመዱና የሚቃረኑ እንደሆነ የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት አስቀድሞ መተንተን ያስፈልጋል::
በአጠቃላይ ይህ አስተባባሪ ኃይል ከእርቅ በፊት በእርቅ ጊዜና ከእርቅ በኋላ ሊሟሉ የሚገባቸውን ሁኔታዎች እጅግ በዝርዝር
አዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አቅርቦና በውይይት አዳብሮ ሊንቀሳቀስ ይገባል:: ይህ ቀላል ሥራ ስላልሆነ የሚመረጡት ሰዎች ስሜታቸውን የሚቆጣጠሩና የሞራል ብስለት ያላቸው: አዋቂዎችና አስተዋዮች: እንዲሁም የመግባባትና ጫናን የመቋቋም አቅም ያላቸው ሊሆን
ይገባል:: ልዩ ልዩ አይነት መስዋዕትም
ለመክፈል የተዘጋጁ መሆን አለባቸው:: በመሆኑም ብሄራዊ መግባባትና እርቅ በብርቱ ልፋትና መከራ የሚመጣ እንጅ እንደሚታሰበው ‘ሰላማዊ’ ብቻ ላይሆን ይችላል::
የመጀመሪያው ችግር የሚሆነው ይህን አስታራቂ ኃይል ማቋቋም ነው:: ማን ነው ይህን ሊያነሳሳው የሚችለው? በተለያዩ አካላትስ ተቀባይነት ይኖረዋል? ፍላጎትና ለኢትዮጵያ መልካም ራእይ ያለው ማንኛውም አካል
ሊጀምረው ይችላል:: ቢያንስ ቢያንስ ይህ ጥናታዊ
ጽሁፍ የገመገማቸውን 18ቱን በብሄራዊ መግባባትና እርቅ ላይ ያተኮሩ መጣጥፎችን ያቀረቡት ምሁራን በመመካከር ለጉዳዩ የሚሆን መሪ
ሃሳብ roadmap ማዘጋጀትና ለውይይት ማቅረብ ይችላሉ:: ጥናቱን በማካሂድበት ጊዜ የታዘብኩትና
ወደፊት ትኩረት ሊሰጠው
የሚገባው ጉዳይ ግን አለ::
ሁሉም መጣጥፎች ራሳቸውን
የቻሉና ሌላውን ለድጋፍም
ይሁን ለትችት በፍጹም
የማይጠቅሱ ናቸው::
ስለአንድ ጉዳይ በሚጽፉ
ሰዎች መካከል ምንም
አይነት ‘መናበብ’
እንደሌለ አመላካች ነው:: ሁሉም
የግል ሩጫውን ተያይዞታል::
ይህን አቁመን በአንድ ጉዳይ ላይ የምንጽፍ ሰዎች መናበብ ብንጀምርና የመነሻ
ሃሳብ ብናቀርብ ብሄራዊ ግዴታችንን እንደመወጣት ይቆጠራል:: የያዘውን የወረወረ ፈሪ አይባልም!!!
ስለብሄራዊ እርቅ የተጻፉ ጽሁፎች
በአማርኛ የተጻፉ
- ተክሉ አባተ
2014 ጎጂ ባህሎቻችን
(የመጨረሻው
ክፍል).
http://www.ethiomedia.com/14store/gojjee_bahlochachin_final_part.pdf
- ተጋ 2013 አገራችንን በእርቅ እንታደጋት” http://www.goolgule.com/reconciliation-the-way-out/
- ያዕቆብ ኃይለማርያም 2014 ብሔራዊ መግባባት ወይስ አገራዊ ውድመት? http://www.zehabesha.com/amharic/archives/33174
- ያዬ አበበ 2014 እውነታ + እውቅና + ፍትህ = እርቅ. http://www.65percent.org/files/EwnetaEwqinaFeteh_Yaye_Abebe.pdf
- ዳዊት ተሾመ 2013 የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ . ክፍል 2 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10340
- ዳዊት ተሾመ 2013 የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ. http://www.goolgule.com/on-the-question-of-national-reconciliation/
- ገለታው ዘለቀ
2014 ኢትዮጵያ የብሄራዊ
እርቅ
ኮሚሽን
ማቋቋም
የሚያስፈልጋት
ጊዜ
ላይ
ናት.
http://www.ethiomedia.com/14store/bherawi_erq.pdf
በእንግሊዝኛ የተጻፉ
- Alemayehu G
Mariam 2013 Cheetahs, Hippos and Saving
Ethiopia. http://ethiomedia.com/2012_report/4559.html
- Ghelawdewos Araia 2010 National Reconciliation and National Development in Ethiopia.
http://ethiopianunitydiasporaforum.com/news/national-reconciliation-and-national-development-in-ethiopia/
- Mesay Kebede 2014 Democracy
and its Trade-off: Ethiopia’s Path to National Reconciliation. http://www.zehabesha.com/democracy-and-its-trade-off-ethiopias-path-to-national-reconciliation/
- Messay Kebede 2013 Which Way Ethiopia: Revolution, Civil War, or
National Reconciliation? http://www.abugidainfo.com/index.php/21346/
- SMNE 2014 Reconciliation http://www.solidaritymovement.org/reconciliation.php
- Solomon Tarekegn 2011 A Call for
a National Conference to Save Ethiopia! http://ecadforum.com/2011/01/20/a-call-for-a-national-conference-to-save-ethiopia/
- Teklu
Abate 2013 Inclusive discourse: A
prelude to national reconciliation. http://www.zehabesha.com/inclusive-discourse-a-prelude-to-national-reconciliation/
- Teodros Kiros 2014 Reconciliation is the language of communicative rationality. http://www.africanidea.org/reconcilation_kiros.html
- Walelgn Mekonnen
2012 It is a time
for national reconciliation and accountability. http://www.ethiopianreview.com/mobile/?p=2781
- Zelalem Eshete
2014 Ethiopia: Call for Opposition & Government. http://www.zehabesha.com/ethiopia-call-for-opposition-government/
- Zelalem Eshete
2014 Ethiopia:
Reconciliation Pyramid.http://www.zehabesha.com/ethiopia-reconciliation-pyramid-zelalem-eshete-ph-d/
ነጻነት ለኢትዮጵያ!!!
ገንቢ አስተያየት ወይም ጥያቄ ካለዎት በteklu.abate@gmail.com ይላኩ!
ነጻነት ለኢትዮጵያ!!!
Subscribe to:
Posts (Atom)
ተልዕኳችን | Our Mission
“65 ፐርሰንት” ትርጉም? የኢትዮጵያ ህዝብ 65 በመቶው እድሜያቸው ከ24 አመት በታች ነው። ተልዕኳችን ለመጪው ትውልድ የመግባባትን ፓለቲካ በአርአያነት ማውረስ ነው። ግባችን ለፓለቲካዊ እርቅና መግባባት መሟገትና ፋና ወጊ መሆን ነው።
What is “65 percent”? 65% of Ethiopia’s population is under 24 years old. Our mission is to model a culture of political concensus for the 65%. Our goal is to advocate for, and initiate reconciliation and consensus among Ethiopians.




